2016-09-22 09:21:00

በአሲዚ እ.ኤ.አ. የ2016 ዓ.ም. ስለ ሰላም የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች የጋራ ጸሎት


ሁሌ እንደተለመደው ያ የዛሬ 30 ዓመት በፊት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አነሳሽነት በካቶሊካዊው የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ተባባሪነት አንድ ብሎ የጀመረው የሁሉም ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች በማሳተፍ የሚካሄደው ስለ ሰላም የጋራ ጸሎት ዘንድሮ እ.ኤ.አ. በአሲዚ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. የተለያዩ የባህል የፖለቲካ የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ማታረላ የሰላም ኖቤል ተሸላሚዎች ማኅበር ሌሎች ከአስራ ሁለተ ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በማሳተፍ የሰላም ጥም፥ የተለያዩ ሃይማኖቶችና ባህሎች ለጋራ ውይይት” በሚል ርእስ ጉዳይ ተመርቶ የተካሂደው የጋራ ስለ ሰላም የጸሎት ሥነ ስርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተሳተፉበት መንፈሳዊ መርሓ ግብር እ.ኤ.አ. መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፕተር ማረፊያ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠቱ 10 ሰዓት ተኩል ተነስተው አስራ አንድ ሰዓት ተኩል አሲዚ ቅድስተ ማርያም ዘመላእክት በሚገኘው በመጋገሊ የእግር ኳስ ሜዳ እንደደረሱም እዛው የአሲዚ ኖቸራ ኡምብሪያ ጉአልዶ ታዲኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሶረንቲኖ የኡምብሪያ ክርለ አገር አስተዳዳሪ ካቲዩሻ ማሪኒ የኡምብሪያ ኅየንተ መንግሥት ራፋኤለ ካኒዛሮና የአሲዚ ከንቲባ ስተፋኒያ ፕሮየቲ አቀባበል ተደጎላቸው ወደ ፍራንቸስካውያን ገዳም እንደደረሱም በፍራንቸስካውያን ገዳm ዓቃቤ አባ ማውሮ ጋምበቲና 25ኛ ዓመት ዝክረ ፕትርክናቸውን ያከበሩት በዚህ አጋጣሚም ከፐሩጃ መንበረ ጥበብ በዓለም አቀፍ የስነ ግኑኝነ ስነ ምርምር ጉዳይ የክብር ማእርግ የተሰጣቸው የቁስጥንጥንya የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ፡ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፍሳዊ መሪ የካንተበሪ ሊቀ ጳጳስ ጸጋዊነታቸው ጁስቲን ወልባይ፡ leአንጽዮኪያ የሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኢግናዚዩስ ኤፍረም ዳግማዊ፡ የሮማ የአይሁድ ሃይማኖት መሪ አቢይ መምህር ፕሮፈሰር ሪካርዶ ሰኚ፡ በግብጽ የአል አዝሃር መንበረ ጥበብ ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር አባስ ሹማን፡ የኡምብሪያ ብፁዓን ጳጳሳትና ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን በመወከል በተገኙት ዜጎች እና በሌሎች የተለያዩ ሃyማኖቶ የበላይ መንፈሳዊ ምሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸው ከሁሉም ጋር በተናጥል አጭር ክሌአዊ የጋራ ግኑኝነት ማካሄዳቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥ ልክ እኩለ ቀን በፍራንቸስካውያን ገዳም ባለው ማእድ ቤት በጋራ ከሁሉም ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳዊ መራህያን ስደተኞችና ተፈናቃዮች የወከሉትን ባሳተፈው የምሳ ማእድ ተቋድሰው በዚህ አጋጣሚም የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ባስደመጡት መልእክት የብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ 25 ዓመት ፕትርክና ዘክረው የምሳ መዓዱ ተጠናቆ እንዳበቃም ከቀትር በኋላ ልክ ሦስት ሰዓት ከሩብ ቅዱስ አባታችን ከፓትሪያርክ ቅዱስነታቸው በርጠለመዎስ ቀዳማዊ በአንጽዮኪያ የሶሪያ ስርዓት ለምትከተለው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ፓትሪያርክ ቅዱስነታቸው ኢግናዚዩስ ኤፍረም ዳግማዊ ከውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና የእንግልጣር አንክሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ጸጋዊነታቸው ጁስቲን ወልባይ፡ የፖላንድ ተወላጅ የስነ ኅብረተሰብና የፍልስፍና ሊቅ ፕሮፈሰር ዝይግሙት ባኡማን ከኢንዶነዢያ የኡለማ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ዲን ስያምሱዲን፡ በእስራኤል የአይሁድ ሃይማኖት አቢይ መምህር ዳቪድ ሮሰን በጃፓን 257ኛው የቡድሃ ተንዳይ ሃይማኖ የበላይ መንፈሳዊ መምህር ክቡረ ክቡራት ኮኣኢ ሞሪክዋ ጋር ከተገናኙ በኋላ ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች እንደየ ተአምኖተ ሃይማኖታቸው  የሰላም የጸሎት ሥነ ስርዓት ያከናወኑ ዘንድ ወደ ተመደበላቸው የተለያየ ስፍራ መዛወራቸው አስታውቋል።

የሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የሰላም ጸሎት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሰጡት ቃለ አስተንትኖ የተከናወነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በሰጡት ቃለ አስተንትኖ የዚህ የዘንድሮው የሰላም የጋራው ጸሎት መሪ ቃል “የሰላም ጥማት፥ ሃይማኖቶችና ባህሎች ለጋራ ውይይት” የሚል መሆኑ አስታውሰው በዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19 ቁጥር 28 “… ኢየሱስ ጠማኝ አለ…” የውኃ ጥማት ከእርሃብ እጅግ ይብሳል። የሚጠጣ ውኃ ማጣት ሊመጣጠነው የሚችል ሌላ ዓነትት ችግር አለ ብሎ ለመናገር ያዳግታል። ያ ልኡል ጌታ ለምሕረቱ ብሎ በሰው ዘንድ እራሱን ዝቅ አደረገ።

ጌታ ጠማኝ ይላል። የተጠማውስ ምንድር ነው? በእርግጥ ያ ለሕይወት አስፈላጊ የሆነው ውኃ በማጣቱ ነው ጠማኝ የሚለው። በተለየ ግን ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ ከሚባሉት ሁሉ ባልተናነሰ ደረጃ የሚገለጠው ፍቅር ነው የተጠማው። እኛን በማፍቅሩ ከዚህ አፍቃሪው ፍቅሩ የሚመነጭውን ውኃ ለመስጠታችን ነው የተጠማው። ፍቅራችን ነው የተጠማው። በነቢይ ኤርሚያስ ምዕ. 2 ቁጥር 2 እግዚአብሔር “በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ” ሲል እኛ ለእርሱ የነበረንን ፍቅር በናፍቆት ያስታውሳል። ሰው ተመስገን የማይል በመሆኑም ይኸንን ፍቅር ረስቶ ውኃ የማይገኝበት የማይፈልቅበ ጉድጓድ ይቆፍራል ኤርሚያስ ምዕ. 2 ቁ. 13 “ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተዋል። ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል” ሲል እንደሚገልጠውም ነው። ይኽ ደግሞ ያ ፍቅርን በፍቅር የማይመልስ ደንዳናው ልብ የሚገልጥ ሲሆን፡ እርሱም መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 69 ቁ. 21 “ … ለጥማቴ ሆምጣጤ ሰጡኝ” እዳለው ነው። የሚያሳዝን ትርኢት።

ያልተፈቀረ ፍቅር፡ ያፈቀረህን ፍቅር በተመጣጠነ የፍቅር ደረጃ አለ ማፍቀር። ታሪክ እንደሚያስታሰንም ይኽ አይነቱ ያልተፈቀረ ፍቅር ቅዱስ ፍራንቸስኮ እጅግ እንዳሳሰበውና ስለ የጌታ ስቃይ ሲል ድምጹን ከፍ በማድረግ ያለቅስና ያነባም እንደነበር የፍራንቸስካውያን የታሪክ ማኅድር ይገልጠዋል (ፍራንቸስካዊያን ታሪክ ቁ. 1413 ተመልከት)፡ እንግዲያስ ያንን ስቁል ያ ፍቅር የተጠማውን ጌታ ስናስተነትን ይኸንን ነው ማስተዋል የሚገባን። እናቴ ቅድስት ተረዛ ዘካልኩታ ለዚህም ነው በሁሉም በማኅበሯ ቤት ባለው የስቁል እየሱስ ምስል ስር ጠማኝ የሚለው ቃል እንዲጻፍ ያደረገቸው። ቅድስት ተረዛ ለዚህ ጠማኝ ለሚለው ጌታ የተጠሙትን የተራቡት የተገፉትን በማገልገል መልስ ትሰጣለች። በድኽነት በስቃይ በሚገኙት ወንድሞቻንና እህቶቻችን ፊት ጉልበታችንን አጥፈን የዋሁን ፍቅር ስንኖር የጌታን ጥም እናረካለን። በመጨረሻው በፍርድ ሰዓትም ለእነዚያ ለተጠሙት ለድኾችና ለተናቁት ተጨባጭ የዋህ ፍቅር የሚያሳዩት ጌታ ብፁዓን ሲል ይጠራቸዋል፡ ይኽም ኢየሱስ “በእውነት እላችኋለሁ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው ሲል” (ማቴ. 25.40) እንደተናገረውም ነው።

የኢየሱስ ቃል በእነዚያ መስተንግዶ በሚጠይቁት በሕይወት እያሉ መልስ በሚጠይቁት አማካኝነት ይናገረናል። በዚያ ጠማኝ በሚለው የጌታ ቃል የእነዚያ በዓለም እያሉ ሕይወት የጨለመባቸው የሚሰቃዩት የተናንሽ ንጹሓንና ድኾች የእነዚያ በጦርነት ምክንያት ሕይወታቸው ለአደጋ የተጋለጠባቸው ሁሉን ጥለው የሚሰደዱት ድምጽ ይስተጋባል። እነዚህ ጌታ ተናንሽ በማለት የሚጠራቸው ወድሞችና እህቶች የመንግሥቱ አካል የሚላቸው የዚያ የቆሰለው የሥጋው ክፍለ አካሉ ናቸው። ድምጽ አላቸው ሆኖም ልክ እንደ ጌታ ጠማኝ ሲሉ ሆምጣጤ ይቀርብላቸዋል። የተነፍጎ ሆምጣጤ የሚጠጡ፡ ማን ነው ድምጻቸውን የሚሰማ? ማን ነው ስለ እነርሱ የሚያስብ? የሚያሳዝነውም ለእኔ ባይነት ስግብግብነት አልፎ አልፎም ለደገፋቸው በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የሚነገርላቸው የማስታገሻ ማስታወቂያ አማካኝነት ድኾችን አርቆ በማስቀመጥ ለአልቦ ርህራሄ ሁነት የተጋለጡ ሆነው ማየቱ ነው።

በዚያ “ኃይልና ጥበብ” (1ቆሮ. 1,24) በሆነው በስቁል ጌታ እኛ ክርስቲያን ያንን የፍቅር ምላሽ ያላገኘው ፍቅር በማስተንተን በዓለም ምህረትን እናስፋፋ ዘንድ ተጠርተናል። በዚያ የሕይወት ግንድ በሆነው መስቀል ያ የክፋት መንፈስ ተሸንፏል። ወደ መልካምነት ተለውጧል። እኛ የስቁል ኢየሱስ ተከታዮች እነዚያ የግድ የለሽነት ተግባር የሚሰጠውን መሪር ጽዋ በመጎንጨት ለዓለም የፍቅር እስትንፋስ የሚሰጡ የሕይወት ግንድ እንሆን ዘንድ ተጠርተናል። ከስቁል ኢየሱስ ጎድን የድሕነት ደም የሕይወት ትእምርት የሆነው ውሃ ፈሰሰ (ዮሐ. 19,34) ዛሬም ከእኛ እማኞቹ ለጠማቸው ሁሉ ደግነት ይፈልቃል።

እንደ ማርያም በመስቀል እግር ሥር መሆን። ጌታ ለእነዚያ ለቆሰሉት ቅርብ እንሆን ዘንድ ቅርቦቹ እንድንሆን ይፈቅዳል። ለእነዚያ በአሁኑ ሰዓት የስቁል ሕይወት ለሚኖሩት ሁሉ ከዚያ ሞትን አሸንፎ ከተነሳው ስቁል ኢየሱስ የማፍቀር ትእምርት የሆነውን ውኃ እናወጣለን። እርሱ ሰላማችን ነው (ኤፈ. 2,14) ቅርብና እሩቅ ላሉት ሁሉ ሰላም ለማበሰር የመጣው (ኤፈ. 2,17) ሰላማችን በሆነው (ኤፈ. 2,14) ይኸንን ስናደርግ በመካከላችን ውህደትና ሱታፌ ይረጋገጣል። ምክንይቱም ፍላጎቱ “አንድ እንዲሆኑ (ዮሐ. 17,21) የሚል ነውና። ስለዚህ እርሱ በፍቅሩ ያቅበን በውህድነት ይቀበለን በማለት የለገሱት ቃለ አስተንትኖ ማጠቃለላቸ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እያንዳንዱ የተለያዩ ኃይማኖች ስለ ሰላም የጸሎት ስነ ሥርዓት ፈጽመው ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች ቅዱስ ፍራቸስኮ አደባባይ በአንድነት ተገናኝተው የአሲዚ ኖቸራ ኡምብራ ጉኣልዶ ታዲኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሶሬንቲኖ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ገዳም አቃቤ አባ ማውሮ ጋምበቲ የቅዱስ ኤጂዲያ ማኅበር መስራች ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ የሶሪያ ዜጋ ተወላጅ ስደተኛ ታማራ ሚካሊ ብፁዕ ወቅዱስ በጠለመዎስ ቀዳማዊ የእስራኤል አቢይ መምህር ዳቪድ ብርድማን በጃፓን የታንዳይ ቡድሃ ሃይማኖ ክቡረ ክቡራት ኮይ ማሪኮዋ በኢንዶነዢያ የኡሌማ ምክር ቤት ሊቀ መንበ ፕሮፈሰር ዲን ስያምሱዲን ንግግር ካስደመጡ በኋላ ቀዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ ምዕዳን ለግሰዋል።  

የሕሊና ጸሎት ተከናውኖ እንዳበቃም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ የሰላም የጥሪ መልእክት አቅርበው እንዳበቁም የሰላሙ መልእክት የሁሉም ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች አማካኝነት ለሁሉም እገሮች እንዲተላለፍ ከተለያዩ አገሮች ለተወጣጡት ሕጻናት ታድሎ እንዳበቃም የሃይማኖት መሪዎች በሰላሙ መልእክት ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሰላምታን በመለዋወጥ የሰላም ትእምርት የሆንው ሻማ የማብራት ስነ ሥርዓሥነ በማከናወን የዘንድሮው የአሲዚ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ስለ ሰላም የጸሎት መርሃ ግብር መጠናቀቁ የድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.