መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  
የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣

RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ስለቤተሰብ የጀመርነውን ትምህርተ ክርስቶስ እንቀጥላለን፣ ዛሬ እንደመሪ ቃል የምንወስደው “አባት” የሚለውን ቃል ነው፣ ይህች ቃል ለእኛ ክርስትያኖች እጅግ ተወዳጅ ናት ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን አባት ብለን እንድንጠራው ስላስተማረን ነው፣ የዚች ቃል ትርጉም ጥልቀት ያገኘውም ጌታ ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ መጠራት ከጀመረበትና ከእርሱ ጋር ያለውን ልዩ ግኑኝነት ለመግለጥ ከተጠቀመበት ወቅት ጀምሮ ነው፣ የታላቁ ምሥጢረ ቅድስት ሥላሴ የአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ ግኑኘት የክርስትና እምነታችን አንኳር መሆኑም ጌታ ኢየሱስ ግለጦልናል፣
አባት የሚለው ቃል ሁላችን የምንረዳው ዓለም አቀፍ ቃል ነው፣ መሠረታዊ ግኑኝነት የምትገልጽ ልክ እንደ የሰው ልጅ ታሪክ ጥንታዊት ናት፣ ይሰውረን እንጂ ዛሬ ኅብረተሰባችን አባት የለሽ ማኅበረሰብ ሆነዋል፣ በሌላ አነጋገር በም ዕራባዊው ባህል የአባት ቦታ ባዶ ቀርተዋል! እንደሌለ ሆነዋል፣ በመጀመርያ ይህ ሂደት ሕግ ከሚያስከብና ገዢ ከሆነው አባት እንዲያው ከበስተውጭ ከመጣ ጭቖና ነጻ እንደመውጣት እና ወጣቶች አለምንም ገደብ ለመራመድ የሚረዳ ሆኖ እየታየ ነው፣ ባለፉት ግዝያት በአንዳንድ ቤተሰቦች ወላጆች እንደገዢዎች ልጆቻቸውን እንደባሮች የሚጨቁኑ የልጅነት መብታቸውን የሚጥሱ ሆነው ልጆች ራሳቸውን ለመቻልና ለእድገት እንዳይራመዱ የሚከለክሉ ዓይነት  ...»ጌታ ኢየሱስ ክርስትያኖች አንድ እንዲሆኑ ይፈልጋል፣

RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን እና በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ቅድስነታቸው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ትናንትና የተጠናቀቀውን ስለ ክርትስያን አንድነት የተካሄደው የአንድ ሳምንት ጸሎት ዘክረው ስለ ክርስትያን አንድነት ጸሎት እንዲቀጥል አሳስበዋል፣
በማያያዝም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትያን ሕብረት እንደሚፈልግ ገልጠው በዕለቱ ከቀትር በኋላ በሮም በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ስለ ክርትያን አንድነት ሲካሄድ የሰነበተው ሳምንተ ጸሎት መጠቃለያ ሥርዓተ ቅዳሴ  ...»ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ አለ እውነተኛ መለወጥና ምህረት እውነተኛ ውኅደት አይኖርም

RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ውህደት የጸሎት ሳምንት መዝጊያ ምክንያት የውፉያንና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ ውፉያን ገዳማውያን ስለ አቢያተ ክርስቲያን ውኅደት ርእስ ዙሪያ ባዘጋጀው አውደ ጉባኤ የተሳተፉትን ተቀብለው ባስደመጡት ምዕዳን፦ ለውህደት የሚደረገው የጋራው ውይይት መንፈሳዊነት የውህደት ተንከባካብያን እንቅስቃሴ መንፈስ መሆኑ በማብራራት፣ መናንያንና ውፉያን ለውህደት ባተኰረው ዓላማ የሚያገለግሉ በዚህ ለውህደት ባቀናው የጋራው ውይይት አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ ካህናት  ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አምባገነን የፆታዊ ርእዮተ ዓለም ትምህርት አዲሱ የቅኝ አገዛዝ ሥርዓት

RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊሊፒንስ ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት አጠናቀው በመልስ ላይ እያሉ በተሳፈሩበት አይሮፕላን ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት ውይይትና ቃለ ምልልስ፦ በፊሊፒንስ ከአቢያተ ሰብ ጋር ያካሄዱት ግኑኝነትና የሰጡት ምዕዳን ዳግም በማስታወስ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አቢያተ ትምህርት ስለ ፆታ የሚሰጠው አዲስ ሕንጸት በእውነቱ ርእዮተ ዓለማዊ ቅኝ አገዛዝ መሆኑና ይኽም ጋብቻ ወይንም ትዳር ቃል ኪዳን የሚለው ቅዋሜ በአዲስ መልክ ለመግለጥ የሚሞርክርና ቤተሰብን የሚያወድም መሆኑ በማብራራት፣ እየተስፋፋ ያለው አዲስ የሥነ ፆታ ትምህርት ባለፉት የቅርብ ዘመናት  ...»


ሢሜተ ጵጵስና አዲስ ለቆመው የባህርዳርና ደሴ ኤጳርቅና

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢትዮጳያ የአዲስ አበባ ሊቀ ጳጳሳት ረዳት በመሆን ሲያገለግሉ ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ሊሳነ ክርቶስ ማተዎስ ሰማሁን ባህርዳንና ደሴን የሚያጠቃልል ላቆሙት አዲስ ኤጳራቅና ጳጳስ እንዲሆኑ መሰየማቸው ከቅድስት መንበር የተሰራጨ ዜና አመለከተ።
በዚህ አዲስ በቆመው ኤጳርቅና የካፑቺን ወንድሞች ማህበር የሲታውያን ገዳማውያን ማኅበር፣ ኮምቦናውያን ልኡካነ ወንጌል፣ ላዛሪስትና የድኾች አገልጋዮች ልኡካን ማኅበር፣ የኢየሱሳውያን ልኡካን፣ የቅድስት ሃና ደናግል ማኅበር፣ የፍቅር ልጆች፣ ቀርመሌሳውያን በነዲክታውያን የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም፣ የፍቅር ልኡካን ማኅበር የአፍሪቃ ልኡካን ደናግል ማህበር  ...»ሰባተኛ ሐዋርያዊ ዑደት ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ተጠቃልለዋል ፡
ቅድስነታቸው በማኒላ በሪዛል ፓርክ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅድሴ
7 ሚልዮን ህዝብ ተሳታፊ ሁነዋል ።


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኤስያ ክፍለ ዓለም በስሪላንካ እና ፍሊፒን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደቶች ዛሬ ተጠቃልለዋል ፡ አሁን ዝግጅታችን በሚሰራጨበት ግዜ ከፍሊፒን ርእሰ ከተማ ማኒላ ሮም ለኦናርዶ ዳ ቪንቺ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል።ትናንት እሁድ ረፋድ ላይ ካረፉበት ከቤተ ሊቀ ጳጳሳት ማኒላ ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ጥንታዊ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቶማስ ተጉዘው ከየሃያማኖት አባቶች ጋር ተገኛኝተዋል።የማኒላ ቅዱስ ቶምስ ዩኒቨርሲቲ ከአራት ዓመታት በፊት የተቆረቆረ 45 ሺ ተማሪዎች የሚያስተናግድ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቶምስ ዩኒቨርሲቲ  ...»


ከዓለም 
ኾርገ ሚሊያ፦ እስያ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልብ ነች

RealAudioMP3 የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅርብ ጓደኛ አርጀንቲናዊ ጋዜጠኛና ደራሲ ኾርገ ሚሊያ ቅዱስ አባታችን የዛሬ ስድስት ወር በፊት በደቡብ ኮርያ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ይኸው እ.ኤ.አ. ከጥር 12 እስከ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በስሪ ላንካና ፊሊፒንስ በሚያካሂዱት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት አማካኝነት ለሁልተኛ ጊዜ ወደ እስያ ክልል ማቅናታቸው እስያ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልብ መሆንዋ የሚመሰክር ነው። ቅዱስ አባታችን ገና ካህን እያሉ በማኅበራቸው ወደ እስያ ወንጌላዊ ልኡክ ሆነው እንዲላኵ ያቀርቡት የነበረ ጥያቄ የሚያረጋግጠው እውነት መሆኑ ገልጠው፣ ባለፈው ዓመት በእስያ ምሥጢረ ጥምቀት  ...»


የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር፦ ጸረ ወንጀልና የወንጀል ቡድኖች ትግል ቆራጥና ወሳኝ ጥረት ይጠይቃል

የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በዓለማችን በተለያየ መልኩ በአዳዲስ የባርነት ሥርዓት ሥር የሰውን ልጅ ለክብር ዘራዥ ጸያፍ ተግባር የሚዳርገው ጸያፍ ተግባር የወንጀል ብድኖች የሚገለገሉባቸው ያመንዝራነት ሕይወት፣ አድልዎ፣ ብዝበዛ፣ የሰውን ለጅ በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ ሙስና ምግባረ ብልሽት የመሳሰሉት የወንጀል ብድኖች በገንዘብ ሃብት የሚያደልበው ኢሰብአዊ ተግባር ለማጥፋት ለሚያበቃው ቆራጥና ወሳኝ ጥረት ኃይል ማስተባበር ያለው አስፈላጊነት የተሰመረበት መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባሮች ሳንሆን ወንድማማቾች ነን በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ያስተላለፉት  ...»


የሥነ ጾታዊ ስሜት ትምህርት በቤተሰብ ላይ የሚሰነዘር የጥቃት ኅልዮ

RealAudioMP3 ጋዜጠኛና ደራሲ ማሪዮ አዲኖልፊ አምነስት ኢንተርናሽናል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር ስለ ፆታዊ ስሜት ትምህርት በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም አቢያተ ትምህርት ስለ ፆታዊ ስሜት ለሚሰጠው ትምህርት እንዲከተሉት በማለት አንዳዊ ፆታዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች ስለ ሚኖሩት ዓይነት ፆታዊ ስሜትና ወንዳ ገረድ ፆታዊ-ስሜት ያላቸውን የሚጠላና የሚያገል ባህል በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመቃወም” በሚል ርእስ ሥር ያወጣው አጭር የመመሪያ ጽሑፍ አስመልከተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ቤተሰብ ለአደጋ ከሚያጋልጠው ኅልዮ መከላከል አስፈላጊ ነው። ይኽ የአምነት ኢንተርናሽናል መመሪያ አደገኛ ኅልዮ ነው” በማለት  ...»


ዓለም አቀፍ የሕጻናት መርጃ ድርጅት መግለጫ

RealAudioMP3 ዕልባት ባጣው የሶሪያው ውስጣዊ ግጭት ሳቢያ 5.5. ሚሊዮን የአገሪቱ ሕጻናት ለአደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማኅበር ትላትና ስለ ሶሪያ ሕፃናት ወቅታዊ ሁኔታ ርእስ ሥር ባወጣው መግለጫ ጠቅሶ፣ አስቸኳይ የስብአዊ አርዳታ እንዲቀርብ አደራ በማለት፣ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የተጠቂው ሕፃናት ብዛት በእጥፍ እጅግ ከፍ ማለቱና አንድ ሚሊዮን የሚገመቱት ሕፃናት ግጭቱ በሚካሄድባቸው ክልሎች ታግተው የቀሩ ሲሆን፣ ለእነዚህ ሕፃናት አስፈላጊውና አሰቸኳይ የሰብአዊ እርድታ ለማቅረብ እጅግ አዳጋች መሆኑና፣ 1.2 ሚሊዮን ወደ ጎረቤተ አገሮች መሰደዳቸውና 4.3 ሚሊዮን በገዛ አገራቸው ውስጥ  ...»RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንጻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን ለጉብኝት የገቡት የረፓብሊካዊት ከፕ ቨርድ መራሔ መንግሥት ኾሰ ማሪያ ፐረይራን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
ርእሰ ብሔር ኾሰ ማሪያ ፐረይራ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተሰናብተው እንዳበቁም በሐዋርያዊ ሕንጻ በሚገኘው አቢያተ ፍርድ ተብሎ በሚጠራው የጉባኤ አዳራሽ በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ በብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፅዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘቸው የጠቆመው ...»


ቤተ ክርስትያን በዓለም 
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በጸናው መለያና በጋራ መከባበር ከምስልምና ሃይማኖት ጋር ውይይት

RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 1926 ዓ.ም. በልኡካነ ወንጌል ላፍሪቃ ማኅበር በቱዚያ አንድ በማለት የተነቃቃውና በሮማ ጳጳሳዊ የሥነ ምስልምና ሃይማኖት ተቋም በሚል መጠሪያ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ዝክረ 50 ዓመት ምክንያት ወደ ተዘጋጀው ዓውደ ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ይፈታ ብሎ ለመበየን ፈጣን ሂደትና ግብረ ገባዊ እርግጠኛነት ያስፈልጋል

RealAudioMP3 በቃል ኪዳን ክብር ዙሪያ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና ሥር ምሥጢረ ተክሊል በተመለከተ የሠፈረው የሕግ አንቀጽ ቅዋሜው ዝክረ 10ኛው ዓመት ምክንያት ጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ ወደ አዘጋጀው ዓውደ ጥናት ቅዱስ አባታችን ...»


ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፦ ህያው ቤተ ክርስቲያን በቪየትናም

RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባጠናቀቁት ዓለም ዓቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት የሸኙዋቸው የአስፍሆተ ወንጌል ለአሕዛብ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ የቪየትናም ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለወጣቶች፦ ማንባትንና ማፍቀርን ተማሩ

RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊሊፒንስ ርእሰ ከተማ ማኒላ በሚገኘው ቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ መንበረ ጥበብ በሚገኘው የስፖርት ሜዳ ከሳላሳ ሺሕ በላይ በሚገመቱ ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸው የአንዳንድ ወጣቶች የምስክርነት ቃል ...»


በጌታ መኖር

RealAudioMP3 የተወደዳችሁ ቤተሰቦች በክርስቶስ የተወደዳችሁ ሁሉ
በዚህ ምሽት እዚህ ተገኝታችሁ የመሰከራችሁት ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያኑ ያላችሁ ፍቅር ለማዳመጥ በመቻሌ እድለኛ ነኝ፣ የእንኳን ደህና መጡት ንግግር ላስደመጡት ለፊሊፒንስ ብፁዓን ...»
አባ ጋብርኤለ ማርያ አለግራ የተባሉ ፍራንቸስካዊ መነኵሴና የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ ለመጀመርያ ጊዜ ቅዱስ መጽሓፍን በቻይና ቋንቋ የተረጐሙ ትናንትና ብፁዕ ተብለዋል፣ የብፅዕናቸው ሥነ ሥርዓትም በአቺረያለ ቤተ ክርስትያን አደባባይ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛን ወክለው እዛ በተገኙ የቅዱሳን ጉዳይ የምትከታተል ማኅበር ኃላፊ በሆኑ በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ተፈጸመ፣ በሥርዓቱ የፓለርሞ ሊቀ ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትናው ዕለት በሎረቶ ባደረጉት ሐዋርያዊ ዑደት እላይ እንደተጠቀሰው በቦታው ተገኝተው የተቀበልዋቸው ምእመናን ከ10 ሺ በላይ እንደሚሆኑ እንዲሁም መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ጊዜም በተለያዩ የሎረቶ አደባባዮችና ጐዳናዎች ከ50 ሺ ሕዝብ በላይ በመገናኛ ብዙሓን እንደተሳተፉ ከቦታው የመጣ ዜና አመልክተዋል፣ ከከተማው ከንቲባ ፓውሎ ኒኮለቲ ጀምሮ የመንግሥት ...»

የዕለተ ሰንበት ንባባትና ስብከት 

RealAudioMP3 ዛሬ የምናነበው ወንጌል (ዮሐ 2፡1-14) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ሰዎቹ ወይን ባለቀባቸው ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ውሃውን ወደ መልካም የወይን ጠጅ በመለወጥ ስላደረገው የመጀመሪያ ተዓምርና ራሱን ለዓለም እንደገለጠ እንዲሁም ሐዋርያቱ እንዴት በእርሱ እንዳመኑ ይናገራል፣፡ ይህ ወንጌል የሚያስተላልፍልንን ትምህርት በአጭሩ እንመለከተዋለን፣፡
በመጀመሪያ ...»


መዝሙር ይሠርቅ ኮከብ. . . . ።
ንባባት፡ ዕብ 11፡8-19፥ 1ዮሕ. 4፡1-9፥ ግ.ሓ. 7፡17-23፥ ማቴ 2፡1-12።
ስብከት ወአነሂ በኲርየ እረስዮ። ወልዑል ውእቱ እም ነገስተ ምድር፥ ውለዓለም አዓቅብ ሣህልየ። መዝ. 89፡፡27~28።
የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


RealAudioMP3 የብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ደምረው
ሊቀ ጳጳስ ዘካቶሊካውያን ዘበኢትዮጵያ
የገና መልእክት፡

 ...»


መዝ፤ አቅዲሙ ነገረ በኦሪት
ንባብ፤ ሮሜ 13፡11-ፍጻሜ፤ 1ዮሓ 1፡1-ፍጻሜ፤ የሓዋ ሥራ 26፡12-19፤ ዮሐ 1፤1-19
ምስማክ፤ ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ፤ እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ፤ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ፣
በዛሬው ሰንበት ከሚነበበው ወንጌል ኃይለ ቃል አድርገን የምንወስደው «ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም ፤» የሚለውን ነው (ዮሐ፡ 1፡11)፡፡
RealAudioMP3
 ...»


መዝሙር፡ ዐርገ እምሃቤሆም አው ወረደ መንፈስ ቅዱስ. . . . . ።
ንባባት፡ ኤፌ 4፡1-7፥ 1ዮሓ 2፡1-8፥ ግ.ሓ. 8፡5-17፥ ዮሓ፡ 14፡15-31።
ስብከት፡ “ዐረገ ውስተ አርያም፥ ጸዌውከ ጼዋ ወወሃብከ ጸጋከ ለእጓለ እምሕያው፥ እስመ ይክሕዱ ከመ ይህድሩ” መዝ. 88፡18።
የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


መዝሙር፡ በሰንበት ዐረገ ሐመረ
ምስማክ፡ ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ “አምላክ በእልልታ፤ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ፤ ዘምሩ ለአምላክችን ዘምሩ” (መዝ 46፤5-6)
ንባባት፤ ሮሜ 10፤1 እስከ ፍጻሜ፤ 1ኛ ጴጥ 3፤15 እስከ ፍጻሜ፤ የሐዋ ሥራ 1፤1-12፤ ወንጌል፡ ሉቃስ 24፡45 እስከ ፍጻሜየአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3
 ...»

ፍጻሜዎች 

አስተማሪዎች ተማሪዎች የክልል መስተዳድር አባላት የተለያዩ የማሙያተኞች ማኅበራት የተሳተፉበት በጠቅላላ 200 ሰዎች የሰላም መልእክት ለማድረስ በሚል መርህ ሥር በኢጣሊያ ከፐሩጃ አሲዚ የሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ የሚያንጸባርቅ የሰላም የእግር ጉዞ በእስራኤልና በእስራኤል በተያይዙት የፍልስጥኤም ክልሎች መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ የሰላም የእግር ጉዞ የተለያዩ የሰብአዊ መብትና ክብር ተማጓች ...»


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን RealAudioMP3 የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ...»


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ብሔራው የማኅብራዊ ሳምንት ትኩረት በቤተሰብ ዙሪያ መሆኑ በኢጣሊያ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች የማኅበራዊ ሳምንት አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የካሊያሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አሪጎ ሚሊዮና የቶሪኖ RealAudioMP3 ሊቀ ጳጳስ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ...»


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ኵላዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት በዓል እንዳከበረች የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ ገብራኤል መልአክ የጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች በጠቅላላ የመገናኛ ብዙሃን ጠበቃ ቅዱስ በመሆኑ፣ እንደተለመደው በዚህ RealAudioMP3 ዓመታዊ በዓል ምክንያት በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው ብሥራተ ገብርኤል ጸሎት ቤት፣ ...»


በስዊዘርላንድ ሳን ጋሎ ሲካሄድ የሰነበተው የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምሉእ ጉባኤ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ የተካሄደው ጉባኤ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ሥነ ምግባራዊ ነክ ጥያቄዎች ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝርከ 50ኛው ዓመት የእምነት ዓመት፣ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ሲኖዶስ በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ትንተና የተከናወነበት መሆኑ ልኡክ ...»


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ