Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ንግግሮች

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ኢዮቤል ርእሰ ጉዳይ ያደረገ ትርኢት አዘጋጆችን ተቀብለው ምዕዳን ለገሱ


ባለፈው ዓመት ጥንታዊ እሴት በሚል ርእስ ሥር በኢጣሊይ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የተኖረው ቅዱስ የምሕረት ዓመት ምክንያት የቅዱስ ኢዮቤዩ ዓመት ጅማሬ የኢዮቤልዩ ታሪካው መጽሓፍ ቅዱሳዊ ታሪክ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የኢዮቤዮ ዓመት እወጃዎች ያወጁበት የውሳኔ ሰነዶች ያካተተ የኢዮቤል ተራኪያን ስእሎች ቅቦች ሰነዶች በኢጣሊያ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ሕንፃ ለትርኢት እንዲቀርብ በማድረግ  ረገድ የተሳተፉትና አዘጋጆችን እ.ኤ.አ. ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር መገናኘታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ አስታወቁ፡

ቅዱስ አባታችንን የትርኢቱን አዘጋጆችን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን፥

ከኢይቤልዩ ዘላቂነት ያለው መፈሳዊ ስጦታዎች መታደል

ባለፈው ዓመት ታሕሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጠናቀቀው ቅዱስ የምሕረት ዓመት ዘላቂነት ያለው የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ስጦታዎችን አብዝቶልናል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይሊኖ አያይዘው ያ ትርኢት ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር የኢጣሊያ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፒየትሮ ግራሶ በተገኙበት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን መርቀው እንደከፈቱትም አስታውሰው፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከ1300 ዓ.ም. ወዲህ የኢዮበልዩ ዓመት ሮማን ምንኛ እንደነካና ታሪኳንም ጭምር የለወጠ የመፈሳውያን ነጋድያን ጸአት ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢዮበልዩን በሚያንጸባርቅ ስልት በመከተል የተገነቡ ሕንፃዎች መንገዶች የግብረ ሠናይ ማእከሎች መፈሳያን ነጋድያን ለማስተናገድ የተገነቡ ማእከሎች በጠቅላላ በዛሪይቱ ሮማ የሚነጸባረቅ ነው። የኢዮቤልዩ ታሪኮች በተጨባጭ የሚነበብባት ከተማ ሆናለች ብለው፥ በኢዮቤዩ ዓመት የእግዚአብሔር ደግነትና ያ ዘወትር የእግዚአሔር ፍቅርና ምሕረት የሚሻው የሰው ልጅ ደካማነት የሚገናኙበት ቅዱስ ወቅት ነው። እግዚአብሔር ዘወትር በምህረቱና በፍቅሩ እኛን ከመፈለግ አይቦዝንም ስለዚህ የምሕረት ዓመት ሰውን ደካማነቱን ተረድቶ ያንን ከአብ የሚመጣውን ምሕረትና ፍቅር እንዲያስተዋልና እንዲቀበልም ነው። እግዚአብሔር አለ ምንም የጥያቄ ውርጅብኝ በእቅፉ የሚቀበል አብ ነው። የሚምር አባት ነው። እኛን ለማቀፍ ሁሌ የተዘረጉ እጆች ያሉት ልጄ የሚል አባት ነው፡ የኢዮቤዩ ዓመትም ይኸንን ነው የሚያረጋግጥልን እንዳሉ አስታውቋል።

የኢጣሊያው የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፒየትሮ ግራሶ በበኩላቸውም ያንን የኢዮበልዩ ትርኢት አዘጋጆች ትርኢቱን በማዘጋጀቱ ሥራ የተሳተፉትን የበጎ ፈቃድ አባላት ሁሉ አመስግነው ያ ትርኢት በእምነትም ሆነ በኢጣሊያ ባህል ዙሪያ አቢይ መልእክት ያስተላለፈ የምሕረት ጸጋ ነው ለማለት ይቻላል እንዳሉ አኵይሊኖ ገልጧል።

ትርኢቱን ለማዘጋጀት በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሥር የሚተዳደረው የቫቲካን ሓዋርያዊ ቤተ መዝገብና በኢጣሊያ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት መካከል የአተሄደው ግኑኝነት ያስገኘው አመርቂ ውጤት መሆኑ ግራሶ አስታውሰው በኢዮበልዩ ዓመት ትብብር መቀራረብ ግብረ ሠናይ የመሳሰሉት እሴቶች የሚጎባላበ ወቅት መሆኑ ሮማ በተግባር ያየቸው መፈሳዊ ገጠመኝ ነው በትርኢቱም ይኽ እውነት ተንጸባርቋል እንዳሉ አኵይሊኖ አስታወቁ።