Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ወጣቶች

ዝክረ መቶኛው ዓመት የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ቃኝ ቡድን (እስካውት)ምሥረታ


በኢጣሊያ የቃኝ ቡድን (እስካውት) ምሥረታ ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘቨላብሮ ባሲሊካ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በዚህ የቃኝ ቡድን ሥር የሚታቀፉት የተለያዩ የእስካውት ማኅበራት አባላት ወጣቶች በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፥ እስካውት የመሆን ምርጫ የሕይወት ጥሪ ነው። ጉዞአችን ከጸሐይ በታች ባሉት የተፈጥሮ መልክኣ ጸጋ፡ በተፈጥሮ ውበት የመንፈስ እርካታ በሚደመጥበት ሁሉ ዝናባማና ጥቅጥቅ ያለ ጉም ለበስ የተሞላበት ሁነት ሊሆን ይችላል በዚህ ሁሉ ማለፉ የእግዚአብሔር ቃል በማስቀደምና በጋራና በግል በማንበብ ወይንም በኅሊናችን የሚናገረውን ቃለ እግዚአብሔር በማስተዋል ሁሉን እንወጣለን። የመወጣጫ መንገድ የሌለ ሆኖ ሲሰማን ቃሉን በውስጣችን ማዳመጥ ካሰብነው በላይ የመወጣጫውን መንገድ ቦግ ብሎ እናገኛለን። ቃሉ መንገድ ብርሃን ሕይወትም ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኤውጀኒዮ ሙራሊ አስታወቁ።

የኢጣሊያ ካቶሊካዊ እስካውት ማኅበር ሊቀ መንበር ማሪለና ላፎርጃ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ እስካውትነት ሕንጸት ነው። አንድ ትልቅ የሕንጸት ሥልት ነው። ዘመናት ቢቀያየሩም ትውልድ ቢቀያየርም ዓላማው ማራኪ ከመሆኑ ባሻገር እስካውትነት እምነት ያጣመረ በመሆኑ ያለው እሴት ሁሌ አዲስ እየሆነ በመቀጠል ይኸው አንድ መቶኛው ዓመተ ምሥረታውን ለማክበር ተበቅቷል ሲሉ ቀጥለውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የኤውሮጳ እስካውት ማኅበር አባል ወጣት ማራ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥  እስካውትነት በሕይወታቸው አቢይ ሥፍራ እንዳለው ገልጠው እስካውት የሚከተለው ደንብና ሕግ የእስካውትነት ወግና ባህል ከውጭ የሚሰጥ ሳይሆን በእስካውትነት ውስጥ ያለ ነው ስለዚህ አባል ስትሆን ይኽ የምትከተለው የእስካውት መመሪያ ሁሉ በውስጥህ እንዳለ ታስተውላለህ። የእምነት ጉዞም ነው። ስለዚህ አብሮ በመጓዝና በመጸለይ በማደግም ወደ ቀና መንፈስ ወጣቱን በመማረክ ጤናማ ኅብረተሰብ በመገንባቱ ረገድ አቢይ አስተዋጽኦ የሚያበረት የሕይወት ስልት ነው ብሏል።

የኤውሮጳ እስካውት ማኅበር ለኢጣሊያ ተጠሪ አንቶኒዮ ዞኮለቶ ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ እስካውትነት ጸሎት ነው። እስካውትነት ኅብረት ሰላም አንድነት ነው። እንዲህ በመሆኑም ዛሬም ቢሆን በአዲስ አባላት ከፍ እያለ በቤተ ክርስቲያን ውስጥና በማኅበራዊ ዘርፍ ሁሉ አቢይ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ጤናማ ዜጋ አፍሪ ስልት ነው ብሏል።

በዚህ ዝክረ መቶኛው ዓመተ ምሥረታ ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከገዛ እራስ መውጣ፡ ወደ የከተሞቻችንና ወደ የኅልውና ጥጋ ጥግ እንበል። እንደ ክርስቶስ ወደ ማለት የሚሉትን፡ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ እግዚአብሔር ከገዛ እራስ ወጥቶ እኛን መስሎ መጣ የሚለውን እውነት የሚያስተጋባው ስልጣናዊ ትምህርት ማእከል ያደረገ መሆኑም ገልጧል።

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ባስደመጡት ስብከትም ለማግኘት ማጣት የሚለው የኤኮኖሚ አመክንዮ የሚጻረር የክርስትና ብሂልና ተግባርም ነው። እስካውትነትም ይኸንን ትምህርት የሚያስተጋባ መሆኑ ገልጠው ለማግኘት በነጻ መስጠት ነው፡ ይኽ ደግሞ ዓለም ከሚያስተምህረው ትምህርት ጋር የሚጻረር ነው። ክርስትናችን ጸጋ ነው። ይኸንን ጸጋ እንደየጥሪያችን ልንመሰክረው ተጠርተናል እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ሙራሊ አስታወቁ።