2015-04-17 16:07:00

የእግዚአብሔር ጥበቃና ድጋፍ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ነግህ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ያደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ፣ በአገረ ቫቲካን እመ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ነዋሪነታቸው ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተወለዱበት

ዕለት መሆኑ አስታውሰው፣ እግዚአብሔር ለሰጣቸው 88ኛው ዓመት ልደት ከሳቸው ጋር ሆነን ጌታን እናመስግን እግዚአብሔር ማለቂያ የሌለው ኃሴት እንዲያድላቸውና እንዲያቅባቸው ሰለ እሳቸው እንጸልይ በማለት አስታውሰው የመልካም የልደት ዓመት ምኞት ቃል ስለ  በነዲክቶስ 16ኛ እሰምተው የዕለቱ ቅዳሴም ስለ እሳቸው እግዚአብሔር ለማመስገን በሚል የጸሎት ሃሳብ የተመራ መሆኑ መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.