Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ቤተ ክርስትያን / ኤርትራ

የአስመራ ካቶሊካዊ መንበረ ኤጳርቅና ልሂቅ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ ዜና ዕረፍት


የኣስመራ ካቶሊካዊ ኤጳርቅና  ጳጳስ በመሆን ለ20 ዓመታት እንዲሁም ልሂቅ ጳጳስ በመሆን እስከ መጨረሻ ለ15 ዓመታት በአጠቃላይ ብጵጵስና ለ35 ዓመታት በክህነት ለ67 ዓመታት በታላቅ መንፈሳውነትና ትጋት ያገለገሉ ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ ዮሓንስ ትላንትና ጥዋት ኣንድ ሰዓት ላይ በሞተ ጻድቃን በ91 ዓመት ዕድሚያቸው ከዚህ ዓለም እንደተለዩ ከኣስመራ የወጣ ዜና ኣመልክተዋል፣ ቀብራቸውም ነገ ቅዳሜ እኢአ ሕዳር 24 ቀን 2009 ዓም እኩለ ቀን ላይ ትውልድ መንደራቸው ዓዲጀኑ ወረዳ ማይ ጻዕዳ በድሮው አጠራር በሰራየ ኣውራጃ እንደሚካሄድ ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ ዜና ኣመልክተዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ካህናት ታሪክ ጸሓፊ የሆኑ የሲታውያን ማሕበር ኣባል ጥቀ ክቡር ኣባ ብሩኽ ወልደጋብር ያቀሩቡት የነፍሰሄር ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ ኣጭር የሕይወት ታሪክ ኣጠር ባለ መልኩ እናቀርብችኋለን፣

ነፍሰሄር ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ ከኣባታቸው ኣቶ ዮሓንስ ገብረመድህንና ከእናታቸው ወይዘሮ ምሕረት ተሰማ በዓዲዜኑ ወረዳ ማይጻዕዳ እኢአ ግንቦት 5ቀን 1917 ዓም ተወልደው ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ኣንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዓድዜኑ ኣጠናቀቁ፣ ስመ ጥር ኣባታቸው ኣቶ ዮሓንስ ገዛራሳቸው ካህን ለመሆን ብርቱ ፍላጎት ቢኖራቸውም ሊሳካላቸው ባለመቻሉ ቢያንስ ከልጆቼ ለዚህ ኣገልግሎት የሚሆን እግዚኣብሔር ሊፈቅድ ይጸልዩ እነበረ እግዚኣብሔርም ልመናቸውን በሁለት ካህናትና ኣንዲት ድንግል እንደመለሳቸው በኲር ልጃቸው እናቴ ጽርሐ-ማርያም (እናቴ ባቲስቲና) የኮምቦኒ ልዑካን ደንግል ኣባል ኣባ ዘካርያስ የሰበካ ካህን ኣባ ሃብተጊዮርጊስም የሲታውያን ማሕበር ካህን ሆኑ፣

በዚህም ነፍሰሄር ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ ኣንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁና ግብረ ዲቊናና ዜማን በሊቀ ሊቃውንት ቄስ ወልደማርያም ክፍሉ ስር ተምረው ከፈጸሙ ከረን በነበረው ዘርአ ክህነት ገብተው ኣስፈላጊውን ትምህርት ከቀሰሙ እኢኣ ግንቦት 25 ቀን 1941 ዓም ከነፍሰሄር ጥቀ ክቡር ኣባ ጴጥሮስ ካሕሳይ በኣንድነት በዓዲዜኑ በብጹዕ ኣቡነ ኪዳነማርያም ካሳ እጅ መዓርገ ክህነት ተቀብለዋል፣

ለጥቂት ግዜ በኤርትራ ካገለገሉ በኋላ በደቡብ ኤትዮጵያ ለስብከተወንጌል በ1945 ዓም ተላኩ፣ መጀመርያ በወላይታና ሰዶ ከዛም በሶዶ ዱቦ እንዲሁም በጫጫ በሮዶ ተኣምር የሚያሰኝ ሓዋርያዊ ኣገልግሎት ለኣራት ዓመታት ካገለገሉ በሂኣላ በደሴ ከተማ ለሶስት ዓመታት ኣገልግለው በኣዲስ ኣበባ ለሌላ ኣገልግሎት ተዘወሩ፣ በኣዲስ ኣበባ ሃገር ስብከት የቤተ ሊቀ ጳጳስ መጋቢ እንዲሁም በመንግስት የቤተክህነት የገዳማውያንና የገዳማውያት ተወካይ በመሆን ለ14 ዓመታት የደብረ ልደታ ለማርያም ቆሞስ በመሆን ደግሞ ለ9 ዓመት ኣገልግለዋል፣ በኣገልግሎታቸው ሁሉ ደስ ብሎት እያመሰግናቸው ሳለ በቤተክርስትያን ውሳኔ እኢኣ ጥር 21 ቀን 1973 ዓም ጳጳስ ተሽመው መጀመርያ የኣስመራ ሃገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ በመሆን ከዛም ኣስተዳዳሪና ጳጳስ በመሆን ለ35 ዓመታት እንደ ጳጳስ ኣገለገሉ፣

ነፍሰ ሄር ብጹዕ ኣቡነ ዘካርያስ በዚህ ኣገልግሎታቸው ሁሉ ያሳዪት ታላቅ መንፈሳውነት ትጋትና ፍቅር በሚያውቃቸው ልብ ሁሉ የተቀረጸ ሲሆን በስልጣን በነበሩበት ዘመን ምንም እንኳ ኣብዛኛው ግዝያቸው በውግያ በድርቅና በልዩ ልዩ ችግሮች የተከበበ ቢኖር ለወገን ተቆርቋሪ በመሆናቸው ቈራጥ መሪ በመኖራቸው ቤተክርስትያንና የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በማዋሃሃድ ብዙ ሰው ከሞት ኣትረፈዋል፣ እንዲሁም በትምህርቶቻቸውና ስብከቶቻቸው እምነት ለማጎልበት ቤተክርስትያኒቱም በሚያስፈልጋት መንፈሳዊ ቁሳዊ ነገሮች ከፍ እንትድል ያደርጉ ኣስፈላጊ ሆኖ በሚግኝበት ጊዜም ስለ ፍትሕና ነጻነት ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ኣለምንም ፍራቻ ይናገሩ ነበር፣