Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ፍትሕና ሰላም

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ለሰብአዊ ቤተ ሰብ መልካምነትና ጥቅም የተሟላ እድገት መንገድ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዝክረ 50ኛው ዓመት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ የደረሱት ዓዋዲ መልእክትPopolorum Progressio-የሕዝቦች እድገት”  ምክንያት በማድረግ ጳጳሳዊ ለምሉእ ሰብአዊ እድገት አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት “ለተሟላ የሰብአዊ እድገት አገልግሎት ተስፋ የተኖረበት ሃሳብ ፤ ዝክረ ሓምሳኛው ዓመት Populorum Progressio-የሕዝቦች እድገት” በሚል ርእስ ሥር  ባሳናዳው እ.ኤ.አ. ከምያዚያ 3 ቀን እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ በተካኤደ ዓውደ ጥናት የተሳተፉትን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. “ምሉእ እድገት ሰብአዊ ቤተ ሰብ ሊጓዝበት የተጠራበት የመልካምነት መንገድ ነው” የሚል ሃሳብ ላይ ተንተርሰው በለገሱት ምዕዳን መጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው ተጋባእያኑን ተቀብለው በለገሱት ቃለ ምዕዳን መግቢያ ይኽ በእሳቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መዋቅራዊ ህዳሴ መርሐ ግብር መሠረት የተቋቋመው ጳጳሳዊ የምሉእ ሰብአዊ እድገት አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያህ ቱርክሶን ፈር በማስያዝ ሥራውን በማስጀመሩና ቅርጽ በማስያዙ ሂደት ላሳዩት ትጋትና ያላቸው ብቃት ጭምር በመጥቀስ የምስጋና ቃል አቅርበው፥ የተሟላ ወይንም ምሉእ ሰብአዊ እድገት ሲባል የአያንዳንዱ ሰውና የመላ ሰብአዊ እድገት የሚያመለክት መሆኑ ገልጠው፥

ሕዝባዊ ውህደት

ምሉእ እድገት ሲባል የተለያየውን ሕዝብ ማዋሃድ ይኽ ደግሞ ተገቢነት ባለው መተባበር የሚል ኃላፊነት በተካነው አግባብ ለተካፍሎ መኖር የሚያግዝ ቅን አግባብ መፍጠር ማለት ነው። ምክንያቱም እንዲህ ሲሆን ብዙ ባለውና ምንም ነገር በሌለው፡ ሌላውን እንደ ጥራጊ የሚያገልና እንደ ጥራጊ ተነጥሎ ተገሎ በሚኖረው መካከል ለሚፈጠረው አስከፊው ልዩነት እንዳይኖር ይረዳል ብለው የውህደት መንገድ ለሰው ልጅ ሰላምና ተስፋ የተካነ መጻኢ እንዲኖር የሚያደርገው  በሕዝቦች መካከል ውህደት እውን ማድረግ ነው እንዳሉ መኒከቱ ገልጠዋል።

ማኅበራዊ ውህደት

ቅዱስ አባታችን ሕዝባዊ ውህደት የሚለው ሃሳብ ካብራሩ በኋላ ማኅበራዊ ሃሳብ የሚለው ጉዳይ ጠቅሰው፥ ሁሉም ለማኅበራዊው ጉዳይ የሚውል የሚሰጠው አስተዋጽኦ አለ። ይኽ ደግሞ ለሕዝቦች ኤኮኖሚያዊ ደህንነት የሚበጅ ነው። ስለዚህ ይኽ መብትና ግዴታን ያካተተ ለማኅበራዊ ጉዳይ የሚውል አስተዋጽኦ እያንዳንዱ የሚሰጠው የድርሻ አስተዋጽኦ በድኽነት የሚኖረውን ሰው እንዲደገፍ የሚያደርግ ነው፡ ኤኮኖሚ፤ ቁጠባ፤ ሥራ ባህል የቤተሰብ ሕይወት ሃይማኖቶች በጠቅላላ ባላቸው ልዩ የገዛ እራሳቸው መለያ ምክንያት በዚህ ምሉእ እድገት ለማማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ የማይተውና ሊሻር የማገባው አስተዋጽኦ አላቸው።

ማናቸውም ከእነዚህ አስተዋጽኦ አላቸው ከተባሉት ተጠቃሾች ውስጥ ማናቸውን የበላይነት ሳይኖረው ለምሉእ ሰብአዊ እድገት የየራሳቸው ኣስተዋጽኦ አላቸው፡ ሰብአዊ ሕይወት ልክ እንደ አንድ የሙዚቃ ጓድ ነው። እያንዳንዱ የተለያዩ መሣሪያዎችን በማቀንቀን ሁሉም የየራሱን ህርመት በማሳተፍና በማካፈል መንፈስ  አንድ ጥዑም ውህደት የተካነው ቕኝት ይፈጥራሉ፡

ግላዊና ማሕበረሰብአዊ ውህደት

ሌላው ተጋርጦ ያንን ግላዊ ውህደትና ማሕበረሰብአዊ ውህደት፡ በምሉእነት ማወሃድ የሚል ነው። በምዕራቡ ዓለም እንደታየው ይኽም ግለሰብ ላይ በማነጣጠር ማሕበራዊነትን በማግለል ወደ ግለኝነት የሚወስደውን የባለቤትነት መንገድ በማክረር እያንዳንዱ እንደ አንድ ደሴት እንዲሆን ወይንም ደግም እያንዳንዱን ሰብአዊ ፍጥሩ በማግለል ማሕበረሰብአዊነትን በተለያዩ ርእዮተ ዓለም አማካኝነት በማክረር የግል ነጻነትን የለም እስከ ሚባልበት ደረጃ እንዲደረስ የሚያደርግ አመለካከት በማክረር ሳይሆን እንዲሁም ያንን ዓለም በንግድ ደረጃ ብቻ የሚመዝናት በቁጠባው ዓለም ላይ እያተኮረ ያለው ዓለማዊ የትሥሥርዮሽ ሂደትም ተወግዶ በበለጠ በሰዎች መካከል መተሳሰብና ተካፍሎ መኖር የሚል ባህል የሚያስፋፋ በማድረግ ግላዊና ማኅበራዊ ውህደት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡ እኔና ማሕበረሰብ ተፎካካሪ ባለ ቤቶች አይደሉም ማኅበረሰብ የግለ ሰቦች ስብስብ ነው፡ ይኽ ደግሞ ያንን የኅብረተሰብ መሠረት የሆነውን ቤተሰብ የሚመለከት ጉዳይም ይሆናል፡ አብሮ መኖር የሚፈጥር ውኅደት ያስፈልጋል  እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ መኒከቲ አያይዘው፥

ሥጋንና ንፍስን ማወሃድ

ጳውሎስ ስድስተኛ የዛሬ 50 ዓመት በፊት በደረሱት ዓዋዲ መልእክትPopolorum Progressio-የሕዝቦች እድገት”  ሥር ልማት-እድገት እሳንሶና አጥቦ የኤኮኖሚን ጉዳይ ብቻ የሚመለከት ነው ብሎ መደምደሙ ትልቅ ስሕተት መሆኑ ያስገነዝባሉ። ይኸንን መሰረት በማድረግም ቅዱስነታቸው  ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥጋንና ነፍስን ማወሃድ የሚለውን ሃሳብ ላይ በማስተንተን፥ “ሥጋንና ነፍስን ማወሃድ ሲባል ያንን የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰብአዊ ፍጡር የሚመለከት ነው፡ በመሆኑም ማንኛውም የልማት/የእድገት ሥራ ይኸንን ግምት ውስጥ ካላስገባ ሊደረስ የታቀደለት ምሉእ ሰብአዊ እድገት ፈጽሞ ሊጨበጥ የማይቻል ይሆናል” የሚለውን ሃሳብ በአጽንኦት ለማሳሰብ በመፈለግ እንደሆነም ኣስታውቋል።

የኢየሱስ ሕይወት

“ኢየሱስ ሕይወት ነው፡ ያ እግዝአብሔር ገዛ ራሱን በማያዳግም ሁኔታ በሙላት የገለጠበት ሕይወት ነው።” በኢየሱስ ዘንድ ሰውና እግዚአብሒር የተክፋፈሉ የተነጣጠሉ አይደሉም፡ በዚህ ምክንያትም ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ የፈጸመውን “ፈውስ፡ ነጻ የማውጣትና የእርቅ” ሥራዎችን ዛሬ በሕይወት ጉዞ ለሚቆስሉት ሁሉ ለማረጋገጥ ተጠርተናል፡” ብለው፥

ክርስትናና ሰው የሚለው ፅንሰ ሓሳብ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የለገሱት ቃለ ምዕዳን ሲያጠቃሉ፥

“የሰው ፅንሰ ሃሳብ የተፈጠረውና የበሰለውም በክርስትናው ባህል ውስጥ ነው። ስለዚህ ክርስትና ሰው በሚለው ዙሪይ የሚገልጠው ፅንሰ ሃሳብ ለተሟላ እድገትና ልማት የሚሸኝ ነው። ምክንያቱም ሰው ሲባል ግኑኝነት እንጂ ግለኝንነት  መተቃቀፍን እንጂ ማግለልን ወይንም መነጠልን እያሰማም፡ ሰብአዊ ክብር የሚል መበዝበዝን የማይል ነጻነትን እንጂ ማስገደድን የማይል ነውቤተ ክርስቲያንይ ይኸንን ጥበብ ለዓለም ከማካፈል መቼም ቢሆን እንደማትደክም ነው፡ ስለዚህ ምሉእ ሰብአዊ ቤተሰብ ሊከተለው የሚገባው የመልካምነት መንገድም ይኽ ነው”

እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ መኒከቱ ካጠናቀሩት ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።