2017-03-27 17:03:00

የኔታ ቪጋኖ፥ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ህዳሴ መመዘኛው ሓዋርያዊነት ነው


“ከ20 ዓመት በኋላ ምን አይነት ቤተ ክርስቲያን” በሚል ጥያቄ ተማክሎ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 23 ቀን እስከ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ከተባበሩት የአመሪካ መግሥታ ግዛት ፐንስይልቫኒያ ከሚገኘው ቪላኖቫ መንበረ ጥበብ ጋር በመተባበር፥ “በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሥተዳድር ዘንድ ሥነ ፈጠራ የሚኖረው ሚና” በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ትርኢት መዝጊያ ቀን የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጽ/ቤት ዋና ጸሓፊ የኔታ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ ተገኝተው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ያነቃቁት ዘርፈ ብዙ ኅዳሴ በቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ዘንድ ያለው አወታዊ አስተዋጽኦ ተኮር አስተምህሮ መስጠታቸው የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

በዚህ በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን ውፉያን የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት አባላት በማሳተፍ በተካሄደው ዓውደ ትርኢት ቀደም ብለው የመንበረ ጥበቡ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ዳል ኮቮሎ ዓውደ ትርኢቱ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር አካሂደዉት በነበረው ቃለ ምልልስ፥ የዓውደ ትርኢቱ ተሳታፊያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲረጋገጥ ያስገነዝቡት ኅዳሴ እግብር ላይ በማዋሉ ሂደት የተሰማሩትና በዚህ ተልእኮ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውና በቅድሚያ ዓውደ ጉባኤው የፈጠራ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚኖረው ተጽእኖ ምን መሆኑ ለመለየትና የፈጠራ ብቃት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሂደት እንዴትና በምን ዓነትት ሁኔታ መተዳደር እንደሚኖርበት የሚያስረዳ መሆኑ ገልጠው፡  ፈጠራ ዙሪያ የሚወያይ በመሆኑም ክፍትና አዲስ ሃሳቦችን የሚያስተናግድ ዓውደ ትርኢት ነው ብለው እንደነበር ይታወሳል።

የዚህ ዓይነት ዓውደ ትርኢት እንዲካሄድ ዋናው ግፊት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያየ ወቅት በሚሰጡት አስተምህሮ፡ ምዕዳን ስብከትና በሚያሰሙት ንግግር የፈጠራ ሥራ (ብቃት) በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አቢይ አስተዋጽኦ አለው በማለት የሚያሰምሩበት ሃሳብ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ዳል ኮቮሎ ሲያስታውሱ፡ የኔታ ቪጋኖ ፥ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን መዋቅራዊ ኅዳሴ መመዘኛው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተልእኮ ነው ብለው ለወንጌል ታማኝ በመሆን የፈጠራ ችሎታውና ብቃቱንም በማሳካት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያሳስቡት ኅዳሴ እግብር ላይ ማዋል። ስለዚህ ኅዳሴ ሲባል ለወንጌል ታማኝ በመሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቃልና የቅድስት መንበር ፍጻሜዎች ባጠቃላይ ወደ ሁሉም አገሮች ማዳረስ ማለት ነው። ለጌታችን ኢየሱስ ወንጌል ታማኝ በመሆን ለህዳሴ ክፍት መሆን። እንዲህ ካልሆነ እንዲህ ነበር የሚደረገው እየተባለ ባለህበት በመሄድ ፈተና ተሸንፈህ መንፈስ ቅዱስ ለሚያነቃቃው ኅዳሴ ገዛ እራስህን ዝግ ማድረግ ማለት ይሆናል፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያሳስቡት የህዳሴ ጥሪ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ወቅታዊው የዓለም ሁኔታ እርሱም ሰብአዊ  ፖለቲካዊ ማሕበራዊ ባህላዊ ሁነቶች ግምት የሰጠ ነው። ይኸን ሁነት በወንጌል ሥር ማንበብና ማስተዋል ማለት መሆኑ የሚተነትን ሰፊ አስተምህሮ ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.