2018-06-26 16:00:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የካቶሊክ ሰነ-ትምህርት ለዓለም ስትንፋስ ይሰጣል” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የካቶሊክ ሰነ-ትምህርት ለዓለም ስትንፋስ ይሰጣል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን ቀደም ሲል ያነበባችሁትን የተናግሩት ማስተማር ማለት ሰውን ማሰልጠን ማለት ነው በሚል መሪ ቃል Gravissimum Educationis በተሰኘው ፋውንዴሽን አነሳሽነት በአሁኑ ወቅት በሮም ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባሄ ላይ በተጋባዥነት ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አንድ መንደር በመሆን ላይ ባለችው ዓለማችን የካቶሊክ ሰነ-ትምህርት ስትንፋስ በመስጠት የክርስቲያን የመዳን ተስፋን በስፊው ለዓለም ያስፋፋል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባድረጉት ንግግር በካቶሊክ የትምህርት ተቋማት መካከል ትስስር እንዲኖር እና ተባብረው ይሰሩ ዘንድ ማበረታቻ ይሆናቸው ዘንድ ቅዱስነታቸው ሦስት አስተያየቶችንም መሰጠታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ ውጤታማ የሆኑትን እያንዳንዱን የአዕምሮ እና የባህል ጠንካራ ነጥቦች ላይ በማተኮር ተቋማትን በማስተባበር፣ ተቋማትን በማስተዋወቅ እና በማስተሳሰር እንዲሰሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  ጥሪ ማቅረባቸው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን  መተባበር እና መቀናጀት ማለት የተለያዩ የትምህርት እና የጥናት ዘርፎችን በማስተሳሰር ለባህላዊ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ስፍራ ወይም ተገቢውን ቦታ በመስጠት ሁሉም የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች "ማህበረሰቡን ማነጽ" የሚያስቻልቸው ቁመና ላይ መድረስ ማለት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገልጸው በጨማሪም ተማሪዎች እና አስተማሪዎች በተቀናጀ መልኩ የሕይወት ልምዳቸውን እና ተመክሮዎቻችወን ሳይቀር ቅን በሆነ መንገድ መስጠት እና መቀበልን ያካትታል ማለታቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

በአሁኑ ወቅት ሰብዓዊ ማኅበረሰብ እያጋጠመው የሚገኘውን ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን  አስመልክተው የተናገሩት ቅዱስነታቸው የካቶሊክ ሰነ-ትምህርት "የሰው ልጅ የሥነ ምግባር ግዴታ ዛሬ በሚከሰቱ ነባራዊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስት ቢቻ ሊመዘን የሚገባው ነገር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚታይ እና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የምናደርጋቸው ማንኛውም ዓይነት ምርጫዎች በወደፊቱ ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስላላቸው" የካቶሊክ ሰነ-ትምህርት ይህንን ሁኔታ ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ቀጣይነት ባለው መልኩ ሊሰጥ ይገባዋል” ብለዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማስተማር ማለት ሰውን ማሰልጠን ማለት ነው በሚል መሪ ቃል Gravissimum Educationis በተሰኘው ፋውንዴሽን አነሳሽነት በአሁኑ ወቅት በሮም ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባሄ ተሳታፊ ለሆኑ ሰዎች ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት የማኅበረሰብ አባላት አሁን በከፍተኛ ደረጃ በዓለማችን በመታየት ላይ ያለውን ማኅበራዊ ለውጦችን በንቃት እንዲከተታል እና በማስተማር ሂደት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥር ማቅረባቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ግቡም ሁሉም የሰው ልጆች "የክርስቲያን መዳን ከተስፋ ቃል ጋር በማነፃፀር ራሳቸውን እንዲጠብቁ" ማስቻል ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በእዚህ ረገድ መምህራን ተስፋ መቁረጥ እንደ ሌለባቸው የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናን በዛሬው ዓለም ውስጥ የተስፋን ዘር መዝራት ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስነታቸው “አሁን ያለንበት አንድ መነደር በመሆን ላይ ባለው ዓለማችን እያመጣ ያለውን ጎጂ የሆኑ አስተሳሰቦችን በመዋጋት መልካም የሆኑ ነገሮችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ለመልካም ነገሮች ድጋፍ የሚያደርግ የአዕምሯዊና ስነ-ምግባራዊ እሴቶችን በቀጣይነት በመገንባት ለዓለም እስትንፋስ ልንሆን ይገባል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማስተማር ማለት ሰውን ማሰልጠን ማለት ነው በሚል መሪ ቃል Gravissimum Educationis በተሰኘው ፋውንዴሽን አነሳሽነት በአሁኑ ወቅት በሮም ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባሄ ተሳታፊ ለሆኑ ሰዎች ቅዱስነታቸው ይህ ማኅበር ውጤታማ በሆነ መልኩ በዓለም ውስጥ እያበረከተ የሚገኘውን አስተዋጾ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችለውን በሦስተኛውን እና የመጨረሻውን እርሳቸው አስፈላጊ እና ወቅታዊ ነው በማለት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት መስጫ ማዕከላት ውስጥ ሊተገበሩ ይገባል ያሉት ወሳኝ ባሕርይ ማንነትን ለይቶ ማወቅ፣ የትምህርት ጥራትና ለጋራ ጥቅሞች ጥንቃቄ ማድረግ የሚሉት እንደ ሆኑ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ባለው መልኩ፣ በመሰረታዊ ተልዕኳቸውን እና በቤተክርስቲያኗ የወንጌል ተልዕኮ መካከል ያለውን ግንኙነት በማስከበር ቀጣይነት በሆነ መልኩ የሕነጻ ትምህርቶችን ሊሰጡ እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግም በትምህርት አሰጣጥ ላይ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት መሰጥ እና የጋራ የሆኑ እሴቶችን መጠበቅ ላይ ባተኮረ መልኩ መደረግ እንደ ሚገባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም መምህራን “እኛ ሁላችን የአንድ ቤተሰብ አባል” መሆናችንን እንድንረዳ በማድረግ ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማስተማር ማለት ሰውን ማሰልጠን ማለት ነው በሚል መሪ ቃል Gravissimum Educationis በተሰኘው ፋውንዴሽን አነሳሽነት በአሁኑ ወቅት በሮም ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባሄ ተሳታፊዎች እንደ ገለጹት “ተልእኳችሁን በሚገባ ለመወጣት ያስችላችሁ ዘንድ ከክርስቲያናዊ ማንነታችን ጋር በሚስማማ መንገድ መሠረት መጣል እንደ ሚገባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ለትምህርት እና ለምርምር ጥራት ተስማሚ እና አግባብ ያላቸውን መስረቶች በመጣል ግባችሁን ለጋራ አገልግሎት በሚውሉ ተግባራት ላይ በማተኮር ሕብረትን የሚፈጥሩ ተግባራትን ማከናወን ይገባል ካሉ በኃላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

ይህ Gravissimum Educationis በመባል የሚታወቀው  ማኅበር እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 28/2015 ዓ.ም ላይ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ባጸደቀው Gravissimus Educationis ሰንድ 50ኛው ዓመት እዩቤሊዩ በተከበረበት ወቅት የካቶሊክ ትምህርት አሰጣጥ የተሰኘው ማኅበር ባቀረበው ጥያቄ መስረት የተቋቋመ ፋውንዴሽን እንደ ሆነም ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመልክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.