Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ወጣቶች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፥ ወጣቶች ለኢየሱስ እነሆኝ (እሺ) ለማለት እንዳያስፈራቸው አሳሰቡ


ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ትዊተር በተሰየመው በማኅበራዊ መርበት ባለው @Pontifex አት ፖነቲፊክስ በተሰየመው አድራሻቸው በዘጠኝ ቋንቋ ተተርጉሞ በሚሰራጨው ዕለታዊ በሚያስተላልፉት አጭር መልእክት አማካኝነት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም.፥  “ውድ ወጣቶች በሙሉ ልባችሁ በለጋስነት ኢየሱስን ለመከተል እሺ እነሆኝ ለማለት አትፍሩ”  እንዳሉና በዚያኑ ዕለትም ሮማ በሚገኘው በቅድስተ ማሪያም ዓቢይ ባዚሊካ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማሰናጃ በበዓለ ሆሳዕና የሚከበረው ብሔራዊ የጣቶች ቀን (ሰበካዊ እቀፍ) ዋዜማ የጸሎትና የአስተንትኖ ስነ ሥርዓት መምራታቸው የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታውቋል።

በሌላው ረገድም ቅዱስ አባታችን ከወጣቶች ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት ያንን እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. “ወጣቶች እምነትና የጥሪ መስተዋል” በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ የጠሩት የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስና እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም. በፓናማ እንዲካሄ የጠሩት 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጭምር  በእይታ ያኖረ መሆኑ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. ብራዚል ሪዮ ደጃነይሮና ሐምሌ 2016 ዓ.ም. በፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በመምራትና መሪ ቃል በመለገስ ተሳትፈው ቀጣዩ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ “ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአል…” (ሉቃስ ምዕ. 1 ቍ. 49) መሪ ሓሳብ በማድረግ እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም. እንዲካኤድ የጠሩት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጥር ወር የሚከናወን መሆኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን።

ቅዱስነታቸው በሮማ ከተማ እ.ኤ.አ. በሆሳዕና በዓል ዋዜማ በቅድስተ ማርያም ዓቢይ ጳጳሳዊ ባዚሊካ 32ኛው ብሔራዊ አቀፍ የወጣቶች ቀን መንፍሳዊ መርሃ ግብር መምራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል። በዚያ በኢጣሊያና በምዕራቡ ዓለም ታሪክ ውስጥ ቀዳሚ ለቅድስት ድንግል ማርያም በተወከፈው ባዚሊካ ከመላ ኢጣሊያ ሰበካዎች የተወጣጡ ወጣት ምእመናን የተሳተፉ ሲሆን፡ ቅዱስነታቸው ከለገሱት ቃለ ምዕዳን በተጨማሪም በተለያየ ጥሪ አማካኝነት ኢየሱስን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከተሉ ወጣቶች ቃለ ምስክንርነት መስጠታቸው አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን በጽሑፍ አቅርበዉት የነበረውን ቃለ ምዕዳን ወደ ጎን በማድረግ  እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም.  “ወጣቶች እምነትና የጥሪ መስተዋል” በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ የጠሩት የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ላይ በማተኮር ወቅታዊው የወጣት ሁኔታ ማዕቅፍ በማድረግ፥ “ዓለም አቀፍ የወጣቶ ቀን ከክራኮቪያ ወደ ፓናማ አቅንቷል። ቢሆንም እንደ ድልድይ ‘“ወጣቶች እምነትና የጥሪ መስተዋል’ በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ የተጠራው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ”  መኖሩ አስታውሰው፡ ይኽ የተጣራው ሲኖዶስ ለካቶሊክ ለመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ለሆኑት ወጣቶች የሚመለከት ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ሁሉም ወጣት የኅብረሰብ ክፍል የሚመለከት ነው፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቤተ ክርስትያን ውጭ ያሉትን ሁሉ የሚመለከት ነው። ሁላችን ቤተ ክርስቲያንም ጭምር ወጣቱን የሚናገረውንና የሚለውን ማዳመጥ ይገባል”  እንዳሉ ጂሶቲ ይጠቁማሉ።

“ተዘንግተው ለብቻቸው ለገዛ እራሳቸው እንደ ተተዉ የሚሰማቸው ብዙ ወጣቶች አሉ፡ የወጣቱ ሕይወት ብዙ መሰናክል የሚያጋጥምው ብዙ ችግር ያለበት ነው። በመገለላቸው ምክንያት መጓዝ የተሳናቸው ብዙ ናቸው። በሥራ አጥነት፡ አብነት በማጣት በሕንጸት አጥረት ተዋህዶ ለማኖር የሚያግዝ እድል በማጣት ምክንያት፡ በጦርነትና ግጭት ሳቢያ ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የመዳረጉ ችግር ስናስብ በአሁኑ ሰዓት መጽኢ ሕይወትን የሚያጨልሙ የሚታዩ ችግሮች ሁሉ ወጣቱ ምን ያክል የተዘነጋ መሆኑ ለተገሎ መኖር አደጋ ተላልፎ መሰጠቱ ተጨባጭ ሁኔዎች ናቸው።”

ስለዚህ የወጣት ክፍል የተጋረጠበት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችለው መንገድ ለማፈላለግ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ተጠርተዋል። 

ቤተ ክርስቲያን ከወጣት ትውልድ ጋር ለመወያየት ትሻለች፡ ወጣቱ ደግሞ ከአዛውንት የኅብረተሰብ ክፍል ጋር መወያየ ይኖርባቸዋል። የአዛውንቱ የኅብረተሰብ ክፍል ሕይወት ለውጣት ትውልድ መጻኢ እንዴትና ምን መሆን እንዳለበት የሚጠቁም ገጠመኝ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን አክለው፥ “

በፓናማ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ስንገናኝ ከአዛውንት የኅብረሰብ ክፍል ጋር መወያየታችሁንና እነርሱን ለማዳመጥ ጊዜ መስጠታችሁና አለ መስጠታችሁ እጠይቃለሁኝ። በእርግጥ የፓናማው ዓለም አቀፍ የወጥቶች ቀን ቃለ ምዕዳን በመስጠት የቅዱስ ጲጥሮስ ተከታይ ይሳተፋል፡ እሳተፍም ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ ተስፈኛ ነኝ  ካልሆነ ግን እኔም ባልሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንደሚሳተፍ የተረጋገጠ ነው”

እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታውቋል።

የተካሄደው የጸሎት ስነ ሥርዓት የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዓርማ የሆነው አቢይ መስቀልና እንዲሁም የቅድስት ማርያም ቅዱስ ምስል ወጣቶች በመሸከም ወደ ባዚሊካው በማስገባት የተጀመረ ሲሆን። የሚሰቃዩት ወጣቶች በማሰብ ቅድስተ ማርያም በተለያየ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው በስቃይ ላይ ያሚገኙትን ዘወትር እግዚአብሔር መጠጊያና አለኝታ መሆኑ ተረድተው በእርሱ ድጋፍ እንዲታመኑ ማርያም ታማልድላቸውም ዘንድ መጸለዩ  የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው ወላጆችና አስተማሪዎች ለወጣቱ ሕንጸት ብቃት ያላቸውና በበለጠም ቃልና ሕይወት በሚያስማማ ውሁድ አብነት አማካኝነት እንዲያንጹ ስለ ወላጆች ስለ አስተማሪዎች በጠቅላላ ወጣቱ በሚመለከት ዘርፍ ሁሉ ስለ ሚያገለግሉት መጸለዩና በመጨረሻም ቅዱስነታቸው የጠሩት በወጣት ዙሪያ ስለ ሚመክረው ሲኖዶስም መጸለዩ ገልጠዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓለ ሆሳዕና በተከበረበት ሰንበት እኩለ ቀን በለገሱት የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮና ጧት መስዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው በለገሱት ስብከትም  32ኛው ሰበካ አቀፍ የወጣቶች ቀን በማስታወስ፥ ሁሉም የዓለም ወጣቶች እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም. በፓናማ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንገናኝ በማለት ያላቸውን ምኞት ገልጸው እግዚአብሔር ፈቅዶት በሰላም ያገናኘን እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ አስታውቋል።