2016-02-13 16:55:00

የተደረግው ውይይት ግልጽ፣ፍሬአማና በውንድማማችነት መንፈስ የተደረገ መሆኑን አስተውቀዋል


በተላንትናው እለት ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 12.2016 በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና ከሞስኮ እና የጠቅላላው ሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ክሪል ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ቅዱስ ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮ ከውይይቱ ቡኋል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስወቁት በሁለቱ አብያተ ክርስትያን መሪዎች መካከክል የተደረግው ውይይት ግልጽ፣ፍሬአማና በውንድማማችነት መንፈስ የተደረገ መሆኑን ገልጸው በተደረገው ገንቢ ውይይት መንፈሳዊ እርካታ እንደተሰማቸው አስተውቀዋል።

ቅዱስነታቸው ከፓትርያርክ ክሪል ጋር ካደረጉት ውይይት ቡኋል ለጋዜጠኞች የምከተለውን መግለጫ ሰተዋል።

“ውይይታችን መሰረት ያደረገው የተቀበልነውን አንድ ጥምቀት በመሆኑንና ሁለታችንም የቤተ ክርስትያን መሪ አቡናት መሆናችንን ከግንዛቤ የስገባ ነበረ። ስለ ቤተ ክርስትያናችን ገንቢ ውይይቶችን በማድረግ ወደፊት እንዴት በአንድነት መጓዝ እንዳለብን ተመካክረናል። ግልጽነት በተሞላው መልኩና የለምንም ጥርጣሬ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላችን መንፈስ ቅዱስ  በውይይታችን ወቅት ከእኛ ጋር እንደ ነበረ እንድሰማኝ አድርጎኛል። ቅዱስነቶ ስላሳዩኝ ትህትና፣ የወንድማማችነት መንፈስ በተለይም ደግሞ አንድነትን ለምፍጠር ያሎትን ትልቅ ጉጉት ፍላጎት በማድነቅና በተጨማሪም ላመስግኖት እወዳለሁ”።

“አንድነታችንን ለማጠናከር ያሳየነው መነሳሳት አላማችንን እውን ለማድርግ ያስችለናል ብዬ አምናለው። ቅዱስነቶ፣ በተለይም እርሶን  እንድሁም ይህንን ውይይት በምናደርግበት ወቅት የተባበሩንን በተለይም ሁለት ሰዎችን ለማመስገን እወዳለው እንርሱም የተከበሩ መጥሮፖሊታን ሕራሊዮን እና ካርዲናል ኮክ እንድሁም በዝህ ወቅት የተባበሩንን ግብረ አበሮቻችን ጭምር ማመስገን እፈልጋለው”።

“በተጨማሪም ኩባን፣ የኩባን ሕዝብና እዝህ ከእኛ ጋር የምገኙትን የኩባን ፕሬዝደንት ስላደርጉልን ተጨባጭ እገዛ እና ልትረዱን ያሳያችቱትን ፍላጎት ማመስገን እፈልጋለሁ። ኩባ በዝህ መንገድ የምትቀጥል ከሆን የሕብረታችን መዲና ትሆናለች ማለት ነው”።

“ዛሬ የፈጽምነው ተግባር ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ፣ ወልደ እና ለመንፈስ ቅዱስ ክብርና  እንድሁም በእግዚአብሔር ለምታመን ሕዝብ ሁሉ መልካም አገልግሎት ይሆን ዘንድ በእግዚአንሔርን እናት ከለላ ስም እንማጸናልን” በማለት መግለጫቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.