Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ሳይንስና ትምህርት

ቅ.እ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው መጽሔት ግኑኝነትና ውይይት የሚያነቃቃ ድልድይ ይሁን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዛሬ 167 ዓመት በፊት አንድ በማለት ሕትመቱን የጀመረው በኢየሱሳውያን ማኅበር የተመሠረተው  በማኅበሩ የሚተዳደረው  La Civiltà Cattolica - ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው አራት ሺሕ የሕትመቱ ቀን ምክንያት በማድረግ በኢየሱሳውያን ማኅበ ጠቅላይ አለቃ አባ ኣርቱሮ ሶዛ የተሸኙትን የዚያ መጽሔት ማኅበረሰብ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የግኑኝነቱ ሥነ ስርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ይኽ የኢየሱሳውያን መጽሔት በአሁኑ ወቅት በአባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ዋና አዘጋጅነ የሚተዳደር ሲሆን ቅዱስነታቸው በለገሱት ምዕዳን፥ መጽሔቱ አራት ሺሕኛው ሕትመቱን ሲያስቆጥር ተራ የመጽሔቱ ብዛት ቆጠራና መቼ ተጀመረ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይሆን፡ በውስጡ ያለፉትና ያሉት የሕይወት ታሪክ መግለጫ ነው፡ እኚሕ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መጽሔቱ በየሁለት ሳምንት የሚያወጣው ኅትመቱ እንደሚደርሳቸውና በጠረጴዛቸውም እንዳለ እንደሚከታተሉትም ገልጠው መጽሔቱ ለብቻው የሚጓዝ ሳይሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ጀልባ በሆነቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ነው፡ ሁሌ እከታተላችኋለሁ አድናቂያችሁም ነኝ፡ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንድሆን ከተጠራሁባት ዕለት ጀምራችሁ በመከታተል እንዲሁም እ.ኤ.አ. ነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ከመጽሔቱ ጋር ያካሄዱት ረዥም ቃለ መጠይቅ አስታውሰው፡ እናንተ በዚህ መጽሔት በኩል ገዛ እራሳችሁን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ዓለም ክፍት የምታደጉና ከሁሉም ጋር ቤተ ክርስቲያንን ታወያያላችሁ ታገናኛላችሁ፡ መጽሔቱ በቅርቡ በስፓንኛ በኢንግሊዝኛ በፈረንሳይኛ በኮርያኛ ቋንቋ መታተም እንደጀመረም ገልጠው፡ አድማሱን እጅግ እያሰፋ ነው፡ ኅያው ባህል በሕዝቦች በባህሎች መካከል ክፍት ያለው ተገናኝ ተሟይ ብዜት መጋራት መወያየት መስጠት መቀበል የተሰኙትን እሴቶች የሚኖር ነው። በመጽሔቱ አማካኝነት የማኅበሩን መንፈሳዊ ጸጋን ትኖራላችሁ፡ እርሱም ካቶሊካዊ እምነትን መከላከል ወይንም መንከባከብ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን እይታና ፍቅር ለዓለም ለመመስከርም ነው፡ እምነት ለእናንተ የእውቀት ፍተሻ ጥናት እና ምርመራ ዋስትና ነው። አለ የመመራመር ግፊትና የአለማረፍ መንፈስ ሁሉም መክኖ በቀረ ነበር። የማወቅ የመመራመር ፍላጎታችሁ በአለማረፍ የተመራ ነውን? ለአንድ ኢየሱሳዊ ልብ ሰላም የሚሰጠው አለማረፍን ነው፡ ምክንያቱም ሁሉም የተረጋገጠ ብሎ በተረጋግጦ መኖር መንፈስን ያደክማል። አለማረፍ የሆነው ማረፍ በመሻቱ ሂደት እንድገ እንዲኖ ያደርጋል።  አንዳንዴ በጠመቅ ትምህርት እማኔ የማኖር ጉዳይ በመመራመሩ ላይ ጥርጠሬ እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል። የእምነት እርግጠኛነት የምርምር አንቀሳቓሽ እንጂ ምርምርን የሚያገል አይደለም።

መጽሔታችሁ የዚህ ዓለም ቁስል ጭንቀት የራሱን በማድረግ ፈውሱ ምን መሆን ይጠቁማል። በማያርፈው ቀልባችሁ ተራመዱ ሁሌ ፈልጉ የበለጠው ዓለም እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥትን ገንቡ። በዚህ ብዙ ተጋርጦ በተሞላው ዓለም ያላችሁ እምነት አስተሳሰባችሁና እወቀታችሁ ሁሉ ክፍት ያደርጋል። እግዚአብሔር ዘወትር ግርምታችን ነው፡ ያስደንቀናል። ስለዚህም ነው እናንተ ሙሉ ነኝ የማይል ሃሳብ የሚያፈልቁ ጋዜጠኞና ጸሓፍት እንጂ ዝግና ደንዳና የሆነ ሃሳብ አቅራቢ መሆን የለባችሁም የምለው። ያላችሁ እምነት እሳቢአችሁን ክፍት ያሚያደርግ እንጂ የሚቆልፍ ወይንም የሚዘጋ መሆን የለበትም። በነቢያዊ የወጌል መንፈስ ለመመራት ፍቀዱ ይኽ ደግሞ አዲስ ኅያው ንቁ አድራጊ ግልጽ ነው የማይል የታወቀ ነው የማይል በአስገራውሚ ጌታ የሚያስገርም ራእይ እንዲኖራችሁ ያስፈልጋል፡ በዚህ በአሁኑ ወቅት በዓለም ከዚያ ርኩስና የሐሰት መሲሓዊነት የሚበረታታ የማፍረስ የማውደም የተዛማጅነት የመጠራጠር የድርቅና የተራ የለብታ ባህል በተስፋፋበ ሁነት ሁሉን ነገር የሚጥል መልካሙንና ከፉው የማይለይ እግበስባሽ ባህል ባንሰራፋበት ወቅት እናንተ የዚያ ክፍት የሆነ ነቢያዊ ባህል አንጸባራቂያን ሁኑ።  ልክ  እንደ ኢየሱሳዊው ቅዱስ ማተዮ ሪቺ የካቶሊካዊ ሥልጣኔ ትርጉም አስተዋውቁ። ለካቶሊኮችም እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያን ድንበር ውጭ፡ በማንኛውም እውነተኛሥልጣኔ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ እንደሚሰራ አስታውቁ።

ሕዝብን አዳምጡ አስተዋይነት ይኑራችሁ። ቤተ ክርስቲያን በዓለም ይኸንን እስተዋይነትን የምትመስክር ነች። በጌታ ኅላዌ ተነቃቅታ የወቅታዊው ዓለም ምልክቶችን የምታነብ የሚከሰቱት ጉዳዮች ሁሉ በማንበብ መገድን የምታመልክት ነች። ለሕዝብና በተለይ ደግሞ ለድኾች መገዱን የምታመላክት ብቻ ሳትሆን አብራ የምትጓዝ ነች። ነገሮችን የማጤን የመለየት ጥበብ የተካነች ቤተ ክርስቲያን ልክ ኢየሱስ ሥጋችን ለብሶ ወደ እኛነት እንደ ገባ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በኅብረተሰብ ውስጥ በመግባት መሰገው ይኖርባታል።

መጽሔቱ ለሥነ ጥበብ ለሥነ ጽሑፍ ሥነ ፊልም ለሥነ ትያትር ለሥነ ሙዚቃ ክፍት መሆን አለበት። የሥነ ጥበብ ስሜት ያለው መጽሔትም መሆን አለበት። በዚህ ባለንበት ዘመን ሰውን እንዴት እንደምንረዳው የሚገልጥ፡ የወቅቱን ሰው የሚያብራራ በዚህ መሠረት የካቶሊክ ትምህርት ማሳደግ በጥልቀት ማጤንና ማሳወቅ አስፈላጊ ይሆናል፡ ሓሳበ ሰፊና ዓይነ ህሊና ያለው መሆን ያስፈልጋል። እንዲህ ሲኮን ብቻ ነው ግትርነት የማይኖረው ዋዛና ቁም ነገር እንዲኖር የሚያስችለው፡ ሓሳበ ሰፊና ዓይነ ህሊና ያለው ምህረትን ያውቃል የውስጥ ነጻነትም ያለው ይሆናል። ዓይነ ህሊና ሲኖረን የተከፈተ ስፍራ ያላቸው እንሆናለን በራስ ላይ እንዘጋም ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የለገሱት ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፥ የካቶሊክ  ሥልጣኔ መጽሔት በኢየሱሳውያን ማኅበርና በኢየሱሳውያን ካህናትና እንዲሁም በብፁዓን ጳጳሳት መደገፍ ይገባዋል። ከሓዋርያዊ መንበር ጋር ልዩ ትሥሥር ያለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መጽሔት ነው እንዳሉ ጂሶቲ ያመልክታሉ።