Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ፍትሕና ሰላም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ ዘወትር ነውጥ አልባ ትግል እንምረጥ


“በሰላም መንገድ መጓዝ መቼም ቢሆን ቀላል አይደለም፡ ቢሆንም ቅሉ ለማንኛውም ዓመጽ የተገባ እውነተኛ መልስ ሰላም ነው”  በሚል ቅዉም ሃሳብ ዙሪያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቺካጎ ሰበካ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 4 ቀን በሚታሰበው ማርቲን ሉተር ኪንግ ለሞት የተዳረጉበት ቀን ዝክረ 49ኛው ዓመት  ምክንያት ባነቃቃው ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስጀመረው የነውጥ አልባ ትግል ዘመቻ ለሰበካው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብላሰ ጆሰፍ ኩፒች መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ዘጋቢ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው በዚህ ባስተላለፉት መልእክት፥ “የሰው ልጅ በማንኛውም ዓይነት ግጭት የሚጠቆሱትን በቀል፤ ጠብ ጫሪነት፤ መልሶ የማጥፋት ጥቃት የተሰኙትን ተግባሮች እምቢ የሚል ስልት እንዲያበረታታ ተጠርተዋል፡ የዚህ ስልት መሰረት ደግሞ ፍቅር ነው” ሲል ማርቲን ሉተር ኪንግ የተናገረውን ቃል ጠቅሰው ይኸንን የማርቲን ሉተር ኪንግ ቃል ነቢያዊ በማለትም ገልጠው ሁሉም በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ “የነውጥ አልቦ ባህል የማይጨበጥ ህልም ሳይሆን በጣም አሰፈላጊ የሆኑት ውጤቶች ያስገኘ ጉዞ መሆኑ በማስተዋል የነውጥ አልቦ ባህል ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖረ ያስፈልጋል” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፥

ነውጥ አልቦ እንቅስቃሴ አንዱ ከአንዱ ጋር እንዳይገናኝ የሚያደርገው ለያይ አጥር በማቃወም ሰላምን መገንባት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ“እውነተኛው የነውጥ አልባ ሂደት የልዩነትና ለያይ አጥሪ የሚቃወም ቁስሎችን የሚፈውስ አገሮችን ያዳነ ነው ስለዚህ ይክ ባህል ቺካጎንም ይፈውሳል” እንዳሉና “የቺካጎ ነዋሪዎች ተስፋቸውን ሳያጨለሙ የሰላም መሣሪያ ለመሆን ለመጪው ትውልድ እውንተኛው ኃይል ፍቅር መሆ እንዲያመለክቱ የሚያበቃቸው መንገድ አብረው እንዲገነቡ” በማሳሰብ “ብዙ ቤተሰቦች በተለያዩ የዓመጽ ምክንያቶች አባሎቻቸውን ውዶቻቸውን ያጡ እንዳሉ እናውቃለን ለእነዚህ የሟቾች ቤተሰቦች ቅርብ በመሆን የስቃያቸው ተካፋይ በመሆን በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት ፈውስንና እርቅን የራሳቸው ተመክሮ ለማድረግ እንዲችሉ ስነ እነርሱ እጸልያለሁ” እንዳሉ አስታውቋል።

እምቢ አድልዎኝነትን፥ ገና ከወጣትነት እድሜ ጀምሮ አመጽን በመቃወም ተግባር መጠመድ

“በጣም የሚያሳዝነው አሁን ባለንበት ዘመን ብዙዎች በጎሳ በኤኮኖሚ ባላቸው የማኅበራዊ ልዩነት ምክንያት ሲገፉና ለአድልዎ ለተገሎና ተዘንግቶ  መኖር ለኢፍትሃዊነትና ለአመጽ ሲዳረጉ ማየቱ ነው። ስለዚህ ይኸንን ዓይነቱን ሌላውን የመነጠሉ የማግለሉ እንደ ወንድም ሳይሆን እንደ ሌላዊ አድርጎ የማየቱ ተግባር እምቢ ማለት ይጠበቅብናል።” ያሉት ቅዱስ አባታችን ይኽ አይነቱ የልብና የቀልብ ባጠቃላይ የሕይወት ጥረት የሚጠይቀው የነውጥ አልባ ባህል የሚነቃቃው ከቤተሰብና ከአቢያተ ትምህርት መሆኑ በማሳሰብ መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ፥ የቺካጎ ሰበካ ላሰናዳው የነውጥ አልቦ ዘመቻ በመንፈስ በተለይ ደግሞ በሕማማት ሳምንት ሁሉም የተለያየ ዓመጽ ሰለባ የሆኑትን በሚታሰቡበት በፍኖተ መስቀል (የመስቀል መንገድ) ጸሎት ለየት ባለ መንፈስ ቅርበቱ እንደሚኖራቸውም ማረጋገጣቸው ጂሶቲ አስታውቋል።