2017-05-26 17:09:00

ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ፥ ቤተሰብ ወጣት ትውልድ ሥራ የአንድ ኅብረተሰብ መሠረት ናቸው


“የወጣቶች ግኑኝነት በእምነት” በሚል ዋና ርእሰ ጉዳይ የተመራው እንዲሁም እ.ኤ.አ. በኢጣሊያ ካሊያሪ ከተማ እ,ኤ,አ, ከጥቅምት 26 ቀን እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ሊካሄድ የተወሰነው የኢጣሊያ ብሔራዊ የማኅበራዊ ሳምንት የማሰናጃ ርእስ በማድረግና በማስከተልም በኢጣሊያ የቤተ ክርስቲያን ኣቢያተ ፍርድ ቤተ ክርስቲያናዊ ሕገ መስተዳድር፤ ወጣቶች፤ ሥራ እንዲሁም አስፍሆተ ወንጌል የተሰኙት ነጥቦች አማክሎ እ.ኤ.አ. ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ቃለ ምዕዳን በይፋ ተጀመሮ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ጉባኤው የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ሆነው ላለፉት ዓስር ዓመታት ላገለገሉት የተልእኮ ዘመናቸው ላጠናቀቁት የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካዲናል አንጀሎ ባኛስኮን የሚተካ አካል ለመምረጥ ሦስት ስሞችን በመጠቆምና ካቀረበ በኋላም ቅዱስነታቸው ከቀረቡቸው ሦስት ዕጩዎች እነርሱም የፐሩጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጉዋልቲየሮ ባሰቲ፡ የኖቫራ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ፍራንቸስኮ ጁሊዮ ብራምቢላና የአግሪጀንቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንቸስኮ ሞንተነግሮን ውስጥ የፐሩጃን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ የምክር ቤቱ በሊቀ መንበር እንዲሆኑ መሾማቸው ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አያይዘው የተካሄደው ይፋዊ ጉባኤው አክሎ የኢጣሊያ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ሁነት ተንትነው ኢጣሊያ አጋጥሟት ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ተላቃ የሥራ እድል ለዜጎች መፍጠር የሚያስችል ብሎም የድኾች የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል የሚያግዝ የኤኮኖሚ እቅድ የማቅረብ የመንግሥት ኃላፊነቶች ለይቶ መወያይቱንም ገልጠው፥  ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ እ.ኤ.አ. ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንጻ ተገኝተው ቀዳሚ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውንም አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር እንዲሆኑ በቅዱስነታቸው የተሾሙት ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ ከምርጫው በኋላ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት መግለጫ፥

ለቤተሰብ ጥበቃና ድጋፍ የሥራ ዕድል የመሳሰሉት ማኅበራዊና ሰብአዊ ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጥባቸው የሚገባ ርእሶች ናቸው በማለት ኢጣሊያ የተነከረችበት ከኤኮኖሚው ቀውስ ጠቅሰው፥ ብዙውን ጊዜ የፖለቲካውን አለም ቀርቤ እታዘባለሁ፥ ያለው ክፍፍል የሚያሳዝን ሁሉም ነገር ጭፍን ያለና የጋራውን ጥቅም ሲስተዋል አላይም። ቤተሰብ ወጣት ሥራ የማንኛውም ኅብረተሰብ ምሰሦዎች ናቸው፡ ስለዚህ በፖለቲካው በማኅበራዊውና በኤኮኖሚው ዓለም ሊማከሉ ይገባል”

ከሁሉም በላይ ወጣቱ ትውልድ ሰብአዊ ክብሩ ወደ ማጣት እያዘገመ ነው። ምክንያቱም ሥራ ለሰው ልጅ ክብር ነው፡ የሥራ ዕድል ካልተፈጠረ የወጣት ትውልድ መጻኢ አሳሳቢ ይሆናል።የፖለቲካው ዓለም ይኸንን ግምት ሰጥቶ ተገቢ መልስ ለመስጠት የሚያስችል እቅድ ሊያፋጥን ይገባዋል። በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ወትሮው የራሷን ሚና ለመጫወትና ድጋፉንም ለመሰጠት ዝግጁ ነች ካሉ በኋላ አያይዘውም፥ የስደተኞች ጉዳይ በቀላሉ ሊታይ የማይገባው ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው። ይኽ በአሁኑ ሰዓት በመታየት ላይ ያለው የሰዎች ፍልሰት የዘመኑ ዓቢይ ስቃይ ነው፡ ስለዚህ ርእዮተ ዓለማዊ መልስ የሚያሻው ሳይሆን ሰብአዊ መልስ ነው የሚያስፈልገው። ስደተኛ መቀበል ማስተናገድ ግዴታ ነው። ሆኖም ሰው አገሩንና ቤቱን ጥሎ ላለ መሰደድ የሚያስችለው ሁነት ሊፈጠርለት ያስፈልጋል። የስደተኛው ጉዳይ በተመለከተም የኤውሮጳ መልስ ምድር ነው? ተከፋፍሎ የነበረው ብሔራዊ ክልል በኤወሮጳ ኅብረት ሥም ወደ ውህደት ተመጥቷል። ሆኖም ውህደቱ ኅብረአዊነት የጠበቀ መሆን ይኖርበታል፡ ኅብረአዊነት ለአንድነት መሆኑ ቤተ ክርስቲያን በመላ የኤውሮጳ አገሮች ብፅዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት አማካኝነት አብነቱን  እየሰጠች ነው። ይኽም ኅብረቱ  እሴታዊ መሠረት ያለው ከሆነ የኅብረቱ ፖለቲካ ይስተካከላል። ስለዚህ እሴቶች መሠረት ያደረገ ሲሆን አጋጥሞ ላለው የስደተኛው ጸዓት የኤውሮጳው ክርስቲያን ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ኤውሮጳዊ መልስ እርሱም ሰብአዊና ግብረ ገባዊ ግዴታ መሆኑ ተረድቶ በማስተናገድ መልስ እንደሚሰጥበት አያጠራጥርም” እንዳሉ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሹ አስታወቁ።

ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ ቅዱስነታቸው ኃላፊነቱን እንደሰጡኝ፡ መልካም አገልግሎት በመመኘት አይዞህ ሁሌ ወደ ፊት ብቻ። ሁላችን ተደጋግፈን እንጓዛለን እንዳሉዋቸው ገልጠው፥ ውይይት ንጽጽርና ማዳመጥ የተሰኙት ነጥቦች መርሓ ግብራቸው በማድረግ፥ ሱታፌን ማበረታታት ለሱታፌ የሚያመች ሁነት መፍጠር፡ ጉባእያዊነትና በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የጋራ ትብብር  በማበረታታት እንዳውም እነዚህ ጉዳዮች የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መረሓ ግብሮችም ናቸው ቅዱስ አባታችን ከኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሚሹት እርሱ ነው። በትሕትና ይኸንን መርሐ ግብር የምክር ቤቱ  መርህ በማድረግ በኢጣሊያ ላለቸው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፡ አለ ምንም ቅድመ ፍርድ በመነጻጸር፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊፈጸሙ የሚችሉት ችግሮች ቀርቦ መመልከት በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት ሊፈጸሙ የሚችሉትን አሰናካይ ተግባሮች ለማስወገድ በኢጣሊያ ያለችው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የፈጸመችው ክንዋኔ ሁሉ ግምት በመስጠት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡ ይኽም በኢጣሊያ ብቻ ሳይሆን በመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ይኸንን ዓይነቱ ገዛ እራስን ቤትን መመልከትና ማጽዳት የሚለው ትልቅ ተልእኮ በስፋት ላነቃቁትና ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሥልጣናዊ ትእዛዝ መሠረት ላስጀመሩት ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማመስገን ይገባል፥ ሕጻናት ሊነኩ አይገባም ቅዱስ አካል ናቸው ሰው ሁሉ ክቡርና ቤተ መቅደስ ነው፡ ስለዚህ እረኞች ጥንቁቆችና ንቁዎች ሆነው እረኝነትን መኖር ይገባቸዋል፡ መልካም እረኞች መሆን አለብን” በማለት የሰጡት መግለጫ ማጠናቀቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.