Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ግብረ ሠናይና ትብብር

የሕፃነ ኢየሱስ ማከሚያ ቤት ሊቀ መንበር ኤኖክ ለቀጣይ አራት ዓመት ዳግም ተመረጡ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ንብረትነቱ የቅድስት መንበር የሆነው የታዋቂው የሕፃነት ኢየሱስ ማከሚያ ቤት የመስተድድር ሸንጐ ሊቀ መንበር በመሆን ላገለገሉትና ያገልግሎት ዘመናቸው ላጠናቀቁት ለማሪየላ ኤኖክ ለቀጣዩ አራት ዓመት በዚሁ ስልጣናቸው እንዲያገለግሉ ዳግም እንደሸሙዋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ፡

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የኤኖክ አገልግሎትና ያሳዩት ትጋትና የአመራር ጥራት ክህሎቻቸው ሙያዊ ብቃታቸውን ሁሉ በማድነቅ በዚሁ ተልእኮ ቅድስት መንበር ለቀጣይ አራት ዓመት እንዲቀጥሉበት ዳግም ስሜቱን እንደሰጠቻቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ፥ ማከሚያ ቤቱ የተቀዳጀው ሕዳሴ ለውጦች አገልግሎቱ ወንጌላዊነt የተላበሰ መሆኑ የሚያሳስብ ወንጌላዊነትን እንዲያጎላ በማድረጉ ረገድ እጹብ አገልግሎት ሰጭ እንዲሆን በሚያበቃው መንገድ በመምራት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የግብረ ሠናይ አገልግሎት በምሉእነት እንዲኖር በማድረጉ ረገድ ለእነዚያ በጠና ለታተሙት ከተለያዩ አገሮች ለሚመጡት ሕፃና የሕክምና ሰብአዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በማቅረብ ለወላጆቻቸውም ጭምር በዚህ ጉዞ በመሸኘት ሂደት የሚሰጠው አገልግሎት በመምራት ኤኖክ ላሳዩት የመሪነት ብቃት ቅድስት መንበር አድናቆቷን በመግለጥ ዳግም ለቀጣይ አራት ዓመት የማከሚያ ቤቱን መስተዳድር ሸንጎ እንዲመሩ መወሰኗ ያመለክታል።

ማሪየላ ኤኖክ እ.ኤ.አ. በ 1944 ዓ.ም. በኢጣሊያ ኖቫራ ከተማ የተወለዱ በብሉይ ሥነ ጽሑፍና በሥነ ሕክምና ሊቅነት ያስምሰከሩ በሕክምና ቤቶች መስተዳድራዊ መዋቅሮች ዙሪያ ያገለገሉና በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚነገርላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ. የካቲት 2015 ዓ.ም. የሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት የመስተዳድር ሸንጎ ሊቀ መንበር እንዲሆኑ በቅድስት መንበር መሾማቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት የካቶሊክ ጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገትና በኮሞ የቫልዱቸ ማከሚያ ቤት ነገር ፈጅ የካሪፖሎ ማኅበር ምክትል ሊቀ መንበር የኢስሙ ማኅበር ሊቀ መንበር የፒዮሞንተ የሥነ ምስራቅ መንበረ ጥበብ ምክር ቤት ሸንጎ አባል መሆናቸውም ይነገራል።

ሕፃነ ኢየሱስ ማከሚያ ቤት እ.ኤ.አ. በ1869 ዓ.ም. በሳልቪያቲ መሳፍንት የተቋቋመና በ1924 ዓ.ም. ለቅድስት መንበር በውርስነት የተሰጠ ሆኖ ንብረትነቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ማከሚያ ቤት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደር ሆኖ ይኸው እስካሁን ድረስ በውስጥና በውጭ አገሮች ሁሉ ትልቅ እውቅና ያለው ሲሆን 607 የማገገሚያ መኝታ ቤት ያለው በማከሚያ ቤቱ የሚተዳደሩት 4 ቅርንጫፎች ያሉት በሥነ ሕፃናት ህክምና ምርምር የተሟላ አገልግሎት መስጫ ያካተተ በተለይ ደግሞ የሕፃናት የተወሳሰቡ በሽታዎች የሚባሉትን የሚያክም በኤወሮጳ ትልቅ ተብሎ የሚነገርለት ከተለያዩ የዓለማችን ክልሎች በጠና በሽታ የተጠቁትን ሕፃናት በማስመጣት የሚያክምና በዚሁ ዘርፍ አቢይ ግብረ ሠናይ ፈጻሚ መሆኑም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ በማስታወስ ይጠቁማል።