Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለኅሙማን፥ ሕይወትን ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚወከፍ ዕጹብ ድንቅ ጸጋ አድርጎ መኖር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመቁጠሪያይቱ ቅድስተ ማርያም ዘፋጢማ ቅዱስ ሥፍራ ለፍራንቸስኮ ማርቶና ለጃቺንታ ማርቶ ቅድስና ለማወጅ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁ ለየት ባለ መልኩ ኅሙማንን በማሰብ ለኅሙማን ምእመናን፥

“የቤተ ክርስቲያን እጹብ ድንቅ ጸጋ መሆናችሁ አውቃችሁ መኖር እንጂ በደረሰባችሁ ህመም ምክንያት አትፈሩ። በዚያ ስለ እናንተና ከእናንተ ጋርም በሚያረገው ፀሎት ላይ አመኔታው ይኑራችሁ፡  ከሁሉም ሥፍራና በሁሉም አካባቢ ስለ እናንተ ጸሎት ወደሰማይ ያርጋል፡አባት የሆነው እግዚአብሔር እናንተን ፈጽሞ አይዘነጋም”።

እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ከመሥዋዕተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ በተከናወነው በቅዱስ ቁርባን ፊት የአስተንትኖናን የቡራኬ ሊጡርጊያ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ከዮሓንስ ወንጌል ምዕ. 12 የተወሰደውን ወንጌላዊ ምንባብ ተንተርሰው ባሰሙት ስብከት፥

“የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፡ ብትሞ ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች” (ቍ. 24) የሚለውን  ጠቅሰው “በመስቀል ስናልፍ በዚያ መስቀል ቀድሞን ጌታችን እየሱ ክርቶስ እንዳለፈ ታምነን፡ በህማማቱ ውስጥ የሁላችን ህማማትን በማኖርና የራሱ በማድረግ ስቃያችንን ሁሉ በራሱ ላይ አኑሯል። ኢየሱስ ስቃይ ምን ማለት እንደሆነ ያውቀዋል። ስለዚህ እኛን ይረዳናል። ልክ ከቅዱስ ፍራንቸስኮ ማርቶና ቅድስትን ጃቺንታ ማርቶ ጋር እንዲሁም በሁሉ ዘመናት ከነበሩት ቅዱሳን ጋር እንዳደረገው ሁሉ ኃይሉን ይሰጠናል”።

ያሉት ቅዱስ አባታችን አክለው፥

“ጴጥሮስ በእየሩሳሌም በወህኒ ቤት ተቀፍድዶ እያለ ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ እንደጸለየች ሁሉ ዛሬም የሚሰቃዩትን ሁሉንም በማሰብ ቤተ ክርስቲያን ትጸልያለች። ጌታም መጽናናቱን ይሰጣል። በፊታችን ይኸውን በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ኢየሱስ ህልው ነው። በዚህ ምሥጢር በሥውር ያለው በእያንዳንዱ በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ቁስል አማካኝነትም ኅልው ነው። በሚስቃዩት ውስጥ ኅልው ነው”

እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው፥ “ዛሬ ቅድስት ድንግል ማርያም ልክ የዛሬ አንድ መቶ ዓመት በፊት በዚህ ሥፍራ ለሦስቱ እረኞች፥ ‘ገዛ እራሳችሁን ለእግዚአብሔር ልትሰጡ ትፈልጋላችሁን? ‘አዎን እንፈልጋለን’ በማለት መልስ የሰጡበት ጥያቄ። ለእኛ ታቀርብልናለች”።

“በተለያየ ህመም የተጠቃችሁ የምትሰቃዩ ውዶቼ፥ ሕይወታችሁ እንደ ትልቅ ጸጋ ኑሩት። ገዛ እራሳችሁን ትብብርና አዛኝ ልብ ተመጽዋች አድርጋችሁ ማሰብ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን በሙላት ሱታፌ ያላችሁ እንደሆናችሁ ማወቅ ይገባችኋል። ከማንኛውም ቃልና ቋንቋ በላይ እንደበት ርቱዕ በሆነው ጽሞናችሁ አማካኝነት ጸሎታችሁና በዕለታዊ ስቃያችሁ ለዓለም ድኅነት ከተሰቀለው በኢየሱስ ኅማማት ጋር ሱታፌ እንዳላችሁ የተረጋገጠ ነው። ይኸንን ስቃይ ተቀብላችሁ እንደ ፈቃድህ ይሁን ብላችሁ በትእግስት ከዚህ በዘለለ መልኩም በኃሴት በመኖር የምትሰጡት ምስክርነት ለእያንዳንዱ ማኅበረ ክርስቲያን ዓቢይ መንፈሳዊ ሃብት ነው”

ብለው፥ “የቤተ ክርስቲያን ብርቅና ክብር ያለው ሃብት ናችሁና ባደረባችሁ ህመም ሃፍረት እንዳይሰማችሁ አደራ በእናንተ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ኅማም ለብዙዎች ድህነት መስዋዕት ነውና”  ሲሉ የለገሱት ስብከት ማጠቃለላቸው አስታወቁ።