Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ፍትሕና ሰላም

ብፁዕ አቡነ ኡርባንቺዝይክ፥ ለመከላከያ ኃይል አባላት ቆሞሶች የሰላምና የምሕረት ምልክቶች ናቸው


ከጥንት ጀምሮ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለመከላከያ ኃይል አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ መስጠቱ አንዱ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርሐ ግብሯ በማድረግ ታገለግላለች። ጦርነት በሰዎች ሕይወት ህሊና ዘንድ የማይሰረዝ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ነው የሚያልፈው። ስለዚህ ጦርነት በወንድሞች መካከል ያለው ጥምረት በአገሮች መካከል ባጠቃላይ በሰዎች መካከል ያለው ግኑኝነት ያሰናክላል ግኑኝነቱን ያበላሻል። እነዚያ በቀጥታ የጦርነት በተቀዳሚነት ተምክሮው የሚኖራቸውም የጦርነት አሰቃቂነት ቀጥተኛ ምስክር የሆኑት ወታደሮች ጦርነት ዘርፈ ብዙ ስንክልና ያስከትልባቿል ከዚህ በመንደርደርም ለመከላከያ ኃይል አባላት የሚሰጠው መንፈሳዊ እንክብካቤ ያለው አስፈላጊነት በአጽንኦት ያሳሰበ ንግግር “ለመከላከያ ኃይል አባላት ቆሞሶችና የሃይማኖት ነጻነት በሰላምና በጦርነት ወቅት” በሚል ርእስ ሥር የኤውሮጳ አገሮች የደህንነትና የትብብር ማኅበር ባካሄደው ዓውደ ጉባኤ  ያስደመጡት በማኅበር ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ያኑዝ ኡርባንቺዝይክ  መሆናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

የመከላከያ ኃይል ቆሞስች ወታደሮችን በሁሉም ሥፍራና በማንኛውም ወቅት ይሸኛሉ። ወታደሮችን ያጽናናሉ ያሉት ብፁዕ አቡነ ኡርባንቺዝይክ ቀርበው ወታደሩ የሚያቀርበውና ያለበት መንፈሳዊ ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራሉ። ቅድሚያ ሊሰጠባቸው የሚያስፈልጉትን እሴቶችን በመጠቆም ማለትም በሰው ልጅ ሕይወትና የአገርና የሕዝብ የሚያስተሳስረውን የጋራ ጥቅም የሚያበክሩትን እሴቶች ያማከለ ሕንጸት ይሰጣሉ።

የመከላከያ ኃይል ዘብ ነው፡ አስከባሪ፡ ሰላም የሚያስከብር ነው፡ ስለዚህ ሚናው የሰላም ዘብን አስከባሪ የሚለው ነው። ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በሁለተ ሺሕኛው የኢዮቤልዩ ቅዱስ ዓመት በዚያ ለየመከላከያ ኃይል አባላት የጸጥታ ደህንነተ አባላት ኢዮቤል ተብሎ ተሰይሞ በነበረው ቀን የመከላከያ ኃይል አባላትን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን፥ “የመከላከያ ኃይል አባላት ሚና አደጋዎችን ከወዲሁ እንዳይከሰቱ ለማድረግ የሚያግዙ ወይንም የሚያበቁ አድማሶችን የምፈትሽ በሁሉም ስፍራ ፍትሕና ሰላም ለማነቃቃት ነው፡ ያንን ለአመጽ የሚከጅለው ፈተና እንዲሸነፍ የሚያደርግ ወንጌላዊ ኃይል ነ፥ ያንን የመከላከያ ኃይል የሚለው መጠሪያ ኃይልና የመከላከያ የሚል ሲሆን የሚኖረው ኃይል ለአበይት የሕይወት የፍትሕ የሰላም የምሕረትና የነጻነት እሴቶ መሣሪያ እንዲውል የሚያደርግ የመከላከል ተግባር ነው”  በማለት ያበከሩት ሃሳብ ብፁዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ ኡርባንቺዝይክ ባስደመጡት ንግግር ዋቢ በማድረግ የመከላከያ ኃይል ሰላምን የሚያፍ ነው እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኝ ሎሞናኮ አያይዘው፥ ቤተ ክርስቲያን ለመከላከያ ኃይል የምትሰጠው መንፍሳዊ እንክብካቤ በሕገ ቀኖና መሰረት ለራሱ የቻለ ሰበካ ነው፡ በዓለም 36 የመከላከያ ኃይል መፍንፈሳዊ ተንከባካቢ ሰበካዎች 2,500 የመከላከያ ኃይል ቆሞሶች እንዳሉ ገልጠው እነዚህ ቆሞሶች ፥ ቅዱነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም.በ 39ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት፥ “የእውነና የሰላም ወንጌል ታማኝ ሰባኪያን” ናቸው እንዳሉት ነው።

ወታደር ክርስቲያናዊ ተስፋን እንዲመሰክር የተጠራ ነው፡ ይኸንን ሃሳብ በመከተልም በሁሉም አገሮች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባሉዋት ሰበካዎችና ቁምስናዎች አማካኝነት ለመከላከያ ኃይል አባላት ቅዱስ ሚሥጥራዊና የመንፈሳዊ ግብረ ኖልዎ እንክብካቤ ታቀርባለች። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅዱስ የምሕረት ዓመት ምክንያት የመከላከያ ኃይልና የጸጥታና ደህንነት አባላት ኢዮቤልዩ ቀን ምክንያት፥ “የመከላከያ ኃይሎችና የጸጥታና ደህንነት አባላት ፍቅር በጥላቻ ላይ ሰላም በጦርነት ላይ አሸናፊ እንደሚሆን ያለውን እርግጠኛነት የሚመሰክሩና ለክርስቲያናዊ ተስፋ አብነት ናቸው” ያሉትን በመጥቀስም ኃይል የሕይወት የሰላምና የፍትሕ መሣሪያ እንዲሆን የሚያደርጉ ናቸው እንዳሉ ሎሞናኮ ገልጧል።

ብፁዕ አቡነ ኡርባንቺዝይክ ያስደመጡት ንግግር ሲያጠቃልሉ፥ የሃይማኖት ነጻነት አንድ የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት ነው፡ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትና ክብር ውሳኔ ዘንድ እውቅና ያገኘ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን በሄልሲንኪ ሰነድ የሚጠራው የዚህ የኤውሮጳ አገሮች የደህንነትና የትብብር ማኅበር የአስርቱ ትእዛዛት ሕግ ሰነድ አንዱ ክፍል ነው፡  እያንዳንዱ ሰው በየትን ስፍራና ሁኔታ የሃያማኖት ነጻነቱ ሊከበርለት ይገባል። የዚህ ነጻነት ተጠቃሚም ሁሉም ሰው መሆን አለበት። ስለዚህ የሰብአዊ መብትና ክብር መስረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነትም ለሁሉም የመከላከያ ኃይል አባላት ሰላም ወይንም ጦርነት ባለበትም ወቅት ሊረጋገጥላቸው ይገባል የሚባለውም ለዚሁ ነው እንዳሉ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።