2015-10-02 16:07:00

ሶሪያ፦ የሩሲያ አየር ኃይል በጸረ ርእሰ ስዩም እስላማዊ ሃገር ጥቃት ተሳታፊነት


እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ. የሩሲያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሶሪያ ርእሰ ብሔር አሳድ ሩሲያ በጸረ እስላማዊ አገር ታጣቂ ኃይሎች ላይ በሚወሰደው በወታደራዊ ጥቃት ትተባበራቸው ዘንድ ያቀረቡት ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ከሰጠበት ወዲህ የሩሲያ አየር ኃይል በሶሪያ በሚገኘው ሓማና ኢድሊብ ክልል በሚቆጣጠረው የተለያዩ ጅሃዳውያን ታጣቂ ኃይሎችን የሚያቅፈው ታጣቂ ኃይል ላይ ጥቃት መጣላቸው ሲነገር፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በውጭ ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ጆን ከርይ በኩል የሩሲያው የአየር ኃይል ጥቃት በጸረ ርእሰ ብሔር አሳድ ታጣቂ ኃይሎች ላይ የተጣለ ነው ሲሉ ለሰነዘረውና የሶሪያ አመጽያን ኃይል ተጠሪ ያስተጋባው ወቀሳ የሩሲያው መንግሥት ጥቃቱ ጸረ ርእሰ ስዩም እስላማዊ አገር ታጣቂው ኃይል ላይ ያነጣጠረ ነው በማለት በውጭ ጉዳይ ሚኒ. ላቭሮቭ በኩል ምላሽ ሰጥቶበታል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ሁለቱ አገሮች በጸረ እስላማዊ አገር ታጣቂ ኃይሎች ትግል በመከላከያ ኃይሎቻቸው ደረጃ ትብብር እንዲኖር የሚል ፍላጎት መንጸባረቁ ሲነገር፣ የሩሲያው መንግሥት የአገሩ አየር ኃይል ስለ ሚሰነዝራቸው ጸረ ርእሰ ስዩም እስላማዊ አገር ታጣቂው ኃይል ጥቃቶች በተመለከተ አመሪካን ጨምሮ መረጃው ለሚገባቸው አገሮች ለማቅረብ የሚሻ መሆኑም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ በኩል አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.