2018-06-06 14:14:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ፥ “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዱ አገልጋይ ሌላው ደግሞ ተገልጋይ ሆኖ ሊኖር አይገባም”።


ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ፥ “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዱ አገልጋይ ሌላው ደግሞ ተገልጋይ ሆኖ ሊኖር አይገባም”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህ መሰረት በግንቦት 15/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ምስጢረ ሜሮን የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስን የምቀበልበት ምስጢር ነውማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

በግንቦት 22/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ባለፈው ሳምንት  ከጀመሩት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ክርስቶስን በሚገባ መቀበል እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባን ልንፈቅድለት ይገባል” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 29/2010 ዓ.ም አሁንም በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ ላይ ባደረጉት የክፍል ሦስት አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያን እንድትስፋፋ የሚረዳት ምስጢረ ሜሮን ነው ማለታቸውን ለመራዳት ተችሉዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

“በዚያኑ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ አላቸው” (ዩሐንስ 20፡19.22)።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 29/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በምስጢረ ሜሮን ዙሪያ የጀመርነውን አስተምህሮ በመቀጠል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ምስጢረ ሜሮን በተቀበሉ ክርስቲያኖች ላይ የሚያደርገውን አዎንታዊ ተጽዕኖ በምንመለክትበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ክርስቲያኖች ነብሳቸውን ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ ያነሳሳቸዋል። መንፈስ ቅዱስ ራሴን ወይም እኔን ብቻ መኣከል ካደረገ የሕይወት ልምድ በመውጣት ለእኛ ወይም በአጠቃላይ ለክርስቲያን ማኅበርሰብ ራሳችንን በመክፈት ለምንኖርበት ማኅበርሰብ መልካምነት ሕይወታችን እንድናውል ያደርገናል።

በምስጢረ ጥምቀት ክርስቶስን መምሰላችንን በማስታወስ በምስጢረ ሜሮን ደግሞ ከእዚያ ባለፈ እና ጠንከር ባለ ሁኔታ ሕያው እና ምስጢራዊ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን አካል እንድንሆን ያደርገናል። ቤተክርስቲያን በዓለም ውስጥ ያላት ተልዕኮ የሁሉንም አካል አስተዋጽ ይፈልጋል። በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን በምናውቃቸው አብረውን በሚጓዙ ሰዎች የተዋቀረች ሕይወት ያላት ፍጥረት አድርገን ልናስባት የገባል እንጂ እንዲያው ረቂቅ እና በሩቅ ያለ እውነታ አድርገን ልናስብ አይገባንም። ምስጢረ ሜሮን ዓለማቀፍ የሆነችሁ እና በመላው ዓለም የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን መንገድ በመሆን፣ ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በተለይም በእየራሳቸው አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሐዋሪያት ተተኪ ከሆኑ ጳጳሳት ጋር በጋራ በመሆን በንቃት  እንድንሳተፉ ያደርጋል።

ምስጢረ ሜሮን በጳጳስ ብቻ የሚሰጥ ምስጢር ነው። የእዚህ ምስጢር በእነርሱ መፈጸም በግልጽ እንደ ሚያሳየው ውጤቱን የሚቀበሉትን ከቤተ ክርቲያን ጋር ይበልጥ ለማቀራረብ፣ ከሐዋሪያት ጋር ለማቆራኘትና ክርስቶስን ከመመስከር ተልዕኮ ጋር የጠበቀ አንድነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታስቦ ነው (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ . 1313)

በእዚህ መልኩ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቀላቀላቸው ደግሞ በእዚህ ምስጢር የቅባ ቅዱስ አቀባብ ስነ-ስረዓት ላይ ባለው ሰላምታ በመለዋወጥ ስነ-ስረዓት ይጠቃለላል። በእርግጥ ጳጳሱ በወቅቱ ምስጢረ ሜሮንን ለተቀበሉ ክርስቲያኖችሰላም ከአንተ ጋር ይሁንበማለት የሰላምታ ቃል ያቀርባል። እነዚህ ቃላት በፋስካ  ምሽት ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሰላምታ ያቀረበበትን የጌታን ሰላምታ በማስታወስ በመንፈስ ቅዱስ መሞላታቸውን የሚያንጸባርቁ ቃላት ሲሆኑየምስጢረ ሜሮን አሰጣጥ ስነ-ስረዓት የሚደመደመው የሰላም ምልክት በመለዋወጥ ሲሆን ጳጳሱ ከመላው ምዕመናን ጋር ያለውን ቤተ ክርስቲያናዊ ሱታፌ የሚያመልክት እና የሚገልጽ ነው። (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምሕርተ ክርስቶስ . 1301) ከጳጳሱ የሰላምታ ቃል መቀበል ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን እና ከቤተ ክርስቲያን ውጪ መንፈሳዊ በሆነ በጋለ ስሜት ሕብረት እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። ሰላምን መቀበል በቁምስና ውስጥ መግባባትን ለመፍጠር እና ሰላማዊ ግንኙነቶችን ለማሻሻል፣ ከሌሎች ጋር መግባባት እንዲፈጠር ያደርጋል። ሰላምን መቀበል ከእኛ በሐሳብ ልዩ የሆኑ ሰዎችን ሳይቀር እንድንቀበል እንዲሁም የክርስቲያን ማኅበርሰብ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች መኖራቸው በራሱ ጸጋ መሆኑን በመቀበል በሰላም እንድንኖር ያደርገናል።

መንፈስ ቅዱስ አዲስ ነገር ይፈጥራል እንጂ የተሰራውን መልሶ የሚደግም አይደለም። የእርሱ ስጦታዎች ልብ-ወለድ እና ምትሃታዊ አይደሉም! የእርሱ ሥራ የእርሱን ማኅተም ያርፈባቸውን ሰዎች ሁሉ ያካትታል። ምስጢረ ሜሮንን የምንቀበል አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ነገር ግን ከእርሱ ቅባ ቅዱስ የተቀበልነው ጸጋ በዘመናት ውስጥ በብርታት እንድንጓዝ ያደርገናል። መልካም የሆነውን የቅድስና ሕይወት መዐዛን በምንሄድበት ሥፍራዎች ሁሉ ከማዳረስ አንቆጠብም። የቅዱስ ወንጌል እሴቶች እንደ ሚያሳስቡንህይወታችንን ልንኖር የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታግዘን ከራስ ወዳድነት፣ ከስንፋና፣ ከኩራት . . . እነዚህን እና እነዚህን ከመሳሰሉ ደካማ ነገሮች ለመላቀቅ ያስቸልናል።

ማንም ሰው ምስጢረ ሜሮንን ለራሱ አገልግልት ብቻ ለማዋል አልተቀበለውም፣ ነገር ግን ለሌሎች ሰዎች መንፈሳዊ እድገት ጭምር ልንጠቀምበት ነው የተሰጠን። በዚህ መንገድ ብቻ ነው እራሳችንን በመክፈትና ከወንድሞቻችን ጋር በመገናኘት ከእራሳችን በመውጣ፣ እኛ ከልባችን እራሳችንን ለሌሎች አገልግሎት ማዋል እንችላለን። ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታ ስንቀበል እኛም በብኩላችን ይህን ስጦታ ፍሬያም እዲሆን የማድረግ ኃላፊነት አለብን። ከፍርሃት እና ከስሌት በመነጨ ሁኔታ ሽባ ሆነን እንዳንቀር፣ ደኽንነት በሚሰማን መንገድ ላይ ብቻ እንዳንራመድ ወደ ፊት የሚገፋን መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ማስታወስ ይኖርብናል። ታሽጎ የተቀመጠ ነገር ሁሉ ስለሚታፈን ሽታን ያመጣል ከእዚያም እንድንታመም እንደ ሚያደርገን በፍጹም መዘንጋት የለብንም። ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን አፍነው እናዳያስቀምጡ አደራ እላችኃለሁ፣ ወደ ነጻነት መነገድ እንድንጓዝ የሚያደርገንን የመንፈስ ቅዱስ ነፋስ ማገድ አይኖርብንም፣ ሕይወታችንን ለወንድሞቻን እና ለእግዚኣብሔር አገልግሎት እንድናውል የሚያደርገንን የፍቅርን የእሳት ነበልባል ማዳፈን አይኖርብንም። መነፍስ ቅዱስ ለሁላችን ሐዋሪያዊ ብርታትን በመስጠት በመንገዳችን ላይ ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን በተግባር እና በቃል  ለማሰራጨት መንፈስ ቅዱስ ሁላችንንም ይራዳን

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.