2017-04-19 16:55:00

ደቡብ ሱዳን፥ ሦስት የዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ሠራተኞች መገደል


በዓለም በሰብአዊ እርዳታ ዘርፍ ትልቅ ድጋፍ የሚስጥ ተብሎ ለሚነገርለት የዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በደቡብ ሱዳን በሚሰጠው የሰብአዊ ድጋፍና ትብብር መርሃ ግብር ተሰማርተው ከሚያገለግሉት ሠራተኞቹ ውስጥ ባለፈው ሳምንት በክልሉ ወደ ሚገኘው የማኅበሩ የምግብ እርዳታ መጋዘን ወደ ሚገኝበት ሥፍራ በመጓዝ ላይ እያሉ መገደላቸውና በዚያች አገር የሰብአዊ እርዳታ ማኅበራት አባላት ሲገደሉ ይህ የአሁኑ የቅትለት አደጋ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳልሆነም ይነገራል።

ስለዚሁ ጉዳይ በተመለከተ በኢጣሊያ ለዓለም አቀፍ የምግብር ድርጅት ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ፍራቸሲስ ከነዲዪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የደረሰው የቅትለት አደጋ ለዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ከባድ ስቃይ ነው፡ እነዚህ የተገደሉት ለተቸገረው ለተራበው ሕዝብ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማገልገል የተሰማሩ ነበሩ። የክልሉ ሕዝብ ሕይወት ለማዳን የተሰማራውን ለዚህ አይነቱ ዘግናኝ ሞት መዳረግ እጅግ የሚያስቆጣና ተረጂው ህዝብ ለከፋ አደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው።

ለተራበው ምግብር በማቅረብ የተፈናቀሉትን ሁሉ በሚገኙበት ክልል ደርሶ  ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ማቅረብ የድርጅቱ ዓላማ ነው በመሆኑም የክልሉ ሕዝብ በምግብ አቅርቦት እራሱን እንዲችል ለማድረግ በቅድሚያ ሰላም ያስፈልገዋል፡ ቀጥሎም የሥራ ዕድል መፍጠር ሲሆን ድርጅቱ በምግብ አቅርቦት ብቻ ሳይታጠር በዚህ ዓላማም ጭምር አገልግሎት ይሰጣል።

በአሁኑ ሰዓት ይኽ የዓለም አቀፍ ድርጅት በተለያዩ ክልሎች ለሰው ልጅ አስፈላጊ በሆኑት መሠረታውያን ነገሮች አቅርቦት ላይ ተጠዶ ይገኛል፡ ይኸንን አገልግሎት የሚፈጽመውም በተለያዩ የመጓጓዣ አውታሮችን በመገልገል ነው። ከምግብ አቅርቦት ውጭ ድርጅቱ  በሥነ ግብርናም ሆነ በተለያየ መስክ ስልጠና በማቅረብ ከተረጂነት ለማላቀቅ የሚያስችል ድጋፎችንም ጭምር በተለያዩ የዓም ክልሎች በማቅረብ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት በደቡብ ሱዳን አስቸኳይ የሆነው የምግብ እርዳታ አቅርቦት ነው። የዝናብ ወቅት ከመድረሱ በፊትን ሊከሰት በሚችለው የዝናብ ውሃ ሙላት ምክንያት ተደራሽነት ለማይኖራቸው ክልሎች ግና ከወዲሁ ቅሙጥ የሰአዊ እርዳታ መኖሩንም ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.