2017-03-28 11:19:00

ሰባቱ ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት


የምሕረት ተግባራት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከኅዳር 29/2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለ349 ቀናት ያህል የሚቆይ ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት ማወጃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህም ቅዱስ የምሕረት ዓመት በመላው ዓለም በምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ መንፈሳዊና አካለዊ የምሕረት ተግባራትን በመፈጸም በኅዳር 11/2009 ዓ.ም በይፋ ተጠናቁኋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተደጋጋሚ እንዳሳሰቡት በእነዚህ 349 ቀናት ውስጥ በቅዱስ በር ማለፍ እና ንስኋ መግባት አስፈላጊ መንፈሳዊ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን ንስኋችን፣ መጸጸታችንን በሚገልጽ መልኩ መልካም ተግብራትን በመፈጸም መግለጽ እንደ ሚጋባ በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን መንፈሳዊና አካላዊ የምሕረት ተግባራትን በመፈጸም ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በይፋ ከተገባደደም ቡኋላ በመላው የካቶሊክ ምዕመናን ልብ ውስጥ እነዚህ የምሕረት ተግባራት ታትመው ይቀሩ ዘንድና ቀጣይነት ባለው መልኩ እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ማከናወን የሚገባን መንፈሳዊ ግዴታዎቻችን እንደ ሆኑ ስያሳስቡን ቆየተዋል።

ስለዚህም አካላዊና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራት በእዚህ በያዝነው የዓብይ ጾም ወቅት ጾማችን ምልአት ይኖረው ዘንድ፣ ለእኛም መንፈሳዊ እና አካልዊ ፀጋን ያበዛልን ዘንድ ለየት ባለ ሁኔታ የምሕረት ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅብናል ማለት ነው። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2447 ላይ የተጠቀሱትን ሰባቱን ሥጋዊ /አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚባሉትን ከዚህ በታች እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል።

ሥጋዊ/አካለዊ የምሕረት ተግባራት

እነዚህ ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት ጠንቅቀን የምናውቃቸው ነገር ግን አብዝተን የምንዘነጋቸው መሰረታቸውን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25: 31 ጀምሮ በጠጠቀሰው የኢየሱስ አስተምህሮ ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ይህም በዓለም መጨረሻ የሚሆነውን የፍርድ ሂደት የሚያመልክትና “ኢየሱስ በመላእክቱ ታጅቦ በፍርድ ወንበር ላይ በመቀመጥ፣ እረኛው በጎችን ከፍዬሎች  እንደሚለይ እርሱም ሕዝቦችን ይለያል፣ በጎቹን በቀኙ ፍዬሎቹን ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል” እንደ ሚለው በመጨረሻው ቀን በኢየሱስ ፊት በምንቆምበት ወቅት ለሚያቀርብልን ጥያቄዎች በድፍረት በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት እንድንችል እና ከፍየሎቹ ተርታ ሳይሆን ገበጎቹ ጎራ መሰለፍ እድንችል የሚያግዙን ተግባራትን መፈጸም ይገባል። እነዚህ ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት እነማን ናቸው?

  1. የተራበን ማብላት: አሁነ በምንገኚበት ዓለማችን በጣም ብዙ የሚባሉ ሰዎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። በተቃራኒውም የበለጸጉ በሚባሉ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የምግብ ብክነት የሚታይ ሲሆን በማነኛውም ረገድ ምግብን ማባከን ተገቢ አለመሆኑን በመረዳት በግባቡ እንድንጠቀም እና የተራቡ ወገኖቻችንን፣ ጎሬቤቶቻችንን፣ እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች በየመንገዱ ወይም ደግሞ የቤታችንን በር ለሚያንኳኩ ሰዎች አስፈላጊውን ምላሽ መስጠት መንፈሳዊነታችንን ያጠናክራል ከእግዚኣብሔር በረከትን ያስገኛል። የተራበን ማብለት በረከትን ያስገኛል። በሉቃስ ወንጌል 16.19-31  ላይ የተጠቀሰውን የሀብታሙን ሰውና የድኻውን የአልዓዛር ታሪክ ማንበብና ያነበብነውን በተግባር በሕይወታችን መፈጸም ይገባናል።

  2. የተጠማን ማጠጣት: በተለያየ የዓለም ክፍል ውስጥ የሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መሰረታዊና ለሰው ልጆች ሕይወት ህልውና አስፈላጊ ከሚባሉ ነገሮች በቀዳሚነት በሚጠቀሰው የንጹህ ውሃ እጥረት ይሰቃያሉ። በንጹሕ ውሃ እጥረት የሚሰቃዩ ወንድም እና እህቶችን የተቻለንን ያህልል በማድረግ የክርስቲያናዊ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል። ይህንን የንጹህ ውሃ እጥረት ለተጠሙ ሰዎች ብቻ ውሃን በመስጠት የምንወጣው ተግባር ሊሆን ብቻ ሳይሆን የሚገባው ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል። ኢየሱስ በቃሉ “ እውነት እውነት እላችኋለሁ የኔ ደቀ መስሙር በመሆኑ ከነዚህ ታናናሶች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም” (የማቴዎስ ወንጌል 10.42)። ውሃ የተፈጥሮ ሐብት ቢሆንም በአግባቡ ካልተጠቀምነው ግን ሊያል የሚችል ሐብት ነው።  ውሃ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በሁለቱም ኪዳኖች ውስጥ የደኅንነት ምንጭ እና እግዚኣብሔር በጌታችን በኢየሱስ አማካይነት በልጁ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ የሚሰጥ የዘላለም ሕይወት ምልክት ሆንም ይጠቀሳል። ስለዚህም በጾማችን ወቅት በንጽሑ ውሃ እጥረት የሚሰቃዩትን ወገኖች ማሰብ  ይጠበቅብናል፣ እኛም ንጹህ ውሃ የማግኘት እድል የገጠመን ሰዎች ሁሉ ውሃን በቁጠባ እና በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል።
  3. የታረዘን ማልበስ፡ ሦስተኛ ሥጋዊ/አካልዊ የምሕረት ተግባር ደግሞ የታረዘን ማልበስ የሚለው ነው። ቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፍ ቅዱሳችን የተጠቀሱትን 10ቱን ትዕዛዛት እንድናከብርና በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያን ምስጢራትን እንድንሳተፍ ጸሎት ማድረግም አስፈላጊ እንደ ሆነ ታስተምረናለች።  ብዙን ጊዜ በየመኖሪያ ቤቶቻችን የሚገኙትን የቁም ሳጠኖችን ከፍተን በምናይበት ወቅት በጣም ብዙ ሊባሉ የሚችሉ የምንጠቀምባቸው አልባስት በብዛት ይገኙ ይሆናል። በማቴዎስ ወንጌል ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን በፍርድ ወንበር ላይ ሆኖ በጎቹን ከፊየሎቹ በሚለይበት ወቅት ከሚጠይቀን አንዱ ጥያቄ መኃል ታርዤ አልብሳቹኛል ወይ የሚለው ነው። ስለዚህም በመጨረሻው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያቀርብልን ጥያቄ አንገታችንን ቀና አድርገን በልበ ሙሉነት አዎን የታረዘን ለማልበስ ሞክሬ ነበር ብልን እንድንመልስ እና ከፍየሎቹ ሳይሆን ከበጎቹ ጎራ መሰለፍ እንድንችል ጉልበት የሚሰጠንን መልካም ነገር በተለይም በአሁኑ በዓብይ ጾም ወቅት ይህንን መልካም ተግባር መፈጸም ይገባናል።
  4. መጠልያ የሌላቸውን ሰዎች ማስጠለል፡የሰው ልጆች በተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የተነሳ ለመጠሊያ እጥረት ይጋለጣሉ። ይህንንም ሁኔታ ለመረዳት ርቀን መሄድ አይጠበቅብንም። ምክንያቱም በየመንገዱ ላይ ወድቀው የሚገኙ ብዙ ሰዎችን ማየት የተለመደ በመሆኑ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን በመኖሪያ ቤት እጥረት የሚሰቃዩ ሰዎችን በተለይም በየጎዳንው ላይ ሰፍረው የሚገኙ የወደፊት የሀገር ተረካቢ የሚሆን ሕጻናትን ማገዝ እንደ ሚገባን ጥሪ ያደርግልናል። በሉቃስ ወንጌል 16: 19-31 ላይ የተጠቀሰውን የሐብታሙን ሰው እና የድኸውን የአልዓዛርን ምሳሌ መመልከት ተገቢ ነው። ድኻው አልዓዛር በሐብታሙ ሰው በር ሥር ተኞቶ በብርድ እና በርሃብ ሲሰቃይ ሐብታሙ ሰው ግን ሁሌ ማታ ማታ በቤቱ ድግስ ያዘጋጅ ነበር። አልዓዛርን ግን አላሰበው ነበር። በመጨረሻው ቀን ግን ሁሉም የተገላቢጦሽ ሆኖ ነበር። ድኻው አልዓዛር በምድራዊ ሕይወቱ በጣም ተሰቃይቶ የነበረ ሲሆን በሰማያዊ በቱ ግን የቅዱሳን መኅበር አባል በመሆን አዲስ የደስታ ሕይወት መኖር ሲጀምር በተቃራኒው ደግሞ በእዚህ ምድር በደስታ እና በፍስሐ የኖረው ሐብታሙ ሰው ግን ወደ ገሐነም እሳት ተጣለ። በጾማችን ወቅት በየቤቶቻችን ደጅ ላይ የሚገኙትን መጠለያ ያጡትን ሰዎች መርዳት ይኖርብናል።
  5. ሕሙማንን መጎብኘት (ማቴ። 25.36 ታምሜ አስታምማችኋኛል)፡ ብዙን ጊዜ የታመሙ ወገኖቻችንን እንዘነጋቸዋለን። ማስተዋል የሚገባን ጉዳይ እነዚህ ታማሚዎች የእኛን ትኩረት እና እርዳት እንደ ሚሹ ማወቅ ግን ያስፈልጋል። የተማሙትን ለመርዳት ምን ምን ተጨባጭ የሆኑ ተግባሮችን መፈጸም ይገባና?

    1. ደም መለግስ

    2. በማይድን በሽታዎች የሚሰቃዩትን ሰዎች ወደ አሉበት ሥፍራ ሄዶ ማጫወት፣ ማዋራት፣ ስቃያቸውን ለጊዜውም ቢሆን እንዲረሱ ማድረግ ያስፈልጋል።

    3. በአከባቢያችን የሚገኙትን የእድሜ ባለዘጎችን መጎብኘት ያስፈለጋል።

    4. ምግብ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ካሉ፣ መድኋኒት የሚፈልጉ ካሉ የመሳሰሉትን እርዳታዎችን ማድረግ ይጠበቃል።

6. የታሰረን መጎብኘት (ማቴ። 25.36) “በዓለም መጨረሻ የሰው ልጅ በመልአክቱ ታጅቦ በክብር ሲመጣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል. . . ታስሬ ጠይቃችሁኛል ወይ? ብሎ ይጠይቃአናል። (ማቴዎስ 25.43)።  በእሥር ላይ የሚገኙ ሰዎች ምንም እንኳን ከጥፋታቸው ይታረሙ ዘንድ በማሰብ የታሠሩ ቢሆንም በእግዚኣብሔር ምልክ እና አምሳያ የተፈጠሩ ወንድም እህቶቻችን መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም። ምንም ዓይነት ስህተት ይፈጽሙ የእግዚኣብሔር ቃልን እንዲሰሙ ማድረግ እና እንዲጸጸቱ መርዳት አስፈላጊ ነው። ስለእዚህም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሣ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን በመጎብኘት፣ ከስህተታቸው ታርመው መልካም ዘጋ ይሆኑ ዘንድ በመጎብኘት ማጽናናት እና ማስተማር ክርስቲያናዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የዜግነትም ግዴታ ነው። በሐሰት መስክሮባቸው፣ ወይም በስህተት በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችንም መጎብኘት፣ በሐሰት የታሰሩ ሰዎች ከሆኑ ተስፋ እንዳይቆርጡ ከመምከር ባሻገር እውነታው ግልጽ እንዲወጣ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል።

7. የሞተን መቅበር (መ. ጦቢት 1.17-19)

ክቡራን እና ክቡራት ታዳሚዎቻችን ቀደም ሲል ስትከታተሉት የነበራችሁት የዓብይ ጾምን አስመልክተን በእዚህ የጾማችን ወቅት ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ሊተገብሩት ይገባል በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን ያዘዙንን ሰባቱን አካልዊ የምሕረት ተግባራት የሚባሉት ነበር።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.