2017-05-24 16:44:00

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አዲስ ሊቀ መንበር እንዲሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተሾሙ


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፐሩጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጉዋልቲየሮ ባሰቲ፡ የኖቫራ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ፍራንቸስኮ ጁሊዮ ብራምቢላና የአግሪጀንቶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንቸስኮ ሞንተነግሮን ለምክር ቤቱ በሊቀ መንበርነት እጩ በማለት ለቅዱስ አባታችን ማቅረቡ ሲገለጥ፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከቀረቡላቸው ስሞች ውስጥ ብፁዕ ካርዲናል ጉዋልቲየሮ ባሰቲን እንደሰየሙ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አያይዘው ምክር ቤቱን ለአስር ዓመት በሊቀ መንበርነት የመሩት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የመጨረሻው የምክር ቤት የሊቀ መንበርነት ኃላፊነታቸው ምክንያት ባስደመጡት ንግግር፡  የኢጣሊያ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ሁነት ተንትነው ኢጣሊያ አጋጥሟት ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ተላቃ የሥራ እድል ለዜጎች ለመፍጠር የሚያስችል ብሎም የድኾች የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል የሚያግዝ የኤኮኖሚ እቅድ መንግሥት የማቀረብ ግዴታ አለበት እንዳሉ አመልክቷል።

ልወደድ ባይነት ርእዮተ ዓለም ከሚከተል ፖለቲካዊ ሥርዓት እንጠንቀቅ

ልወደድ ባይነት ርእዮተ ዓለም የሚከተል ፖለቲካዊ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ መሳይ ስርዓት ነው። በአሁኑ ሰዓት በመላ ኤውሮጳ እየተስፋፋ ብቻ ሳይሆን እግር እየተከለም ነው። ይኽ ዓይነቱ ፖሊቲካ ለሕዝብ ነው የሚጠቅመው ወይንም ደግሞ ሕዝብ መሣሪያ የሚያደርግ ሥርዓት ነው? የሚያስፈልገው ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካው ችግሮችን ተጋፍጦ መፍትሔ እንዲያገኝ መጣጣር እንጂ ችግሮችን ተገን በማድረግ ለእራስ በትረ ሥልጣን መጠቀም አይደለም። ልወደድ ባይነት ወይንም ሕዝብነት በሚል አጠራር በአሁኑ ሰዓት በኤውሮጳ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች እየተፈጠሩና እየተስፋፉ ያሉት የፖለቲካ ሰልፎች ካለ ማጥላላት በብልህ ፖለቲካና ትንተና መልስ መስጠት እንጂ እነርሱን በመከተል ጠቅላላው ፖለቲካዊ ሂደት ሕዝብነት ርእዮተ ዓለም ማስጠለቅ አይደለም። ሕዝብነት ወይንም ልወደድ ባይነት ርእዮተ ዓለም የሚከተለውን ፖለቲካ ብቃት ባለውና አመንዮ በተካነ አናቦ በመተንተን፡ የሕዝብ ስቃይ መከራ ችግር ብሶት ማእከል በማድረግ የሚሮጥ በመሆኑም መደናገጥ አያስፈልግም ስለዚህ ፖለቲካ ወደ ጥልቅ ትርጉሙ እንዲመለስ ከተደረገና ህዝብን ለማገልገል የሚያግዝ ጥበብ መሆኑ ተስተውሎ በዚህ መንገድ እግብር ላይ ማዋል ከተቻለ ለሕዝብነት ፖለቲካ ብቂ መልስ መስተት ይቻላል።

ቤተሰብ አለ መደገፍ ቅትለት ነው

በተለያየ ወቅትና ሁነት ከሚከሰቱት ከአዳዲስ ሰነ ሰብእ ትንተና ሰዉ እንዲጠበቅ አሳስበናል። በሰው ስም ባህልን ሕግን ነጻነት በሙላት ለመኖር በሚል ሰበበ አስባብ የሚነዙት ጾታዊ ብዙህነት፡ ከዚያ ባህርያው ከሆኑት ወንድና ሴት ከሚሉት ጾታዎች ውጭ ከሦስትም አራትን ከዛም በላይ የጾታ ዓይነት አለ የሚል መደናገርን የሚፈጥር ለቤተሰብ አደጋ የሆነው ሰ ሰብእ ሂደት በጥብቅ ተገቢ ምላሽ መስጠት በማኅበራዊ ረገድም ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከት ፖለቲካ በአሁኑ ሰዓት ለብቻው ለተተወው ቤተሰብ ቅርብ በመሆኑ በወሊድ እጥረት በገዛ እራሱ ላይ ቅትለት እየፈጸመ ያለው ሕብረተሰብ እራሱን ማዳን ይኖርበታል እንዳሉ ጓራሺ ገልጠዋል።

ለወጣት ትውልድ ማሰብ

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በመጨረሻም ስለ ወጣት ትውልድ እንዲታሰብ ሲያመልክቱ፡ ብዙውን ጊዜ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለመንግሥትን ለፖለቲካ አካላትን ለማኅበራውያን ተቋማትን ሁሉ በተለያየ መልኩ ጥሪ አቅርበዋል የሥራ እንድል እንዲፈጠር የተሟላ ሰብአዊ እድገት የተካነ ሕንጸት ማስፋፋት ያለው አስፈላጊነት በመተንተን እንዲህ ማድረግ ለአገር ድህነትና ለብሩህ መጻኢነት ጎዳና መሆኑም በጥልቀት አስገንዝበዋል። አሁንም የቀጥልበታል እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ ይናገራሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.