2015-05-22 16:53:00

ናይጀሪያ፦ ማኅበራዊ እራስ ወዳድነት ለመቃወም የብፁዕ አቡነ ካይጋመ ጥሪ


የናይጀሪያ ሕዝብ ራስ ወዳድነትና የራስ ጥቅም ማስቀደም ከሚለው አመለካከት ወደ የአገርና የሕዝብ እርሱም የጋራ ጥቅም ማስቀደም ወደ ሚለው አመለካከት እንዲለወጥ፣ ሕዝብ የመረጠው መንግሥት አገርና ሕዝብ በተገባና ብቃት ባለው መልካም አመራር እንዲያስተዳድር በናይጀሪያ የጁባ ሰበካ ረዳት ጳጳስ እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለተሰየሙት ለክቡር አባ ደኒስ ቺዲ ኢሲዞህ ማዕርገ ጵጵስና ለመስጠት የቅዱሳት ሚሥጥራትና ሥርዓተ አምልኮ ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ልሂቅ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሲስ አሪንዘ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ 56 የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት በናይጀሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ አውጉስቲን ካሱጃ ታጅበው የመንግሥት ተወካዮችና ምእመናን የተሳተፉበት በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ የናይጀሪያ የጆስ ሊቀ ጳጳሳትና የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኢግናዚዩስ ካይጋመ ባሰሙት ስብከት ጥሪ ማስተላለፋቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ምግባረ ብልሽት ሙስና፣ ሃይማኖታዊ አክራሪነት የአገር በሽታ ናቸው

ብፁዕ አቡነ ካጋመ የአገርና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም በሚል ጥሪ ላ ያነጣጠረ ባስደመጡት ስብከት ናይጀሪያ እጅግ የሚያሰቃየው እየተስፋፋ ያለው በሽታ ምግባረ ብልሽት ሙስና ሃይማኖታዊ አክራሪነት መሆኑ ጠቅሰው፣ ይኽ የአገርና የሕዝብ እድገት ጠፍሮ፣ ብሔርተኝነት አክራሪነትል የአመራር አካላት ውድቀት የሚያስፋፋው እክል ለመቅረፍ ፍቱን መንገድ የአገርና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም የሚል ክብር መከተል ነው። ይኸንን ግምት በመሰጠት ማኅበረ ክርስቲያን ነቢያዊ ድምጽ በመሆን ስለ አገር ከፖለቲካው ውዝግብና ከነዳፊ ተግባር ተቆጥበው የእርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህል በማነቃቃት ለእግዚአብሔር ክብር ስም የአገር ጨውና ብርሃን ሆነው እንዲገኙ አደራ እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እምቢ ለቅድመ ፍርድና ለጥላቻ መንፈስ፣ ስለ አገር እርቅና አንድነት መጸለይ

አገር ለመገንባት የጥላቻ መንፈስ በጎሳዎችና በፖለቲካ አካላት መካከል የሚታየው በክርስቲያኖች መካከልም ሳይቀር የሚታየው የመጠራጠር መንፈስ በመዋጋት ለይቅር መባባል፣ ለመደጋገፍ ለመቀራረብ ባህል ሁሉም ተግቶ፣ እምቢ ለቅድመ ፍርድና ለጥላቻ መንፈስ እንዲል አሳስበው፣ ስለ አገር እርቅና አንድነት ማኅበረ ክርስቲያን እንዲጸልይ አደራ እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.