2016-02-08 16:04:00

በእቅድ የተያዘው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና የፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የግኑኝነት መርሃ ግብር


እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በሃገረ ኵባ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በሞስኮና መላ ሩሲያ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል መካከል ግኑኝነት እንደሚካሄድ የተሰጠው ዜና ዓለም አቀፍ ትኵረ የተሰጠው ከመሆኑም ባሻገር በቤተ ክርስቲያን ታሪክና በዓለም ታሪክ አቢይ ክስተት መሆኑ የተለያዩ የዜና አውታሮችና የታሪክ ሊቃውንት አስተያየት እየሰጡበት ሲሆን ይኽ በእቅድ ስለ ተያዘው የግኑኝነት መርሃ ግብር አስደግፈው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ግኑኝነት ለሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የምስራቅ ሥርዓት ለሚከተለዩት አቢያተ ክርስቲያን የሚንከባከብ ቢሮ ኃላፊ የዶመኒካውያን ገዳም አባል አባ ሃይቺንዝ ደስቲቨለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልስል፦ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና በመላ ሩሲያና የሞክስካ ፓትሪያርክ መካከል ግኑኝነት እንዲከናወን የተደረገው ጥረት የቆየና 25 ዓመት ያስቆጠረ የጋራ ጥረት ነው። ስለዚህ ባንድ ቀን የተወሰነ ሳይሆን ብዙ ዓመታት የፈጀ እቅድ ነው፣ ባለፉት የመጨረሻ ዓመታት ውስጥ ግኑኝነት እንዲረጋገጥ የሚደግፉ የጋራ ጥረቶች ስኬታማ እየሆኑ መጥተዋል፣ በተለይ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ቀን ወዲህ እየጎላ የመጣ አመርቂ ጥረት ነው። ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከተመረጡበት ቀን ጀምረው ከሳቸው ጋር ለመገናኘት ያላቸው ፍላጎት በመላ ሩሲያና ሞስካ ፓትሪያርክ የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሜጥሮፖሊታ ሂላሪዮን አማካኝነት የገለጡት ሲሆን፣ ሜጥሮፖሊታ ሂላሪዮን ግኑኝነቱ እንዲረጋገጥ አቢይ ሚና መጫወታቸውም በተደጋጋሚ በቅድስት መንበር ያካሄዱት ጉብኝት ያረጋግጠዋል ብለዋል።

እስካሁን ድረስ ጉዳዩን ያዘገየው ሌላው ሃይማኖቱን እንዲቀይር የሃይማኖት ቅስቀሳ እንዳይስፋፋ በሚል ስጋት መሆኑ በተደጋጋሚ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይታይ የነበረው ሁነት ነው።  ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም በኡክራይ ስላለቸው ከመላ ሩሲያና ሞስካ ፓትሪያርክ ጋር ውህደት ያላት በሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሥር የምትመራው ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለገዛ እራሱ ግኑኝነት እንዳይካሄድ በከፊሉ ሚና ነበረው፣ ሆኖም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሌላው ሃይማኖቱ እንዲቀይር የምታደርገው ቅስቀሳ አለ መኖሩ ግልጽ እየሆነ በመታየቱና መቼም ቢሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዓላማም ሃይማኖትን ማስቀየር አለ መሆኑ በመረጋገጡም ነው። ሰለዚህ ግኑኝነቱ ፍቅር መሠረት ያደረገ ነው። ለውህደት የሚደረገው የጋራው ጥረት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ሥር ትጠቃለል የሚል ሳይሆን የዚያ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ያለው ውህደት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን በሱታፌ እንዲኖሩት የሚል ቲዮሎጊያዊ አመክንዮ የሚከተል ነው ብለዋል።

ቀዳሚነት በጉባእያውነት የሚል መንፈስ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የሚያንጸባርቁት አመክንዮ በካቶሊካዊትና በቁስጥንጥንያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ለውህደት ታልሞ የሚደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት እያስገኘ መጥቷል። ሆኖም ቅድስት መንበር ከቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላት ግኑኝነት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች አቢያተ ክርስቲያን ጋር ለምታደርገው ግኑኝነት ሚዛን ይሁን አትልም፣ ቢሆንም ቅሉ የሚያግባባ ሥነ ቤተ ክርስቲያናዊ ቲዮሎጊያዊና ቅዱስ መጽሐፍና ሥነ ቤተ ክርስቲያናዊ መሠረት ያደረገ ሃሳብ ነው ብለዋል።

በኵባ ጉኑኝነት ከተከናወነ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፣ ወዳሪያን ሳይሆን ወንድማማቾች ናቸው፣ ግኑኝነቱም ይኸንን የሚያስተውል ነው። በካቶሊካዊትና በሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ሥነ ቤተ ክርስቲያን ሥነ ቅዱሳት ምሥጢራት በሚመለከቱ ርእስቶች አንድ አይነት አመለካከት ነው ያለው። ይኽ ደግሞ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለውህደት ታልሞ ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.