Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ንግግሮች

ቅዱስነታቸው በግብፅ የሚያደርጉትን ሐዋሪያዊ ጉብኝት አስመልክተው ያስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጪው አርብ በሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም. የሁለት ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ግብፅ እንደ ሚጓዙ መግለጻችን ያታወሳል። ይህንን ከአንድ ቀን ቡኃላ የሚያደርጉትን ሐዋሪያዊ ጉዞ አስመልክተው በታላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 17/2009 ዓ.ም. የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክታቸው እንደ ገለጹት “ዓለማችን በአሁኑ ወቅት ሰላም፣ ፍቅር እና ምሕረት ያስፈልጓታል” ማለታቸውም ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ያስተላለፉትን መልእክት የጀመሩት በአረብኛ ቋንቋ “አሰላም አሌኩም” (ሰላም ለእናንተ ይሁን) በማለት ነበር።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉትን የቪድዮ መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።  

የዚህን መልእክት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የዓለም የስልጣኔ ምንጭ፣ የአባይ ወንዝ ስጦታ እና እንግዳ ተቀባይ፣ አበው እና ነቢያት የኖሩባት፣ ደግ እና አዛኝ የሆነ ሕዝቦች የሚገኙባት ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚኣብሔር ድምፁን ያሰማባት ያችን ተወዳጅ የሆነች ሀገር በቅርብ ቀን ለመጎብኘት በመሄዴ ከልብ የመነጨ ደስታ እና ምስጋና አቀርባለሁኝ።

ከሁለት ዓመታት በፊት የንጉሥ ሂሮደስን ዛቻ በመፍራት በስደት ወደ እዚያ የሄዱንት የቅድስት ቤተሰብን የተቀበለችሁን ሁገር  እንደ ጓደኛ፣ እንደ የሰላም መልእክተኛ እና እንደ ነጋዲ ሆኜ ለመጎብኘት ወደ እዚያ ለመሄድ በመነሳቴ እውነተኛ ደስታ ይሰማኛል። የቅዱስ ቤተሰብ የጎበኛትን ሀገር እኔም ለመጎብኘት በመዘጋጄቴ ክብር ይሰማኛል።

ለሁላችሁም ሰላምታን በማቀርብበት በአሁኑ ወቅትኡም ኢል ዱኛ’ (በአማሪኛው የዓለም እናት) እያላቹዋት የምትጠሩዋትን ግብፅ እንድጎበኝ ስለጠራችሁኝም አመሰግናለሁ።

ለሀገሪቷ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት፣ ለቅዱስነታቸው ለፓትሪያርክ ቴዎድሮስ ሁለተኛ፣ ለታላቁ ለአልዓዛር ኢማም እና ለኮፕቲክ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ፣ በአጠቃላይም ለጋበዛችሁኝ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናየን አቀርባለሁኝ። ልባችሁን ሁሉ ለከፈታችሁልኝ እና በተለይም ደግሞ ይህ ሐዋሪያዊ ጉዞ እንዲሳካ የበኩላቸውን ሚና የተጫወቱትን ሰዎች ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁኝ።

ይህ የእኔ ጉብኝት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ ያለኝን ፍቅር፣ መጽናናት እና ማበረታቻ፣ በተጨማሪም በግብፅ እና በአከባቢው ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የጓደኝነት፣ የመከባበር፣ የወንድማማችነት እና በተለይም ከእስልምናው ዓለም ጋር እና ከሁሉም የአብርሃም ልጆች ጋር  እርቅ ይፈጸም ዘንድ፣ መልእክት የሚያስተላለፍ እና ምስክርነቴን ያንጸባርቅልኝ ዘንድ እመኛለሁ። የእኔ ጉብኝት ከሙስሊሞች ጋር የሚደረገውን ሐይማኖታዊ ውይይት እና ተወዳጅ ከሆኑት የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ጋርም የሚደረገውን የመግባቢያ ውይይት ፍሬያማ የሆነ አስተዋጾ እንደ ሚያበረክትም ተስፋ አደርጋለሁ።

ዓለማችን እና የእናንተንም ተወዳጅ ሀገር ልብ ያደማ አስከፊ በሆነ ጭፍን ግጭቶች ተበጣጥሳ ትገኛለች። ዓለማችን ሰላም፣ ፍቅር እና ምሕረት ያስፈልጓታል። ዓለማችን ነጻ የሆኑ እና ሌሎችን ነጻ ማውጣት የሚችሉ፣ ብርታት ያላቸው፣ መጪውን ዘመን ለመገንባት ካለፈው ታሪክ መማር የሚችሉ ከጭፍን ጥላቻ ሁሉ ነፃ የሆኑ ወንድ እና ሴት  የሰላም ሰዎች ያስፈልጓታል። ዓለማችን የሰላም፣ የመወያየት፣ የወንድማማችነት፣ የፍትህ እና የሰባዊነትን ድልድይ መገንባት የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጓታል።

ውድ ግብፅዊያን ወጣት እና አዛውንት ሙስሊም እና ክርስቲያን አብታም እና ድኸ የሆናችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሁሉን የሚችል እግዚኣብሔር እንዲባርካችሁ እና ሀገራችሁንም ከማንኛውም ዓይነት ክፉ ነገር ይጠብቅላችሁ ዘንድ እለምነውዋለው። እባካችሁን ለእኔ ጸልዩልኝ!

ሹክራን ጣዕያ ምስር ! አመሰግናለሁ ግብፅ ለዘልዓለም ትበልጽግ!

 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ይህ ቀደም ሲል የታደማችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 17/2009 ዓ.ም. በግብፅ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልክተው ያስተላፉት የቪዲዮ መልእክት ሙሉ ይዘቱን ነበር።