Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ሳይንስና ትምህርት

የኔታ ቪጋኖ፥ ቅዱስ ኣባታችን ገር ሁን ሲሉ የተስፋን ብልጭታ የምታሳይ ሁን እያሉ ነው


የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ዋና ጸሓፊ የኔታ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ እ.ኤ.አ. ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 51ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ያስተላለፉት መልእክት በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በይፋ ለንባብ ማብቃታቸው የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።

የኔታ ቪጋኖ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱትም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት በቅድሚያ ነገሮችን ሁነቶችን ክንዋኔዎችን አስተውሎ የሚተርክ መሆን ይገባዋል የሚለውን ነጥብ ተጨባጭ ሁነት ግራ የሚያጋባ ወይንም አሻሚ አንዳልሆነ ያስገነዝባሉ። በተለይ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን የግኑኝነት አገልግሎታቸው ገንቢና የሚከተለውም አመክንዮ መልካም ዜና ነው፡ ነገር ግን መልካም ዜና ሲባል ተጨባጩን ሁነት በይቆይልኝ አስቀምጦ ሊጨበጥና ሊከወን ተቻይ የማይሆነውን ምናባዊ ዓለም ማቅረብ ማለት አይደለም። እውነትን በማቅረብና ገንቢ በመሆን የተስፋ ጭላንጭ የሚያሳይ መሆን ይኖበታል። እንዲህ ባለ ሂደት ያንን አሉታዊነትን ያማከለ የዜና አቀራረብ አሊያም ስልት ማረም እጅግ አስፈላጊ ነው። በእርግጥ ታሪክ ጥላና ብርሃን አለው። ሆኖም ሁሌ ግራጫማው ታሪክ ላይ ብቻ ችክ ማለቱ ተስፋን ያጨልማል ስለዚህ እውነቱን በመከተል ነገር ግን ግራጫማውም ይሁን ብሩሁ የታሪኩን ክውንነት ስታቀርብ የተስፋ ጭላንጭል መጠቆም መቻል ተገቢ ነው። ስለዚህ የመገናኛ ብዙኃን የግኑኝነቱ ተግባር ግራጫማው ታሪክ ወይንም ግብረ እኵይ ዋና ተወናያን የሚያደርግ መሆን የለበትም።

ተጨባጩን ሁነት ለማቅረብ ብቃት ያለው የመገናኛ ብዙኃን እጅግ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ያለውን እውነት ማቅረብ ያስፈልጋል። ሆኖም አሉታዊው እንዲሁም ተፈጥሮአዊም ይሁን ሰው ሰራጭ እኵይ ክስተት ዙሪያ መረጃ ስታቀርብ ይኸንን ዜና አድርገህ ስታቀርብ እኩይ ክስተቱን ሊለውጥ የሚችል ተስፋ በማቅረብ ብቃት መሸኘት ያስፈልጋ። ችግሩ አጋጥሞኋል ለስቃይ ተዳርገሃል ሆኖም በዚህ ውጣ ውረድ ጎዳና አብሬህ አጓዛለሁ እደግፍሃለሁ የሚል የተከሰተውን እኩይ ሁነት እንዳልተከሰተ አድርጎ ለማሳየት ሳይሆን በስቃይም በችግርም ለብቻህ አይደለህም ብሎ ለማጽናናት ሰብአዊነትን ለማነቃቃት ነው።

የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን ዓለም አቀፍና ብሔራዊ የመገናኛ ብዙኃን ለመደገፍ ብቃቱ አለው። እርሱም ተጨባጭ ክስተት ዜና አድርጎ ወይንም በውይይት መድረክ አማካኝነትም ይሁን ስታቀርበው ለሌላው ስታስተላልፈው፡  የምታገናኘው ዜና ይዞታውና አንኳር መልእክቱ ምን መሆን እንዳለበት መለየቱ ያስፈልጋል። ይህ ሲባል ደግሞ የተከስተው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ከክስተቱ የማይዘል ክስተቱን ብቻ ለማገናኘት ሳይሆን ቅዱስ አባታችን እንደሚሉት ከዚያ ከተከሰተው ጉዳይ ምን መማር እንደሚያስፈልግ መለየትና ክስተቱን በማገናኘት አገልግሎት በማገናኘቱ ረገድ ስህተት ከተፈጠረም ተሳስችያለሁ ብሎ ይቅርታን መጠየቅ እውነትን አለ መፍራት፡ ሁሌ የተስፋ ጭላንጭል የሚያሳይ መሆን አለበት።

ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በ51 የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ያስተላለፉ መልእክት ለመገናኛ ብዙኃን ሀዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ስናነብ ስናገናኝ መጀመሪያ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አሁን ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚሉት መመዘኛው መንፈሳዊ - ትንታኔ ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ። ሆኖም መንፈሳዊ ትንተና ሲባል ተጨባጭ አለ መሆን ማለት አይደለም። መንፈሳዊነት ከታሪክ ከሰው ልጅ ተጨባጭ ሁነት ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር የተቆራኘ ነው። ብዙዎች መንፈሳዊነት ሲባል ከተጨባጩ እውነት የራቀ ብለው ሊረዱት ይችላሉ ሆኖም መንፈሳዊነት በተፈጥሮና በፍጥረት የተወሰጠ እውነት ነው እንዳሉ የገለጡ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው እ.ኤ.አ. ጥር 24 ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጋዜጠኞች ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ባከበረችበተ ዕለት የኔታ ቪጋኖ በዚህ በቫቲካን ረዲዮ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን አባላት የተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ አገልግሎታችን ገንቢና የልዩነት አንዱን ሌላው የሚያገል የግንብ አጥር ተወግዶ አገናኝ ድልድይ ለመገንባ የሚደገፍ መሆን አለበት የሚል ቀዉም ሃሳብ ያማከለ ስብከት ማስደመጣቸው አስታውቋል።