2018-07-02 15:20:00

ር,ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ መንግሥታት ስለሰላም መንጋገር መጀመራቸው መልካም የሚባል ጅምር ነው


ር,ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ መንግሥታት ስለሰላም መንጋገር መጀመራቸው መልካም የሚባል ጅምር ነው

የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሰራት ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ቅዱስነታቸው በሰኔ 24/2010 . ለዓለም ያስተላላፉት ሳምንታዊ መልእክት. . .

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁን የተናገሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 24/2010 ዓ.ም በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ ካደርጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ደንግል ማሪያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነው፣ ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ የሚደገመው የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መጸነሱን በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በሶሪያ እና በኒካራጉዋ እየተከሰተ የሚገኘው ግጭት መፍትሄ እንዲፈለግለት ጥሪ ማድረጋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ኢትዮጲያ እና ኤርትራ መንግሥታት መካከል ለ20 ዓመታት ያህል የነበረው ፍጥጫ አቁመው ወደ ሰላም ጎዳና መመለሳቸው ቅዱስነታቸው ተስፋ ሰጪ የሆነ አጋጣሚ መሆኑን በድናቆት ተናግረዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት ስማንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እየተከሰቱ የሚገኙ ግጭቶች እልባት እንዲፈለግላቸው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን በሶሪያ በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልክ ባገረሸው የእርስ በእርስ ጦርነት ለባለፉት በርካታ አመታት በስቃይ ላይ በነበረው ሕዝብ ላይ ተጫምሪ ስቃይ መጨመር የጭቃኔ ተግባር በመሆኑ የተንሳ ለሶሪያ ግጭት ባለድርሻ አካላት መፍትሄ እንዲያፈላልጉ ቅዱስነታቸው ጥሪ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በአሁኑ ወቅት በኒካራጓ በፖሌቲካዊ አመለካከት ልዩነት የተነሳ እየተከሰተ የሚገኘውን ግጭት በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በኒካራጓ ሰላም ይፈጠር ዘንድ ጸሎት እንደ ሚያድርጉ ጠቅሰው በእዚያ የሚገኙት የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ሰላም እንዲፈጠር እያደርጉ የሚገኙትን ጥረይ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ቅዱስነታቸው አሳስበው በንካራጓ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሚና ሊሆን የሚገባው ወደ ዲሞክራሲ የሚደርገውን ሽግግር በሰላማዊ መነገድ እንዲጠናቀቅ ውይይት እንዲካሄድ ማግባባት ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የሶሪያን የእርስ በእርስ ጦርነት በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው የሶሪያን ጉዳይ በማስብበት ወቅት ሁሉ ልቤ በሐዘን ይሞላል ያሉት ቅዱስነታቸው የሶሪያ ሕዝብ ሰላም ያገኝ ዘንድ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ መንግሥታት ከበርካታ አመታት በኃላ በመካከላቸው ሰላም ለመፍጠር መስማማታቸው በጣም የሚያበረታታ እና መልካም የሆነ ዜና መሆኑን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነት የሰላም ውይይቶች ገንቢ በመሆናቸው የተነሳ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸው ይህ የሰላም ስምምነት ለአፍሪካ ቀንድ እና እንዲሁም ለመላው የአፍሪካ አህጉር ጠቃሚ እና በአብነት ሊጠቀስ የሚገባው ጉዳይ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

በበርካታ ግጭቶች መካከል በእውነቱ ታሪካዊ ተብሎ ሊገለጽ በሚችል መልኩ ተነሳሽነት በመውሰድ በእርግጥ ይህንን መልካም ዜና ነው ለማለት ይቻላል፣ ከሃያ አመታት በኃላ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ መንግሥታት ስለሰላም መንጋገር መጀመራቸው መልካም የሚባል ጅምር ነው።  የእዚህ ዓይነቱ መልካም ግንኙነት በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ ሁለቱ ሀገራት በአጠቃላይ ለመላው አፍሪካ የተስፋ ብርሃን ሊፈነጥቅ የሚችል አጋጣሚ ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.