Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው "እምነታችን የመንግሥተ ሰማይ መልሕቅ ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳምንት አንድ ቀን ዘወትር ረዕቡ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚይደርጉ ይታወቃል። በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ተስፋን በድጋሚ በምያለመልመው እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ (ማቴዎስ 28፡20) በሚለው በክርስቶስ ቃል ዙሪይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል። ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 18/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን መልክት በመጫን ማደመጥ ትችላላችሁ!

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!

በዚህ በያዝነው የፋስካ በዓል ሰሞንየክርስቲያን ተስፋበሚል አርእስት የማቀርብላችሁ አተምህሮ የምያጠነጥነው በክርስቶስ ከሙታን መነሣት ላይ ሆኖ መሰረቱን ደግሞ ቀጣይነት ባለው በእግዚኣብሔር ጥበቃ እና ፍቅር ላይ ባለን ጥልቅ መተማመን ላይ ያደረገ ነው። ቅዱስ ማቴዎስ የጻፈው ወንጌል  የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ውልደትን አማኑኤልእግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ነውበማለት ይጀምርና ከሙታን የተነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ እስከ መጨረሻው ከእናንተ ጋር ነኝ ብሎ በገባው ቃል ይደመድማል። እግዚኣብሔር የቀድሞ አባቶቻችንን እንደ መራቸው ሁሉ፣ እኛንም በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ከጎናችን በመሆን የምድራዊ ጉዞ ግባችችን እስክንመታ ድረስስ ከጎናችን ይሆናል።እስከ ዘመናት ፋጻሜ ድረስይንከባከበናል።ሰማይን ምድር ያልፋሉነገር ግን እርሱ ለእኛ ያለው መለኮታዊ ጥበቃ እስከመጨረሻው ድረስ ይቀጥላል። ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የክርስቲያን ተስፋ በመልሕቅ ይመሰላል፣ ይህም የሆነበት ምክንያት የእግዚኣብሔር የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን የሚያሳይ፣ በሕይወታችን ዘመን ምልአት የሚያስገኝ መሆኑን፣ የክርስቶስን ሞት እና ትንሣኤንም የሚያሳይ ምልክት በመሆኑ የተነሳ ነው። የእኛ ተስፋ ያለው በእግዚኣብሔር ላይ ነው እንጂ በራሳችን ወይም ደግሞ በዓለም ላይ አይደለም፣ ይህንንም የምንረዳው ሕይወታችን በችግር፣ ተስፋ መቁረጥ እና በሽንፈት ውስጥ በሚገባበት ወቅት ሳይሆን ኢየሱስ እንድንከተለው ያቀረበውን ጥሪ በዝግጁነት ስንቀበል ብቻ ነው። ከሙታን በተነሳው በክርስቶስ ላይ ያደረግነው ተስፋ በሁሉም የሕይወታችን እርምጃ ውስጥ በመግባት ወደ ዘልዓለም ሕይወት የምናደርገውን እርምጃ ያጽናው።

 

ክቡራን እና ኩብራት የዝግጅታችን ታዳሚዎች ቀደም ሲል ስተከታተሉት የቆያችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 18/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ነበር፣ አብራችሁን በመሆን ስለተከታተላችሁን ከልብ እናመሰግናለን።