Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ንግግሮች

ቅዱስነታቸው "እኔም ብሆን በሕይወቴ የቦዶነት ስሜት የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ" ማለታቸው ተገለጸ።


“እኔም ብሆን በሕይወቴ የቦዶነት ስሜት የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ፣ መንፈሳዊ ሕይወቴ በጨለማ ውስጥ የገባበት ወቅቶች ነበሩ፣ በሕይወቴ ዘመን አንድ አንዴ ‘ጌታ ሆይ ይህንን ነገር መረዳት አቅቶኛል’ ያልኩበት ወቅቶችም ነበሩ” ቀደም ሲል ያዳመጣችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለት በየካቲት 30/2009 ዓ.ም. ከጀርመኑ ደይ ዜይት ከተባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከተናገሩት የተቀነጨበ ነው።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዜት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ደይ ዜይት የተባለው የጀርመን ሳምንታዊ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነው ጆቫኒ ዲ ሎሬንሶ ለቅዱስነታቸው “ሰዎች እምነታቸው ቀውስ ውስጥ በሚገባበት ወቅት የእነዚህን ዓይነት ሰዎች ከገቡበት ቀውስ ይወጡ ዘንድ ምዕመናን እንዴት ሊረዱዋቸው ይችላሉ?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው ሲመልሱ “ማንም ሰው ቀውስ በሕይወቱ ሳይገጥመው ሊያድግ አይችልም፣ በሰው ልጆች ሕይወት ተመሳሳይ የሆኑ ቀውሶች ሁሌም ይከሰታሉ። የሥነ-ሕይወት እድገት በራሱ ቀውሶች ይገጥሙት የለምን? እምነትም እንደዚያው ነው በቀውሶች መሃል በተመሳሳይ መልኩ የሚያልፈው” ብለዋል።

“እኔም ብሆን በሕይወቴ የቦዶነት ስሜት የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ” ብለው ቅዱስነታቸው መናገራቸው የጀርመኑ ሣምንታዊ ጋዜጣ ዴይ ዜይት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጆቫኒ ዲ ሎሬንሶ በጣም አስገርሞት እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል። “እምነት ስጦታ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “ማንም ሰው ከገባበት የእመንት ቀውስ በራሱ መውጣት አይችልም፣ ከገባበት ቀውስ ለመውጣት የግድ የእግዚኣብሔር እገዛ ያስፈልገዋል፣ እግዚኣብሔርን ጠይቁት እርሱም ዛሬ ይሁን ነገ መልስ ይሰጣችኃል፣ ነገር ግን አንድ አንዴ በዛ ቀውስ ውስጥ ሁነን ልያስጠብቀን እንደ ሚችል መረዳት ይኖርብናል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ከጀርመኑ ሣምንታዊ ጋዜጣ ዴይ ዜይት ጋር አድርገውት የነበረው ቆይታ በቀጣይነት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው እንደ እርሳቸው አገላለጽ “ሦስተኛው የዓለም ጣርነት” በማለት የሰየሙትን ቀስ በቀስ በአፍርካ፣ በዩክሬይን፣ በኢሲያ፣ በኢራቅ እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍል እየተካሄዱ የሚገኙትን ግጭቶች እና ጦርነቶች ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም ተገልጹዋል። ከእዚህም ባሻገር በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በአንድ አንድ ፖሌቲከኞች እያንጸባረቁት ሚገኙትን የሰፊውን ሕዝብ መብት እና ሰፊው ሕዝብ የሚፈልገውን ምግባር ሁሉ እናስፈጽማለን በማለት ራሳቸውን እንደ “መሲህ” በመቁጠር የተደበቀ ዓላማቸውን ሰፊውን ሕዝብ በመጠቀም ለመስፈጽም የደፈጣ ውጊያ በማድረግ ላይ በሚገኙ ሰዎች ላይ አትኩሮ የነበረ ሲሆን ይህም እንደ እርሳቸው አገላለጽ ወቅታዊ የሆነ ውዥንብር እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የጀርመኑ ሣምንታዊ ጋዜጣ ዴይ ዜይት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጆቫኒ ዲ ሎሬንሶ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ሁኔታና እርሳቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡበት እለት ጀምሮ ከወቀሳ አምልጠው አያውቁም የሚል ጥያቄ  በቀጣይነት ያቀረበላቸው ሲሆን ቅዱስነታቸውም ሲመልሱ “አንድ አንድ ጊዜ የእኔን የአሠራር ሁኔታ የሚቃወሙ ሰዎች አሉ፣ ይህንን እኔም የምቀበለው ጉዳይ ነው፣ ምክንያቱም እጅግ በረከት ያሉ የተለያዩ አስተሳሰቦች ስለሚገኙ ነው። ይህም ሰባዊ የሆነ ነገር ነው፣ ይህም ወቀሳና ቅዋሜ እኔ የሚያጎለብተኝና የሚያሳድገኝ ነው እንጂ አፍራሽ አይደለም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆኜ ከተመረጥኩበት እለት አንስቶ እስከ ዛሬ እለት ድረስ ሰላሜን የሚያሳጣኝ ምንም ዓይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም” በማለት ከመለሱ ቡኋላ ከጣዩ ዓለማቀፍ የሐዋሪያው ጉብኝታቸው መዳረሻ ሕንድ፣ ባንግላዲሽ እና ኮሎንቢያ ሊሆኑ እንደ ሚችል ጠቁመው በደቡብ ሱዳን ሊያደርጉት አቀደው የነበረው ሐዋሪያው ጉብኝት እውን የሚሆን አይመስለኝም ብለው ሁል ጊዜም እንደ ሚሉት “እባካችሁን ለእኔ ጸልዩልኝ” ካሉ ቡኋላ ከጀርመኑ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዴይ ዜይት ዋና አዘጋጅ ከሆነው ጆቫኒ ዲ ሎሬንሶ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀዋል።