2018-01-11 15:56:00

በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ከሚደረገው የመግቢያ ጸሎት በፊት ያለው የጸጥታ ጊዜ ሐሳባችንን በአንድነት ወደ እግ/ር ለማቅረብ ይረዳል


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። ከእዚህ ቀደም ማለፈው ሳምንት ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ጀምረውት የነበረው የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በመስዋዕተ ቅዳሴ በመግቢያ ሥነ-ስርዓት ውስጥ የሚገኘውን “የኑዛዜ ጸሎት”  በተመለከት ጥልቅ የሆነ አስተምህሮ አድርገው እንደ ነበረ መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ይህም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስርዓት ውስጥ የሚገኘው የኑዛዜ ጸሎት በራሱ ቅዱስ በመሆኑ የተነሳ እኛም ይህንን ቅዱስ የሆነ ምስጢር ተገቢ በሆነ መልኩ ለመካፈል እንችል ዘንድ በእግዚአብሔርና በወንድሞቻችን ላይ የፈጸምነውን ኃጢአቶች በሚገባ ማስተዋል እንችል ዘንድ ይረዳናል ማለታቸው ይታወሳል። የጥር 2/2010 ዓ.ም. የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዋቸው ትኩረቱን ያደርገው በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስርዓት ላይ ካለው የኑዛዜ ጸሎት በመቀጠል በሚገኘው “ክብር ለአምላክ” በሚለው የወዳሴ መዝሙር እና “የመግቢያ” ጸሎት ላይ ያጠነጠነ ነበር። 

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ባለፈው ሳምንት በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ባደረግነው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመስዋዕተ ቃዳሴ ወቅት የሚባለውየኑዛዜ ጸሎትስለ ራሳችን ያለንን እውነታ እንድንገነዘብ በማድረግ፣ ትክክለኛ ማንነታችንን ተገንዝበን፣ ኃጢአተኞች መሆናችንንም ተቀብለን፣ ይቅርታን እንደ ሚደረግልን ተስፋ በማድረግ ራሳችንን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ እንደ ሚረዳን መግለጻችን ያታወሳል።

በሠው ልጅ መከራና በመለኮታዊ ምሕረት መካከል ግንኙነት በሚፈጠርበት ወቅት በምስጋና የተሞላ "ክብር" ይገለጻል።በጣም ጥናትዊ በሆነ ደማቅ ወዳሴ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት  ለእግዚኣብሔር እና ለበጉ የክብር መዝሙር እና ውዳሴ ታቀርባለች

ይህ የውዳሴ እና የክብር መዝሙር የሚጀምረውበሰማያት ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይሁንየሚለው ኢየሱስ በቤተልሔም በተወለደበት ወቅት ሰማይ እና ምድር በተገናኙበት ወቅት መልአክት ባሰሙት ውዳሴ ወቅትም የተዘመረ ውዳሴ ነው።በሰማያት ለእግዚኣቤር ምስጋና፣ በምድርም በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ሰላም ይሁን!” በማለት እኛም በዚህ የወዳሴ ጸሎት ውስጥ እንሳተፋለን።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅትክብር ለአምላክካልን ቡኃላ ወይም ደግሞ ይህክብር ለአምላክየማይባል ጸሎት የማይባል ከሆነ ከእዚያው በመቀጠል ከሚገኘውከኑዛዜ ጸሎትበመቀጠል በተለየ ሁኔታ የተዘጋጀየመግቢያ ጸሎትበሚል አርእስት የቀረበ በአመት ውስጥ በሚገኙትን የተለያዩ የስርዓተ አምልኮ ወቅቶችን ከግንዛቤ ያስገባ ጸሎት ይደረጋል።

ካህኑ "እንጸልይ" በሚለው የግብዣ ጥሪ አማካይነት ሕዝቡ በጸጥታ በተሞላ መንገድ ሐሳባቸውን እንዲሰበስቡ አጥብቆ በማሳሰቡ፣ በመጨረሻም ሕዝቡ እግዚኣብሔር በእዚያ ቦታ እንደ ሚገኝ ልብ እንዲሉ በማድረግ እና ይህንንም ሐሳብ በሕዝቡ ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ፣ ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ የሚሳተፉ ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴውን በእዚሁ ሐሳብ ተሞልተው እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል። ካህኑእንጸልይይላል፣ ይህንንም ተከትሎ ጸጥታ ይሰፍናል፣ በእዚህ ጊዜ እያንዳንዱ ምዕመን በጸሎት ሊጠይቀው ወይም ሊማጸነው የፈለገውን ነገር ያሰላስላል።

ጸጥታ ማለት የቃላት አለምኖር ማለት አደለም፣ ነገር ግን ሌሎች ድምጾችን ማለትም የልባችንን ድምጽ በተለይም ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ  ለማዳመጥ ዝግጁ መሆን ማለት እንጂ። በስረዓተ አምልኮ ውስጥ ያለው ጸጥታ ባህሪው የሚወሰነው በሚከሰትበት ሁኔታ እና ቦታ ላይ ነው፣ ለምሳሌምበኑዛዜ ጸሎት ወቅት እና ካህኑ እንጸልይ ካለ ቡኃላ ያሉት የጸጥታ ጊዜያት ነገሮችን እንድናስታውስ ይረዳናል፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ቡኃላ ወይም ደግሞ ከስብከት ቡኃላ ያለው የጸጥታ ጊዜ በሰማናቸው ቃላት ላይ በአጭሩ እንድናሰላስል የሚረዳን የጸጥታ ጊዜ ነው። ከቅዱስ ቁራባን ቡኃላ ያልው የጸጥታ ጊዜ ደግሞ በውስጣችን የውዳሴ ቃል፣ ምስጋና እና ምልጃን እንድናደርግ የሚረዳን የጸጥታ ጊዜ ነው ስለዚህ ከመግቢያ ጸሎት በፊት ያለው የዝምታ ጊዜ እኛ ለምን በእዚያ ቦታ እንደ ተሰበሰብን እንድናስብ ያደርጋል። በዚህ ጊዜ ልባችንን  በማዳመጥ ከዚያም ለጌታ ልባችንን ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል።

ምናልባትም በሥራ ደክመን፣ ወይም ደግሞ ከደስታ እና ከሀዘንን ስፍራዎች መጥተን ይሆን ይሆናል፣ እኛም ጌታን መለመን እና የእርሱን እርዳታ መጠየቅ ይኖርብናል። የታመሙ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞች ይኖሩን ይሆናል ወይም ከባድ መከራዎች ያጋጥሙናል። እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን እና ለዓለም ዕጣ ፈንታው መልስ ይሰጥ ዘንድ በአክብሮት በአደራ ለእርሱ እንሰጣለን። እናም ይህ ካህኑ የመግቢያ ጸሎት ከማድረጉ  በፊት የሚገኘው አጠር ያለ የዝምታ ጊዜ እነዚህን ነገሮች እንድናስብ የሚያደርገ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ፍላጎት በማሰላሰል፣ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር በመግለፅ፣ የሚደረገው የመግቢያ ጸሎት በእዚያ ስፍራ የሚገኙ የግለሰቦችን የጋራ የጸሎት ሐሳብ በአንድ ላይ በማሰባሰብ ጠቅለል ባለ ሁኔታ በእነዚህ ሐሳቦች ላይ ተመርኩዞ የሚደረግ የመጊቢያ ጸሎት ነው። በእዚህ አጋጣሚ ካህናት በቀጥታ ወደመግቢያው ጸሎትከመሄድ ይልቅ ከእዚህ ጸሎት በፊት ያለውን የጸጥታ ጊዜ እንዲያከብሩ ማሳሰብ እወዳለሁ። ያለዚህ የጸጥታ ጊዜ የምዕመናኑን ሐሳብ በአንድ ላይ መሰብሰብ ያዳግታል።

ካህኑ ይህንን የመግቢያ ጸሎት እጆቹን ዘርግቶ በሚጸልይበት ወቅት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያኖች በጸሎታቸው ወቅት እንደ ሚያደርጉት ዓይነት፣ እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እጆቹን ዘርግቶ እንደ ነበር የሚገልጽ ተምሳሌት በመላበስ ካህኑየመግቢያ ጸሎትበሚያደርግበት ወቅት እጆቹን ወደ አድማስ ይዘረጋል። በእዚያን ወቅት ክርስቶስ በዚያ ጸሎት ውስጥ ይኖራል። ካህኑ የሚያቀርበው እግዚኣብሔርን ደስ የሚያሰኘውን መስዋዕት ኢየሱስ እስከ መጨረሻው ድረስ ታዛዥ በመሆን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበትን  የስቅለት ቀን  መታሰቢያ መሆኑን እናውቃለን።

በላቲን የስርዓተ አምልኮ ወቅት የሚደረጉት ጸሎቶች ይዘታቸው በጣም አጭር ቢመስልም ነገር ግን ብዙ ጥልቅ የሆነ ጥርጉም ያዘሉ ናቸው፣ በጣም ውብ የሆኑ አስተንትኖዎችን ልናደርግባቸውም እንችላለን። በጣም ወብ ናቸው። ወደ መጽሐፍ ቅዱሳችን ስንመለስ ከመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውጭም ቢሆን እንኳን በእግዚኣብሔር ቃል ላይ ማሰላሰል ወደ እግዚአብሔር እንዴት መመልስ እንደ ሚገባን፣ ምን መጠየቅ እንዳለብን፣ ምን ዓይነት ቃላትን መጠቀም እንዳለብን እንድናውቅ ይረዳናል። በዚህም ይህ መስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ለሁላችን ትክክለኛውን የጸሎት መንፈስ የምንማርበት ትህምርት ቤታችን ይሆናል ማለት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 2/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ መስዋዕተ ቅዳሴን በተመለከተ ካደርጉት አስተምህሮ ተወስዶ የተተረጎመ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.