2017-08-07 15:05:00

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ ከድኾች ጋር ስንገናኝ ከእኛ ጋር ሊገናኝ ከሚመጣው ክርስቶስ ጋር እንገናኛለን


ሌላው ከእኔ የተለየውን በአክብሮት ማስተናገድና መቀበል በእርሱ ውስጥ ያለው በተለይ ድግሞ ድኻና ጎስቋላ በቀላሉ ለአደጋ የተጋለጠ ከሆነ በእርሱ ውስጥ እኔን ለማግኘት የሚመጣው ክርስቶስን ነው የማስተናግደው የሚል በድኻውና በጎስቋላው በተጨቆነው ውስጥ የሚገለጠውን ክርስቶስ መቀበል ለአንድ ክርስቲያን ትልቅ ክብር መሆኑ የሚያብራራ ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ መረብት ባለው @Pontifex በተሰየመው አድራሻቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኤማኑኤላ ካምፓኒለ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው በዚህ የትዊተር መልእክታቸው አማካኝነት ለሚሰቃየው ለድኻው ለተናቀውና በተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር አማካኝነት ተነጥሎ ለሚኖረው ያላቸው ጥልቅ ቅርበት ይመሰክራሉ። ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ክልል የማይል ክርስትና እምነት ሊሆን አይችል ወይንም ክርስቶስን የሚከተል ነው ብሎ ለመናገር እንደማይቻልም በማመላከት ማኅበረ ክርስቲያንና ቤተ ክርስቲያንን ክርስቶስ በመምሰል ሂደት እንዲያድጉ ይመክራሉ።

ባለ እንጀራና ጎረቤት የሚለው ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ ስለ ሚገልጠው ቃል፡ እንደ ገዛ እራስህ አፍቅር የሚለው ምዕዳኑን እንዲስተዋል የሚያመላክት ነው፡ ይኽ ክርስቶሳዊ ጥሪ ቅዱስ አባታችን የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማእከል እንዲሆንና በሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር መተርጎም የሚገባው ክርስቶስ ለእኛ ያለው ቅርበት ማረጋገጫ መሆኑ ያስተምራሉ። ካለ ማቋረጥም ዘወትር አደራ የሚሉት ሥልጣናዊ ምዕዳንም መሆኑ ካምፓኒለ ያስታውሳሉ።

ሌላውን ምንም የሌለውን ነጥሎ እንደ ቆሻሻ ተመልክት የሚለው ሰው በመሆኑ ሳይሆን በሚኖረው ሃብት መከበር አለበት የሚለውን ባህል ሌላውን በመቀበል በቃልና በተግባር መዋጋት እንዳለብን፡ ሌላው ክእኔ ጋር ለመገናኘት የሚመጣ ክርስቶስ ነው ይኸንን በስብከታቸው በሥልጣናዊ ትምህርታቸው በሚፍጽሟቸው ዓለም አቀፍም ይሁን ብሔራው ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ካለ መታከት የሚያሰምሩበት ክርስቶሳዊ ሃሳብ ነው። እ.ኤ.አ. ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አዳራሽ፥ ከሰባት ሺሕ በላይ የሚገመቱ ከውጭና ከውስጥ የመጡት ምእመናን የኢጣሊያ ህሙናንና ጉዳተኞች ወደ ቅዱሳት ሥፍራዎች መንፈሳዊ ንግደት የሚሸኝ ማኅበር 110ኛ ዓመተ ምሥረታ ምክንያት ተቀብለው፥ ግብረ ሠናይ ወንጌላዊ ተግባር ነው በማለት በተለያየ የግብረ ሠናይ አገልግሎት የተሰማሩት የበጎ ፈቃድ አባላት በዓለም በሚታየው ስቃይና መከራ በሚሰቃየው ሰው ሁሉ ፊት ያንን በኢየሱስ የተገለጠው እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር መስካሪያን ሁኑ፡ ድኻው የሚሰቃየው የክርስቶስ አካል ነው” ብለው እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካምፓኒለ ባጠናቀሩት ዘገባ  በማስታወስ ጠቅሰዉታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.