2016-10-20 17:07:00

የቅድስት መንበር ልኡክ በተባበሩት መንግሥታት የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ዝክረ ነገር ባደረገው ጉባኤ ያስደመጡት ንግግር


የዓለም ሕዝብ በኑክሊየር የጦር መሣርያ ተከትሎ የሚመጣው ጉዳቱ በቀጣይነት የሚያስነብረው በላዩ ላይ ከሚያንዣብበው ዛቻ ነጻ ይሆን ዘንድ የሚያሰማው ድምጹን ቅድስት መንበር የራሷ በማድረግ ስለ ሰብእዊ ፍጡር ሁሉ ድምጿን ታሰማለች ያሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተጠራው የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ዝክረ ነገር ባደረገው 71ኛው ክፍለ ጉባኤ የተሳተፉት ለቅድስት መንበር ቋም ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በርናርዲቶ አውዛ፥ ሰላምና የዓለም አቀፍ መረጋጋት በዓለም ተመጣጣኝ ዛቻ በማስፋፋት አይደለም፡ ሰላምና መረጋጋት በሁሉም አገሮች የተመጣጠነ ሌላው የማስፈራራት ብቃት በማረጋገጥ የሚከወን አይደለም እንዳሉ ዘጋቢያችን ጃዳ አኵይሊኖ አስታውቋል።

በአቶሚክ የጦር መሣሪያ ማነጣጠር ሰላም የተጠበቀ ማድረግ የሚለው አነጋገር የተሳሳተ እምነት ነው

የኑክሊየር ጦር መሣሪያ አታላይ የሆነ መረጋጋት የሚያስገኝና በኑክሊየር ጦር መሣሪያ የሚረጋገጠው ሰላም አደገኛነቱ እጅግ ከፍ ያለ የተሳሳተ እምነት ነው። ስለዚህ የጦር መሣሪያ ባለ ቤትነት ግብረ ገባዊ ስህተትና ይኽ ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ክውንተ አውታር አማካኝነት ሊጤን ይገባዋል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይሊኖ አያይዘው፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኑክሊየር የጦር መሣሪያ ላንዴና ለመጨረሻ እንዲታገድ ጥሪ ያቀርባሉ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በቪየና የኑክሊየር የጦር መሣሪያ በሰው ልጅ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ በሚል ርእስ ዙሪያ ተወያይቶ ወደ ነበረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት ሰላምና ወድማማችነት የምኞታቸው ማእከል በማድረግ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙላት የታገደ የማድረጉ ውሳኔ ሰላምና ወንድማማችነት እንደሚያስገኝ አስተማማኝ ሲሆን የጋራ ቤታችን የሆነው ተፈጥሮም ጭምር የዚህ ውጤት ተቋዳሽ ይሆናል። ሰላም በፍትህ በማኅበረ ኤኮኖሚያዊ ልማት በነጻነት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር በማክበር በሁሉም ማኅበራዊ ጉዳይ የሕዝብ እኩል ተሳታፊነት በማረጋገጥ በሕዝቦች መካከል መተማመን በመገንባት ላይ የጸና ሲሆን ዘላቂ ይሆናል በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ ብፁዕ አቡነ በርናርዲቶ አውዛ በማስታወስ ደግማው እንዳስተጋቡት ያመለክታሉ።

የቅድስት መንበር የኑክሊያር ጦር መሣሪያ ምርት ኣገች ውሳኔ ገቢራዊነት ትቆማለች

ብፁዕ አቡነ አውዛ ባሰሙት ንግግር ዓለም አቀፍ ደረጃ የኑክሊየር ጦር መሳሪያ ምርት የእገዳ ስምምነት ለዓለም አቀፍ ስምምነት ሕይወት መሆኑ ቅድስት መንበር እንደምታምንበትና ይኸንን ውሳሄ ሁሉም አገሮች አለ መከተል ምንኛ አደገኛ መሆኑ በማብራራ እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ጉዳይ በተመለክተ ጽኑ ሁሉንም የሚያጣምድ ሕግ ዙሪያ ለይቶ በትክክል እንዲወያይ አንድ ዓለም እቀፋዊ ጉባኤ ይጠራ ዘንድ ታነቃቃለች ብለው ከገለጡ በኋላ አያይዘው፥

የሁሉም ቀደምት የአገር ተወላጆች በአገሬዎች የሚጠሩት የኅብረተሰብ ክፍል አባላት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ

የአገሬዎች ሕዝቦች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሚለውን ሃሳብ ማእከል በማድረግ የእነዚህ በአሁኑ ሰዓት ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ ብዛት ውስጥ 370 ሚሊዮን ይሸፍናል ነው ተብሎ የሚነገርላቸው አገሬዎች በአሁኑ ሰዓት ትርፍ ማካባት በሚለው የዓለም ፖለቲካ በሚከተለው የሰው ልጅ መብትና ክብር ብሎም የተፈጥሮ ምኅዳር ግድ የማይለው ሂደት ለከፋ አደጋ ተጋልጠው ከገዛ መሬታቸውና አካባቢያችው እንዲፈናቀሉ ከመደረግም አልፎ ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። ስለዚህ እ.ኤ.አ. እክሰ 2030 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ግቡን ይመታ ዘንድ በፓሪስ የተደረሰው የልማት እቅድ ዝክረ ነገር የተፈጥሮ የአካባቢ አየር ጥበቃ ስምምነት ጋር አሳክቶ በዚህ እቅድ አገሬዎች በታዛቢነት ሳይሆን በተወናዋይነት እንዲካተቱና በአገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረጉት የልማት እቅዶችና ስለ ልማት በሚደርጉ ስምምነቶች በዋነኛነት ታሳታፊያን እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት ያስደመጡት ንግግር እንዳጠቃለሉ አኵይሉኖ አስታውቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.