Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ስብከቶች

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "የእግዚኣብሔርን በጎች በትህትናና በፍቅር መገልገል ይገባል"ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 25/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ኢየሱስ በጎቹን ለሐዋሪያው ጴጥሮስ በአደራነት በመስጠት እነዚህንም የእግዚኣብሔር በጎች በትህትናና በፍቅር እንዲመራቸው በአደራነት ስጦት ነበር ብለዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱ በላቲን ስርዐተ አምልኮ አቆጣጠር በተነበበውና ከዩሐንስ ወንጌል 21፡15-19 በተወሰደው ኢየሱስ ጴጥሮስን ተወደኛለህን? ብሎ ሦስት ጊዜ እንደ ጠየቀው በሚያወሳው ምንባብ ዙሪያ ባጠነጠነው ስብከታቸው እንደ ገልጹት በወቅቱ በኢየሱስ እና በጴጥሮስ መካከል የነበረው ውይይት በጓደኝነት መንፈስ የተደረገ ውይይት እንደ ነበረም ጠቅሰው ኢየሱስ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ “ትወደኛለህን?” የሚል ጥያቄን ካቀረበለት ቡኃላ በጎቹን ለጴጥሮስ በአደራ መልክ አስረክቦታል ብለዋል።

“ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ ቡኃላ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል “አላውቅህም” ብሎ ሦስት ጊዜ ክዶት ለነበረው በጣም ኅጢያተኛ ለሚባል ሰው “አንተ ከእነዚህ ሁሉ አብልጠህ ተወደኛለህን?” በማለት ጥያቄ አቅርቦለት እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ በጣም ኅጢያተኝ የሚባለውን ሰው ነበር የመረጠው” ብለዋል።

የእግዚኣብሔር ሕዝብ እረኛ እንዲሆን የተመረጠው ኅጢያተኛና ከዳተኛ የተባለ ሰው ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ ጴጥሮስ በጎቹን በፍቅር እንዲመራቸው ፈልጎ እንደ ነበረ እንድናስብ ያደርገናል ብለዋል።

“ራሳችንን ቀና አድርገን በመጓዝ እንደ አንድ ጨቋኝ ሰው መሆን በፍጹም የለብንም! አዎን በኅጥያት እና በስህተቶችም ውስጥ ሆነን የእረኝነት ተግባሮቻችንን ኢየሱስ ራሱ እንዳደረገው በትህትና እና በፍቅር መፈጸም ይገባናል። ጴጥሮስ በወቅቱ በነበረው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ “ጌታ ሆይ እንደ ምወድህ አነተ ራስ ታውቃለህ አለው” በስህተት እና በደካማነት ውስጥ ቢሆንም እንኳን ኢየሱስን እንደ ሚወድ ገለጸ። ለምንድነው እርሱ ኢየሱስ በጎችህን ጠብቅ ከማለት ይልቅ ቤጎቼን ጠብቅ ያለው? ጴጥሮስ ኢየሱስን ከወደደ በጎቹንም እንደ ሚወድ እና በጎቹም የእርሱ እንደሚሆኑ ለማሳየት ፈልጎ ነው”።

ኢየሱስ ለሞት ተላልፎ በተሰጠበት ወቅት ጴጥሮስ ኢየሱስን ክዶት እንደ ነበረ በድጋሚ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ኢየሱስን ክዶት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን “አንተ ሕያው የሆነው የእግዚኣብሔር አንደኛ ልጁ የሆንክ ክርስቶስ ነህ” በማለት በእርግጠኛነት ስለ ኢየሱስ ጌታነት መስክሮ እንደ ነበረም ተቅሰው ኢየሱስን ሦስት ጊዜ በካደበት ወቅት ኢየሱስ ትኩር ብሎ ሲመለከተው መራር የሆነ ለቅሶ ውስጥ ገብቶ እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

“በቀጣይነትም ጴጥሮስ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ለጌታ አገልግሎት በማዋል ኢየሱስ የገጠመው ዓይነት የመስቀል ላይ ሞት ገጥሞት ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ አገልግሎቱ በምንም ዓይነት መልኩ ሳይኩራራ “እኔም እንደ ጌታዬ የመስቀል ላይ ሞት ይገባኛል” በማለት ተገልብጦ ተሰቅሎ መሞቱን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ዛሬ እኛ ኢየሱስ እና ጴጥሮስ ካደረጉት ውይይት ጌታ ራሳችንን ዝንቅ አድርገን መጓዝ እንዳለብን እንደ ሚመክረን መረዳት እንችላለን፣ ራችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ መብት የሚሰጠን እግዚኣብሔር ነው፣ ነገር ግን ራሳችንን ዝቅ ማድረግ ኅጢያተኞች መሆናችንን እና ጌታ የሆነው ኢየሱስ ብቻ ነው፣ እኛ ደግሞ የእርሱ አገልጋዮች መሆናችንን እንድንረዳ ያስችለናል ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።