Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ማሪያም መቅደላዊት የተስፋ ሐዋሪያ ናት!


ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻን በማስከተል ርዕሰ ሊቃነ ጵጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 9/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተማሩትን ትምህርተ ክርስቶስ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳማጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በነዚህ ስማንታት የማቀርብላችሁ አስተንትኖ ምኅዋሩን በፋሲካ ምስጢር ዙርያ በማድረግ የሚሽከረከር ነው። በወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ዛሬ የኢየሱስን ከሙታን መነሣት በቅዳሚነት የመሰከረችውን የመቅደላዊት ማሪያምን ታሪክ እንመለከታለን። ቀጥሎ የነበረው የሰንበት ቀን በመሆኑ የተነሳ ልማዳዊውን የቀብር ስነ-ስርዓት መፈጸም አልተቻለም ነበር። በዚህም ሐዘን በተሞላበት እለት ሴቶቹ ጎህ ሲቀድ የኢየሱስን በድን ሽቶ ለመቀበት ወደ መቃብሩ ሥፍራ ሄዱ። ቀድማ የደረሰችው ግን ከሐዋሪያቶቹ አንዷ የነበረች፣ ከገሊላ አንስቶ እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ ኢየሱስን የተከተለችው፣ ቤተ ክርስትያን በተመሰረትቸበት ወቅት በቀዳሚነት አገልጋይ የነበረቸው ማሪያም መቅደላዊት ነበረች። ወደ ቀብር ሥፍራ ያደረገችው ጉዞ ብዙ ሴቶች በታማኝነት በሞት ያጡዋቸውን ወዳጆቻችውን ለመጎብኘት ወደ መቃብር ስፍራ ይሄዱ እንደ ነበረ ያመለክታል። ይህም በሞት አማካይነት ሊበጠስ የማይችል ሐቀኛ የሆነ ግንኙነት እንዳለ እና ያ ተወዳጅ የሆነ ሰው በሞት ቢለይም እንኳን ለዘለዓለም መልካም ይሆን ዘንድ ያላቸውን ምኞት ያሳያል።

ቅዱስ ወንጌላችን (ዩሐንስ 20፡1-2,11-18) እንደ ሚገልጸው ማሪያም መቅደላዊት በቀላሉ ጉጉት የምያድርባት ሴት አለመሆኗን ያስረዳል።  በእርግጥ በመጀመሪያ የቀብር ሥፍራውን ካየች ቡኃላ ደቀ ማዛሙርቱ ተደብቀው ወደ ሚገኙበት ሥፍራ ቅር በተሰኘ ስሜት በመሄድ የመቃብሩ ክዳን የነበረው ድንጋይ ተንከባሎ እንዳየች ነገረቻቸው፣ እርሷ በውቅቱ በቀዳሚነት በቀላሉ አስባው የነበረው መላምት አንድ ሰው መጥቶ የኢየሱስን አስክሬን እንደ ወሰደ ነበር የገመተችው። ማሪያም መቅደላዊት በቀዳሚነት ያበሰረችው የኢየሱስን ትንሳኤ ሳይሆን መላው ኢየስሩሳሌም በእንቅልፍ ውስጥ በነበረበት ወቅት ያልታወቁ ሰዎች አስክሬኑን መሰራቃቸውን ነበር።

በመቀጠልም ቅዱስ ወንጌል ማሪያም መቅደላዊት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ቀብር ሥፍራ መሄዷን ይተርካል። ትሄዳለች ትመለሳለች በቀላሉ ማመን አልቻለችም ግትር የሆነች ሴት ነበረች። በሁለተኛው ደረጃ ያደረገችው ጎዞ ግን እንደ መጀመሪያው ፍጣን አልነበረም፣ በጣምም ከባድ ነበረ። ማሪያም መቅደላዊት ሁለት ጊዜ ነበር ወደ ጥልቅ ሐዘን ውስጥ የገባችው፣ በመጀመሪያ በኢየሱስ ሞት የተነሳ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቃላት ለማብራራት በምያዳግት ሁኔታ በጠፋው በኢየሱስ በድን ምክንያት ነበር። ዐይኖቹዋ በእንባ ተሞልተው አጎንብሳ ወደ መቃብሩ ውስጥ ትመለከት በነበረችበት ወቅት ባልጠበቀችው መንገድ እግዚኣብሔር በአስገራሚ ሁኔታ ተገለጸላት። ማሪያም መቅደላዊት ከጎኑዋ የነበሩትን ሁለት መላእክት መመልከት በለመቻልዋና ከጎኑዋ ቆሞ የነበረው ሰው የመቃብሩ ስፍራ ጠባቂ ሰራተኛ መስሉዋት ስለተሰማት በዚህ ምክንያት የተነሳ ወንጌላዊው ዩሐንስ ማሪያም መቅደላዊትን በብዢታ ውስጥ እንደ ነበረች አድርጎ ነበር ያቀረባት ነገር ግን በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ሊዘነጋ የማይችለው “ማሪያም” የሚለው ስሟ በተጠራ ጊዜ ነበር የነቃችው።

ይህ በወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ግልጸት በግለሰብ ደረጃ የሆነ ግልጸት መሆኑን ማሰብ እንዴት ያስደስታል! ሁል ጊዜም ቢሆን የምያውቀን፣ በችግር አስጥ በምንሆንበት እና ግራ ስንጋባ የሚመለከተን፣ ስናዝን አብሮ የሚያዝን፣ በየስማችን የሚጠራን አንድ አካል አለ።  ይህንንም በብዙ የወንጌል ገጾች ላይ የምናገኘው እውነታ ነው። በኢየሱስ ዙሪያ እግዚኣብሔርን ለማግኘት የሚፈልጉት ብዙ ሰዎች አሉ። የምያስገርመው እና የሚያስደንቀው ነገር ግን ከእኛ በጣም ቀደም ብሎ ለሕይወታችን የሚጨነቅ፣ ችግራችንን ለመፍታት የሚፈልግ፣ በየስማችን የሚጠራን የእያንድ አንዳችንን ፊት የሚያውቅ እግዚኣብሔር ሊፈልገን ይወጣል። እያንድ አንዱ ሰው እግዚኣብሔር በዚህ ምድር ላይ የሚጽፈው የፍቅር ታሪክ ነው። እየአምድ አምዳችን የእግዚኣብሔር የፍቅር ታሪክ ነን። እያንድ አንዳችን በየስማችን ይጠራናል፣ ከነስማችን ያውቀናል፣ ይመለከተናል፣ ይጠብቀናል፣ ይቅር ይለናል፣ ይታገሰናልም። እያንድ አንዳችን ይህ ተመኩሮ አለን።

ኢየሱስ “ማሪያም” ብሎ በጠራት ወቅት ሕይወቱዋ ተቀየረ፣ ይህም በኢየሱስ የቀብር ስፍራ የተሰማው ድምጽ የእያንዳንዳችን እጣ ፈንታ ነው። ወንጌላዊያኑ ማሪያም ስሟ በተጠራ ጊዜ የነበራትን ደስታ በወንጌል ውስጥ ገልጸውታል፣ የኢየሱስ ትንሣኤ አንድ ጊዜ ተመስክሮ የሚያልቅ ነገር ሳይሆን ሁል ጊዜ በሕይወታችን የምንመሰክረው ጉዳይ ነው። የእኛ እግዚኣብሔር ሕልመኛ ነው፣ ዓለማችን መነፈሳዊ ለውጥ ያመጣ ዘንድ ይመኛል፣ ይህንንም በልጁ ከሙታን መነሳት እውን አድርጎታል። ማሪያም መቅደላዊት ኢየሱስን ልታቅፈው ፈልጋ ነበር፣ ነገር ግን እርሱ አሁን ሰማያዊ በመሆኑ የተነሳ ወደ ወንድሞቹ ማለትም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄዳ ይህንን የትንሳኤ ዜና እንድታበስር ነገራት። ኢየስስን ከመገናኘቷ በፊት እርኩስ መንፈስ ተጠናውቱዋት የነበረች ሴት አሁን ደግሞ የታላቁ እና የአዲሱ ተስፋ መስካሪ ሆነች። የእርሱ አማላጅነት እኛም የዚህ ዓይነት ተመኩሮ እንዲኖረን ይርዳን፣ በለቅሶዋችን ወቅት፣ በተረሳንበት ወቅት፣ በየስማችን የሚጠራንን የክርስቶስን ድምጽ ለመስማት እና በእርሱ የሚገኘውን ደስታ  “ጌታን እኮ አየሁት!” እንደ ከዚህ ቀደም ዓይነት ሰው አይደለሁኝም እኔ ኢየሱስን በማየተ የተነሳ የሕይወት መንገዴን ቀይሪያልለሁኝ፣ የቀየርኩትም ኢየሱስን በማየቴ የተነሳ ነው ብለን ለማወጅ ያብቃን። ይህ ነው ኃይላችን ይህ ነው ተስፋችን። አመሰግናለሁ።