Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው "እግዚኣብሔር ከመባዕ ይልቅ ምሕረትን ይወዳል ማለታቸው" ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ርዕቡ እና እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ምያስተላልፉ የሚታወቅ ሲሆን በየካቲት 5/2009 ዓ.ም. የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎትን ከምዕመናን ጋር ከደገሙ ቡኋላ ያስተላለፉት አስተምህሮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ-ሊጡርጊያ አቆጣጠር በእለቱ በተነበበው ከማቴዎስ ወንጌል (5:17-47) ላይ በተወሰደው ምንባብ ዙሪያ  ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእዚህም ምንባብ ኢየሱስ ለሕዝቡ “የሙሴን ሕግና የነቢያትን ትምህርት ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ እኔ ፍጹም ላደርጋቸው መጣው እንጂ ልሽራቸው አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ሕግ ሁሉ ይፈጸማል እንጂ ከሕግ አንዲት ጭረት ወይም አንዲት ነጥብ አትሻርም” በሚለው የኢየሱስ ቃል ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ አስተምህሮ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

በእዚሁ የወንጌል ቃል ላይ ተንተርሰው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት. . .

በዛሬው እለት ስርዓተ ሊጡርጊያ የምናገኘው ምንባብ ከማቴዎስ ወንጌል የተወሰደና  ኢየሱስ በተራራው ላይ ያደረገው ስብከት ሁለተኛ ክፍል ነው። በእዚህ ምዕራፍ ኢየሱስ አድማጮቹን የሙሴን ሕግ ትርጉም በሚገባ መረዳት ይችሉ ዘንድ በሕጉ ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፉት ሕጎች ሁሉ እውነተኛ ናቸው፣ ነገር ግን ሁሉም አይደሉም። ኢየሱስ ሕግን ተፈጻሚ ለማድረግና የእግዚኣብሔርን ቃል ሙሉ በሙሉ አንዲት ነጥብ እንኳን ሳትሻር ተግባራዊ ለማድረግ ነው የመጣው። ኢየሱስ የሕግን መሠረታዊ ጥቅም በመግለጽ፣ ይህም መሠረታዊ ዓላማውን በጠበቀ መልኩ ለማስፈጸም፣ እንዲሁም ይህንን በስብከቱና በተጨማሪም ራሱን ለመስቀል ሞት መስዋዕት በማድረግ ተግብሮታል። ስለዚህም ኢየሱስ የእግዚኣብሔርን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ እንዴት መተግበር እንደ ምንችል አስተምሮናል። ይህንንም በቅድሚያፍትህን ማድረግ ያስፈልጋል!” የሚለውን ሀረግ በመጠቀም በጊዜው ለነበሩት ጽሐፍትና አይሁዳዊያን አስረግጦ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ሁሉንም የእግዚኣብሔር ትዕዛዛትንና ደንቦችን መጠበቅ ያስፈልጋል በሚል ህሳቤ ሳይሆን መተግበር የሚጠበቅብን፣ ይህንን ፍትህ ተጨባጭ በሆነ መልኩ በፍቅር፣ በልገሳና በምሕረት፣ የሕግን አጠቃላይና አንኳር የሆኑ እሴቶችን በመረዳት መተግበር ያስፈልጋልብለዋል።

“ሕግጋትን መጠበቅ” ማለት አሉ ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ሕግጋትን መጠበቅ ማለት ይህንን መፈጸም እችላላሁ፣ ያንን ግን አልችልም፣ እስከ እዚህ ድረስ ብቻ ነው እንጂ መተግበር የምችለው እስከ እዚያ ግን መድረስ አልችልም” በማለት ራሳችንን መገደብ ማለት ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በዛሬው ከማቴዎስ ወንጌል 5 በተነበበው የወንጌል ቃል ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በቀድሞ ጊዜ ለነበሩ ሰዎች የተባለውን ሰምታችኋል፣ ይኸውምአትግደል ሰውን የገደለ ይፈረድበታልየሚል ነው። እኔ የምላችሁ ግን ይህ ነው፣ ሰውን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ደግሞም ማንንም ሰውአንተ የማትረባ` ብሎ የሚሳደብ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል. . .ስለዚህ መባህን በመሰውያው ላይ ለእግዚኣብሔር በምታቀርብበት ጊዜ ያዘነብህ ሰው እንዳለ ብታስታውስ መባህን በመሰውያው ፊት አስቅምጥና ሂደህ በመጀመሪያ ከእዚያ ሰው ጋር ታረቅ ከእዚያም ተመልሰህ መባህን አቅርብበማለት ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የይቅርታን አስፈላጊነት እና እግዚኣብሔርን ደስ የሚያሰኘው ከምስዋዕት ይልቅ ምሕረትን መሆኑን አስረድቶዋቸው እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

በዛሬ የማቴዎስ ወንጌል  (5:17-37) ኢየሱስ “መግደል፣ ማመንዘርና የመሐላ ቃልን አታፍርስ” በሚሉት 3 ታላላቅ ትዕዛዛት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው አትግደል የሚለው ትዕዛዝ የሚያመልክተው የሰውን ነብስ ማጥፋት ብቻ እንዳልሆ ኢየሱስ አስተምሮናል ካሉ ቡኋላ የሰውን መብት መጋፋትና አለአስፈላጊ የሆኑ ስድቦችን መጠቀም በራሱ እንደ መግደል ይቆጠራል፣ ወንድሙን የሚሳደብ ሰው በልቡ ውስጥ ወንድሙን እንደ ገደለ ይቆጠራል ስለዚህም እባካችሁን ከመሳደብ እንቆጠበ ብለዋል። 

ማመንዘር እንደ ስርቆት ይቆጠራል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የማመንዘር ጽንሰ ሐሳብ በቀዳሚነት የሚፈጠረው በልባች ውስጥ ነው ፣ ይህም የተሳሳተ ምርጫ እንድንወስድ  በማድረግ አሳባችንን እንድንተገር በመገፋፋት ወደ አመንዝራነት ይከተናል ይገፋፋናልም ብለዋል።

የመሐላ ቃልን አታፍርስ የሚለውን ትዕዛዝ በተመለከተ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “በጭራሽ አትማሉ፣ በሰማይም ቢሆን አትማሉ ሰማይ የእግዚኣብሔር ዙፋኑ ነው” ብሎ እንደ ነበረ በማስታወስ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስንታቸው በአንጻሩም መሐላችን በቤተሰባችን፣ በማኅበረሰባችን፣ በሥራ ቦታችን. . . ወዘተ ያለምንም የበላይ አካል ጣላቃ ገብነት መግባባትንና ተአማኝነትን  ለመፍጠር፣ መግባባትን ለማምጣት መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት ከለይ የተጠቀሱትን የወንጌል ቃል ምክሮችን ሁሉ በተግባር ላይ እንድናውል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትርዳን ካሉ ቡኋላ በተጨማሪም ሁሉንም ነገር በፍቅር በመፈጸም የእግዚኣብሔርን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማከናወን እንድንችል መነፍስ ቅዱስ በጸጋው ይሙላን ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።