2016-05-18 16:26:00

የሐዘን መግለጫ የተሌግራም መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ.ም. 90 ዓመት ዕድሜያቸውን አክብረው የነብሩት ሮማ በሚገኘው ቪላ ሉዊሳ በተሰየመው የአዛውንት ተንከባካቢ ማእከል ውስጥ እንክብካቤ እያገኙ የነበሩት በኢጣኢያ አልባ ከተማ እ.ኤ.አ. በ 1925 ዓ.ም. የተወለዱት ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ኮፓ እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ምክንያት ለብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ የሐዘን መግለጫ የቴለግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት፥ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ኮፓ የሚደነቁ የቤተ ክርስቲያን ሰው ቤተ ክርስቲያንን በታማኝነት ያገለገሉ ታማኝ አገአልጋይ በማለት እንደገለጡዋቸውና ክህነታቸው ከዛም በጵጵስና ብሎም በካርዲናልነት ሐዋርያዊ ኃላፊነት ወንጌልን ቅድስት መንበርን በትጋት ያገለገሉ ትሁት የዋህ ላለፉት ስድስት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ያገለገሉ እጅግ ጥንቃቄ በሚጠይቁ ተልእኮዎች ተመድበውም በጥራትና ትጋት ያገለገሉ አቢይ የሥነ ላቲን ባህልና ቋንቋ ሊቅ በዚሁ በነበራቸው ሊቅነትም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የተዋጣለት እንዲሆን አቢይ አስተዋፅዖ የሰጡ በማለት እንደገለጡዋቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕ ካርዲናል ኮፓ በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ መሥተዳድር ሥር በመታቀፍ ከ 1952 ዓ.ም. ማገልገ ጀምረው በ 1958 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ቢሮ ውስጥ ተመድበው ያገለገሉ፡ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በመሳተፍ በነበራቸው የሥነ ላቲን ባህልና ቋንቋ ሊቅነትም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ በማጠናቀሩና ለኅትመት በማብቃቱም ረገድ አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥  እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 1980 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሰታ ስዩም ሊቀ ጳጳስ ተብለው ከተመረጡ በኋላ ማዕርገ ጵጵስናውን ከቅዱስነታቸው እጅ ተቀብለው፡ በ 1990 ዓ.ም. በቀድሞ ቸኮስላቫኪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በተጨማሪም በረፓሊክ ቸክና በስሎቫኪያም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሆነው እንዲያገለሉ በ1993 ዓ.ም. ከተሾሙ በኋላ እስከ 2001 ዓ.ም. በፕራግ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን እንዳገለገሉም በማስታወስ ያመለክታል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ካርዲናል ተብለው መሾማቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞ እንዳመለከተውም በጠቅላላ የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት በብፁዕ ካርዲናል ኮፓ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት ወደ 214 ሲወርድ ከእነዚህም ውስጥ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ሕገ ቀኖና ባስቀመጠው መሥፍረት እርሱም ከ80 ዓ.ም. እድሜ በታች የሚለው ውሳኔ መሰረት የመምረጥ መብት ያላቸው 114 መሆናቸው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.