2018-01-29 08:28:00

ር.ሊ.ጳ ፍድራንችስኮስ የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማህበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልእክት


ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍድራንችስኮስ፣ ትናንት ጥር 18 ቀን 2010 ዓ. ም. ላለፉት ቀናት በስብሰባ ላይ የቆዩትን የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማህበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ የተሳተፉትን አባላትን በሙሉ አመስግነው፣ በእምነት ጎዳና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንስተው በመወያየታችሁ ልባዊ ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አሰምተዋል።

የእዚህን መልእክት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመት ትችላላችሁ

 

ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ፣ በቅድስት መንበር የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ማህበራት ጉባኤ በኩል፣ ለእምነት ወንድሞች፣ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን፣ ለጳጳሳት ጉባኤ፣ የእምነት አካሄድንና እና የምስጢራት ቅድስና በማብራራት ለምታከናወኑት ዕለታዊ አገልግሎት ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ዛሬ በእምነት መንገድ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለመመልስ የሚያግዙ መልሶችን በማፈላለግ፣ የሰው ልጅ ከሚወድቅበት ከባድ ሃጢአት ምሕረትን የሚያገኝበትን መንገድ፣ ለጋብቻ ሕይወት የሚሰጠውን ክብርና የሚደረግለትን ድጋፍ በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ስታደርጉ ቆይታችኋል።

ለበርካታ ጥያቄዎች የሰው ልጅ መንፈሳዊ ድጋፍ ሳይታከልበት ብቻውን መመለስ አይችልም። ጥረት ቢያደርግም አዳዲስ ጥያቄዎችን የሚያስከትልና ስለ ስነ ህይወት እና ስነ ምግባር ምርጫዎች ውስጥ ይገባል። የዛሬ ሰው ማንነቱን በሚገባ ስለማያውቅ በምን መልኩ መመለስ እንዳለበት ይቸገራል። በዚህ የተነሳ አገልግሎታችሁ የሰው ልጅ ድንቅ የሆነውን መለኮታዊ ጥሪውና ከእውነት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለውን ምክንያታዊ ግንኙነት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት የሚያሳየን መንገድ ነው። የሰው ልጅ እግዚአብሔር ብቻ በሚሰጠው ብርሃን በመታገዝ ራሱንና፣  እግዚአብሔር ለዓለም ያለውን ግሩም ዕቅድ ማወቅ ይችላል።  

የክርስቲያን ሕይወት ከዘለዓለማዊ ሞት የሚድንበትንና ሌሎችንም ለምሳሌ የመዳንን ትርጉም ለማስረዳት ብላችሁ ለምታሰርጉት ጥናት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

አንዳንድ የዘመናችን ርዕዮተ ዕለም ወይም አስተሳሰቦች የሰው ልጅ የመዳንን ትርጉም በራሱ ሃይል አጥንቶ ወይም ፈልጎ ለመድረስ የሚያደርገውን ጥረት ያመለክታሉ። እኛ ግን መዳንን የምናገኘው ከሞት በተነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ ለዚህም እኛን ከአባቱ እና ከሰዎች ጋር እንድንገናኝ ያደረገንን መንፈስ ቅዱስን እናመሰግናለን። አባት ከልጆቹ ጋር እንደተዋሄደ ሁሉ፣ እኛ ሁላችን ከልጁ ከኢየሱስ ጋር አንድ አካል እንድንሆን አዘጋጅቶናል። ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ 8 ቁጥር 29.

በስፋት ከያዛችሁት ጥናት ጋር ደግሞ በኢኮኖሚና ፋይናንስ መስክ ያለውን ስነ ምግባር መርሳት የለብንም። ይህም የሰውን ልጅ ከሚመለከተው አንድ ክፍል ብቻ በመውሰድ በሞራላዊ አካሄድ ይህን እንዴት እንደሚመልስ መመልከት ነው።  የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁል ጊዜ በግልጽ እንደሚናገሩት ኤኮኖሚንና ፋይናንስ እንቅስቃሴዎች የኤኮኖሚ ዘዴዎችን፣ ሕጎችንና ግብረ ገብን የተከተሉ መሆን እንዳለባቸው ያስረዳሉ። 

በእነዚህ ጊዜያት በጥልቀት የተመለከታችሁት ሌላው ርዕስ፣ በሞት አፋፍ ላይ ያሉትን ነፍሳት ወደ ዘለዓለማዊ ዕረፍት መሸኘትን የተመለከተ ነው። ይህን በተመለከተ ዓለማዊ መሆን ወይም ፍጹም መሆን ጉዳዩን በግል የመወሰን መብት እያላበሰው በብዙ አገሮች ዘንድ የሰው ልጅ በሕይወቱ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው የሚያስረዳ ርዕዮተ ዕለም በመስፋፋት ላይ ይገኛል። ይህን በውዴታ የሚደረግ ሕይወትን የማጥፋት ምርጫን የስልጣኔ ክፍል አድረገው በመውሰድ ያከናውኑታል።

እርግጥ ነው ሕይወት የሚገባውን ክብር ካጣና  በውጤታማነት እና በምርታማነ ብቻ የተመለከት ከሆነ በሕይወት ላይ ሁሉን ነገር ማከናወን ይቻላል። በዚህ አጋጣሚ የሰው ልጅ ሕይወት ከተወለደበት ዕለት አንስቶ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የማይገረሰስ ክብር ያለው ነው።

በሰው ልጅ ሕይወት የሚደርሱ ሕመሞች፣ ስቃዮች፣ የሕይወት ትርጉሞችና በመጨረሻም ሞትም፣ የጊዜአችን ሰው በሙሉ ተስፋ መመልከትና መቀበል ያለበት ነው። በሕይወቱ የሚያጋጥመውን ሕመምና ሞትም ቢሆን ለመቀበል የሚያስችለውን ተስፋ ካልያዘ በቀር ሰው የወደ ፊት ሕይወቱን በመልካም ሁኔታ ለመኖር ይቸገራል። ይህን ለዘመናችን ሰው በሚገባው ማስረዳት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ አደራና አገልግሎት ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚያተኩረው የሰው ልጅ የራሱን ክብር ሳይረዳ ሲቀር፣ የሕይወቱ መጨረሻ ግቡን ሲዘነጋ፣ በእምነት የእግዚአብሔርን አባታዊ ፍቅር መመስከርና ስብዕናን የተላበሰ መልካም መንገድ ማበጀት ነው። ይህን በሚገባ ማከናወን ለእናንተ እና ለሌሎች የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተቋማት የተሰጠ ሃላፊነት ነው።

ለአገልግሎታችሁ ከፍተኛ ትኩረትን እንደምትሰጡ ተስፋን በማድረግ፣ ከጎናችሁ መሆኔን እያረጋገጥኩላችሁ ሐዋርያዊ ቡራኬዬን እልክላችኋለሁ በማለት መልዕክታቸውን አጠቃልለዋል።         

 








All the contents on this site are copyrighted ©.