Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ንግግሮች

ቅዱስ አባታችን ከኤል ፓይስ ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ኤል ፓይስ ለተሰየመው የስፐይን ዕለታዊ ጋዜጣ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓብሎ ኦርዳዝ ላቀረቡላቸው መጠይቅ የሰጡት መልስ እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጋዜጣው ባወጣው ኅትመቱ አስነብቧል።

ቅዱስ አባታችን በሰጡት መልስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው መመረጣቸው ያስከተለባቸው ምንም ለወጥ የሌለ ቢሆንም። ሁሉን ለማድረግ የሚፈልጉት ነገር እንዳያደጉ ያላገደባቸው ቢሆም ሁሌ ይመኙት የነበረው የጎዳና ካህን የመሆን ፍላጎታቸው ለመከወን እንዳይችሉ ቢያደርግም ይኸንን ፍላጎት ለየት ባለ መልኩ እየኖሩት እንደሆነም ገልጠው፡ ከሕዝብ እርቃ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ታስፈራኛለች። ቤተ ክርስቲያን ፈሪሳዊነት ከሕዝብ መራቅን ስትኖር ገዛ እራሷን ከዚህ በላይ ገዛ እራሷን ለመጉዳት አትችልም። ህያው ያልሆነች ቤተ ክርስቲያን ሙት ነች። መንግሥታዊ ያልሆነ የግብረ ሠናይ ማኅበር፡ ለግብረ ሠናይ በጎ ፈቃደኞችን የምታደራጅ የእርዳታ ተቋም ልትሆን ትችላለች። ህያውነቱ ግን አይኖራትም። በወንድና በእህት በድኻው አማካኝነት የጌታን ሥጋ መንካት። ማቴዎስ ወጌንጌል ምዕ. 25 የምትኖር ቤተ ክርስቲያን፡ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ተጠምቼ ተርቤ….አጠጣችሁኝ መገባችሁኝ…”  የሚለውን መኖር ነው፡

እርግጥ ነው ምግባረ ብልሽት ሰው ባለበት ሥፍራ ሁሉ አለ። ነገር ግን የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ተቋማትን ብቻ መተቸቱ ተገቢ አይደለም።  በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምግባረ ብልሽት ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፡ ግብታዊ ሥር ነቀላዊ ለውጥ የሚቀሰቅሱ ብዙ ቅዱሳንም አሉ። እውነተኞች የቤተ ክርስቲያን ዋና ተወናያን ቅዱሳኖች ናቸው። ካህን የቤተሰብ አባት እናት ዓላማዊ ምእመን ሳይል ወንጌልን የሚኖ ቅዱስ በቤተ ክርስትያን ውስጥ አለ። ዕለታዊ ሕይወታቸውን ሰብአዊ ክብራቸውን ሳያዋርዱ የሚገፉ አባቶች እናቶች አያቶች አዛውንቶች ቤተ ክርስቲያንን ወደ ፊት እንድትል የሚያደርጉ ቅዱሳን አሉ።

እሳችው እየከወኑት ያለው ህዳሴ የካቶሊክ ጠመቅ ትምህርት የሚያስክድ ነው የሚል ትችት ከባህል አቃብያን የቤተ ክርስቲያን አባላት ዘንድ  ሲቀርብ ይሰማል ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ። እኔ ምንም አይነት አብዮት እያራመድኩ ሳይሆን ወንጌልን ነው ወደ ፊት እንዲል እያደረግኩ ያለሁት። ወንጌል በመሠረቱ እንቅፋት ነው። በዚህ  ጉዞ ለብቻቸው እንዳልሆኑና በሁሉ ወጣቶች አዛውንቶች የሚረዱዋቸው ህይሉ አብሮአቸው የሚጓዙ መሆናቸ ገልጠው። የማይደግፍ የሚቃወም ካለ በእውነቱ  ከሁሉም ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነኝ። ድንጋይ መወርወር አልወድም። ከሁሉም ጋር መወያየት፡ ግልጽ ውይይት እንጂ፡ ሐሜታና ስም ማጥፋት አያስፈግም።

የአርነት (የነፃነት) ቲዮሎጊያ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው ሲመልሱ፥ ይኽ የአርነት ቲዮሎጊያ በላቲን አመሪካ አወንታዊ ተመክሮ እንዳለው ሁሉ አሉታዊ ገጽታም ነበረው። አሉታዊው ገጽታውም ተጨባጩን ሁነት በማርክሳዊ ርእዮተ ዓለም ሥር ለመተንተን መሻት ነው። ስለዚህ ቫቲካን ይኽ ቲዮሎጊያ ውጉዝ በማለት መልስ የሰጠው እንደሚታወቀውም ቅዱነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት ለሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅይንተ ብፁዕ ካርዲናል ራትዚንገር እያሉ ነበር በሰጡት የማብራሪያ መልስ፥ አወንታዊ ገጽታውን እወቅና በመስጠት ያንን የአርነት ቲዮሎጊያ ተገን በማድረግ ተጨባጩን ሁነት በማርክሳዊ ርእየት የመተንተኑ ተግባርን ግን ቤተ ክርስቲያን ውጉዝ ብላዋለች፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ውጉዝ ያለቸው ይኸንን ሁለተኛውን ግጹን እንጂ ጠቅለል ባለ አነጋገር የአርነት ቲዮሎጊያን አይደለም።

በመቀጠልም ዓለማችን እየኖረው ያለው እሳቸው እየተገማመሰ የሚካሄድ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት የሚሉት ሃሳብ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሲመልሱ፥ ያለው ኢፍትሃዊ እክልነት አልቦ የሆነው የኤኮኖሚ ስልት ወይንም ሥርዓት፡ እጅግ በቁጥር አናሳ የሆነው የዓለም የኅብረተሰብ ክፍል ከጠቅላላው የዓለም ሃብት ውስጥ 80 መቶኛውን የሚሸፍነውን ባለ ቤት ሆኖ ማየቱ እግጅ የሚያሳዝን ነው። ይኽ ደግሞ ምን ያክል ገንዘብ ተመላኪ መሆኑ ያረጋግጥልናል። ይኽ ነው ገዳይ የኤኮኖሚ ስልት የሚባለው። ይኽ ኤኮኖሚ ብዙዎች እንደ ጥራጊ የሚጥል የሚያገል ነው።

አዲሱ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእስ ብሔር ትራምፕ በተመለከተም ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡ አስቀድሞ አስተያየት መስተጠት እንደማይወዱ ተግባርን ማየትን እንደሚወዱ ጠቅሰው። ክርስትና ተጨባጭ ነው። በመሆኑም ነገሮችን በተግባር ሲታይ ተጨባጭ አስተያየት እንደሚሰጡበት ገልጠዋል፡ የማንነትን መለያ ለያይ ግንቦችን በመገንባት፡ በእሾኻማው አጥር ድንበርን በመከለል በማረጋገጥ መለያህንከሚበክል ሁሉ አድንሃለሁ የሚሉት የሐሰት አዳኞች አሉ። ለዚህ ነው ከሚለያይ ግንብ ይልቅ አገናኝ ድልድይ በማቆም መወያየት ያስፈልጋል የምለው ብለው። መቼም ቢሆን መወያየት ይበጃል፡ ስደተኛውን ማስተናገድ መብቱንና ግዴታውን ማሳወቅ። ማንኛውም አገር ድንበሩን የመከላከል መብት አለው ነገር ግን ሕዝባቸውን ከጎረቤት አገር ጋር እንዳይወያይ የማድረግ መብትም ሆነ ሃላፊነቱ አልስተሰጣቸውም። ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ነው የምታሳስበው። ማስተናገድ በሰላም አዋህዶ ለማኖር ማነጽ ትላለችች በቀዳሚነትም ተወናያን በመሆን በቃልና በሕይወት እየስመሰከረቸው ትገኛለች፡ አዳዲስ የባርነት ሥርዓቶች ሰውን ለክብር ሰራዥ ተግባር የሚዳርጉ፡ ተባዕተኛነት የሚያረማምዱ ሴቶችን የበታች የሚለውን ርእዮተ ዓለም የሚያረማምዱ፡ ጸያፍና ጎጂ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚሰርዝ ተግባር ሁሉ ውጉዝ ነው።

በመቀጠልም ስለ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጤንነት ጉዳይ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥይቄም ሲመልሱ፥ እርግጥ የእግር ችግር አለባቸው ሆኖም የአምሮአቸውን የመዘከር ብቃቱ የሚደንቅ ነው። በምርኩዝ ነው የሚራመዱት ሆኖም የማስታወስ ብቃታቸውና ያላቸውም የመዘከሩ ኃይል ከወጣት አምሮ ጋር ተስተካካይ ነው። በመጨረሻም ተሌቭዥን ይመለከታሉን ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ፡ ተሌቭዥን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 1990 ዓ.ም. ወዲህ ማየት ማቆማቸውና ከዚያች ቀን ወዲህ ተሌቭዥን አይተው እንደማያውቁ ገልጠው። ይኽ ደግሞ በጸሎቴ እግዚአብሔር የጠየቀኝ ጉዳይ ነው፡ ተሌቭዥን ባለ ማየቴ ምንም አልቀረብኝም እንዳሉ ኤል ፓይስ ካወጣው ኅትመቱ ለመረዳት ተችሏል።