Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ክርስትያኖች የጌታን ፈልግ በመከተል ፍቅር ምን ማለት እንደ ሆነ ለመረዳት ይችላሉ።


ክርስትያኖች የጌታን ፈልግ በመከተል ፍቅር ምን ማለት እንደ ሆነ ለመረዳት ይችላሉ። ይህንን ቀደም  የተናገሩት ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሲሆኑ፣ ይህንምም መልእክት ያስተላለፉት በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 13/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ ተመስርተው ካደረጉት አስተንትኖ የተወሰደ ነው።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ ካደረጉት አስተንትኖ ባሻገር በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ በአዲስ መልክ የተቀሰቀስው ደም አፋሳሽ ጦርነት ያበቃ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸው የተጠቀሰ ሲሆን በማከልም በመጭው ሰኔ 22/2009 ዓ.ም. የቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ አመታዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት ወቅት ከተለያዩ አህጉራት ለተውጣጡ 5 አዳዲስ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግ እንደ ሚሰጣቸው ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

“ለክርስትያኖችም ቢሆን ፍቅር ምን ማለት እንደ ሆነ ማወቅ፣ ለሌሎች መልካም ነገሮችን መመኘት መቼም ቢሆን ቀላል ነገር አይደለም በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የኢየሱስን ፈለግ በመከተል እና በእርሱ ጸጋ ታግዘው በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የተሰጠውን የፍቅር ትርጉም መረዳት ግን ይችላሉ” ብለዋል።

በእለቱ በተነበበው ከዩሐንስ ወንጌል 14፡15-21 በተወሰደው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የመጨረሻውን ርት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከተቋደሰ ቡኃል “ወላጅ እንደ ሌላቸው ሕጻናት ብቻችሁን አልተዋችሁም” በማለት ቃል ገብቶላቸው እንደ ነበረ ያስታውሱት ቅዱስነታቸው የእውነት መንፈስ የሆነውን “አጽናኙን መንፈስ ቅዱስ” እልክላችዋለው ብሎ ቃል ገብቶላቸው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰው ይህም መንፈስ ቅዱስ “የክርስቶስ ዳግም መምጣትን በደስታ” እንዲያውጁ ይረዳቸውል ብለዋል።

“ይህንን የክርስቶስ ቃል በማስተንተን ዛሬ እኛ በእምነት አጋዥነት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከአብ እና ከወልድ ጋር ሕብረት ያለን ሕዝቦች እንደ ሆንንን እንረዳለን። ይህም የሕብረት ምስጢር የቤተ ክርስትያን የማይነጥፍ ተልዕኮዋ ምንጭ ነው፣ ይህንንም ቤተ ክርስትያን እውን የምታደርገው በፍቅር አማክይነት ነው ብለዋል።

ምቀኝነት እና መከፋፈል የቤተ ክርስትያንን ገጽታን የሚያጠለሹ ነገሮች ናቸው በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ፍቅር ግን ኢየሱስን እንድናውቀው ያደርገናል “እግዚኣብሔርን እና ባለንጀራን መውደድ የሚሉት ቃላት በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ተጠቅሰው የሚገኙ ዋነኛ የሚባሉ ትእዛዛት መሆናቸውን ቅዱስነታቸው ጠቅሰዋል።

ጌታ ቅዱስ ወንጌል ለሚያቀርብልን የፍቅር ጥሪ በርኅራኄ መልስ እንድንሰጥ አደራ ይለናል ያሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም በሕይወታችን ውስጥ ሁሉ እግዚኣብሔርን በማስገባት እና ራሳችንን ወንድሞቻችንን በተለይም ደግሞ ከፍተኛ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እና መጽናናትን ለሚሹ ሰዎች ሁሉ ልዩ ትኩረት ሰጥተን  ለማገልገል ዝግጁ መማድረግ እንደ ሚኖርብንም ያሳስበናል ብለዋል።

“አንድ ቀላል የማይባል ባሕሪ አለ፣ ለክርስትያኖችም ቢሆኑ በቀላሉ የሚገኙት ነገር አይደለም፣ ይህም መውደድ ምን ማለት መሆኑን የመረዳት ባሕሪ ነው” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ይህንን ባሕሪ የኢየሱስን አብነት በመከተል እና በእርሱ ጸጋ በመታገዝ እውን ማድረግ ይቻላል ብለዋል። አንድ አንዴም በተቃራኒው ትዕቢት፣ ምቀኝነት፣ መከፋፈል የመሳሰሉ ክፉ ነገሮች ውብ የሆነውን የቤተ ክርስትያን ፊት የምያጠለሹ ነገሮች ናቸው ካሉ ቡኃላ አንድ የክርስትያን ማሕበረሰብ   በክርስቶስ ፍቅር ተሞልቶ መኖር ይኖርበታል ካሉ ቡኃላ በተቃራኒው ክፉ የሚባሉ ነገሮች ግን አንካሶች ሁነን እንድንኖር ያደርጉናል፣ እኛንም አንድ አንዴ እነዚህ ክፉ ነገሮች ያታልሉናል ብለዋል።

የዚህ ጥቃት ሰላባ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ድክመትን የሚያሳዩ ሰዎች መሆናቸውን በመጥቀስ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ ከቤተ ክርስትያን ይርቃሉ ይህንንም የምያደርጉበት ምክንያት ተቀባይነት የሌላቸው፣ ሰው እንደ ማይረዳቸው እና እንደ ማይወዳቸው ሆኑ ስለ ሚሰማቸው ነው ብለዋል።

ፍቅር ቅጽበታዊ በሆነ መልኩ ለአንድ ክርስትያን የሚሰጥ ስጦታ አይደለም በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእየለቱ የፍቅርን ጥበብ መማር ያስፈልጋል፣ በእየለቱ በታላቅ ትዕግስት የክርስቶስን የፍቅር ትምህርት መከታተል ያስፈልጋል፣ በእየእለቱ ይቅርታን ማድረግ እና ኢየሱስን መመልከት ያስፈልጋል፣ ጠበቃችን  እና አጽናኛችን በሆነው፣ ኢየሱስ በሚልክልን መንፈስ ቅዱስ ታግዘን ግን እውን ማድረግ እንችላለን ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።