Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ፍትሕና ሰላም

ማንኛውም ዓይነት ኢኮኖሚ የሰው ልጆችን መብት እና ማሕበራዊ ዋትናን ያረጋገጠ ሊሆን ይገባል።


የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮን የተመለከተ በቀዳሚነት የተጻፈው ሐዋሪያዊ መልእክት እንደ አሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1891 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ሊዮ 13ኛ አማክይነት የተጻፈው በላቲን ቋንቋ Rerum Novarum በአማሪኛው የፖሌትካ ለውጥ በሚል አርዕስት የታተመው እና በወቅቱ በማንሰራራት ላይ በነበረው የእንዱስትሪ አብዮት ምክንያት ጉልበታቸው ያለ አግባቡ ሲበዘበዝ ለነበሩ ሠራተኞች ጥብቅና የቆመና ሠራተኞች ተገቢው እንክብካቤ ይደረግላቸው ዘንድ የሚያሳስብ ሐዋሪያው መልእክት እንደ ነበረ ይታወሳል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1991 ዓ.ም. በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ የዚህን ሐዋሪያዊ መልእክት 100ኛ አመት ለመዘከር በማሰብ Centesimus Annus መቶኛው አመት በሚል አርዕስት ሐዋሪያዊ መልእክት ጽፈው እንደ ነበረም ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት የእንዱስትሪን መስፋፋት ተከትሎ በዓለማችን የሚታየውን ያልተመጣጠነ እድገት እና የሰራተኞች መብት ጥሰት የሚነቅፍ እና ማሕበራዊ ዋስትናቸውን ለማስከበር በማሰብ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ Centesimus Annus “ቼንትዚሙስ አኑስ” የተሰኘ አንድ ተቋም ባለፈው አመት ማቋቋማቸው ያታወቃል።

በዚሁ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም 10/2009 ዓ.ም. በዚሁ ቼንቴዚሙስ አኑስ በተሰኘው ተቋም በተዘጋጀውን አውደ ሪዕይ ከተለያዩ 18 ሀገራት የተውጣጡ 300 ሰዎች መሳተፋቸውም ተገልጹዋል። ይህንን አወደ ርዕይ አስመልክቶ ከሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ ጋብርኤላ ቼራዞ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉት የተቋሙ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ጆቫኒ ማርሴጒኤራ የማሕበሩን ተግባራት አስመልክተው እንደ ገለጹት “ይህ ቼንቴዚሙስ አኑስ የተሰኘው ተቋማችን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን አስተምህሮ በመከተል በተለይም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚታየውን ያለተማጣጠነ እድገት እና የሰራተኞች መብት ጥሰትን በመከታተል፣ ማጋለጥ፣ የማነቃቂያ ስብሰባዎችን ማዘጋጀት እና በተጨማሪም ማንኛውም ኢኮኖሚ የሰራተኞች መብት እና ማሕበራዊ ዋስትናቸው አቅፎ የያዘ ሊሆን የገባል የሚል አመለካከት የሚያራምድ ተቋም እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ የሚታየው የቴክኖሎጂ እድገት በሥራ ሕልውና ልይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መምጣቱን የገለጹት ፕሮፌሰር ጆቫኒ ማርሴጒኤራ ቴክኖሎጂ እየተራቀቀ በሚሄድባቸው ወቅቶች ሁሉ አንድ የቴክኖሊጂ ውጤት የብዙ ሰዎችን ሥራ ተክቶ የምሰራት ብቃት ስላለው በዚህም የተነሳ የታላላቅ ፋብሪካዎች ባሌቤቶች ሰዎችን ቀጥሮ ከማስራት ይልቅ ተክኖሎጂን መጠቀም እየጀመሩ በመምጣታቸው የተነሳ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ከፍተኝ የሆነ የሥራ አጥነትን ፍጥሩዋል ብለዋል።

የሰው ልጆች ሕገወጥ ዘውውር ውስጥ በመሳተፍ በዚህ ወንጀል ምክንያት ገንዘብ እያፈሱ የሚገኙ የተደራጁ ወንጀለኞ የሚፈጽሙዋቸው ሕገወጥ ተግባራት በሁልተኛ ደረጃ የሰራተኞችን ሕልውና እየተፈታተን አየሚገኘው ጉዳይ ነው በማለት አስተያየታቸውን የቀጠሉት ፕሮፌሰር ጆቫኒ ማርሴጒኤራ በዚህም ምክንያት ለአቅመ አዳም እና ሔዋን ያልደረሱ ሕጻንትን ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች ለሕገወጥ ስራ በመዳረግ ጉልበታቸው እየተበዘበዘ እንደ ሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል። የማሕበራችን ዋንኛው ዓላማ እነዚህን ተግዳሮቶች መከላከል እና ከተቻለም አደጋውን ከነአካቴው ማጥፋት፣ ካልሆነም ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንዲቀንሱ የማድረግ ተልዕኮ እንዳለውም ገጸው በማንኛውም የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ሊሰጠው የሚገባው ትርፍ ማጋበስ ሳይሆን መተኪያ የሌላቸው የሰው ልጆች ሊሆኑ ይገባል የሚል ከፍተኛ አቋም እንዳላቸውም ጨምረው ገልጸዋል።