Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ግብረ ሠናይና ትብብር

ቅዱስ አባታችን፥ በነቢያዊነት መንፍፈስ ሰውን ልጅ የሚዋርድ ተግባር ሁሉ አምቢ በሉ


በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና ካቶሊካውያን የግብረ ሠናይ ማኅበራትን የሚያቅፈው ጳጳሳዊ ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር በተለያዩ አገሮች ለሚገኙት ቅርንጫፎቹ አስተዳዳሪዎች በጠራው ዓውደ ጉባኤ ተሳታፍያንን ተቀብለው ቃለ ምዕዳን መለገሳቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቤተ ክርስቲያን ህልውና ወንጌላዊነትን ልኡካነ ወንጌላዊነት ነው። ሆኖም ወንጌላዊነት ከሚያጋጥመው ከተለያዩ ሁነት ጋር ሊሰምርና የቤተሰብ የማኅበራዊ ሕይወት ሰላም ፍትሕና ምሉእና ተቀባይነት ያለው ልማት ተኰር የሆነ ዓለም አቀፋዊ ሕይወት ጭምር ግምት የሚሰጥ መሆን አለበት። የቤተ ክርስቲያን ልዩ ትኵረት ድኾች ላይ ነው። ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ አግላይ ሂደቶችን ትቃወማለች መቃወም ብቻ ሳይሆን የተነጠሉትን ተገለው የሚኖሩትን የሁሉም ድኾች ጠበቃም ነች።

የምንኖርበት ወቅታዊው ባህል ነጣይ አግላይ ብሎም ሁሉም የሌለው እንዲሆን የሚያደርግና ሁሉንም ያጣውን ደግሞ እንደ ጥራጊ የሚያይ ነው። ስለዚህ መተባበርና ተጋርቶ መኖርን ለመማር ግዴለሽነትንና በእራስ ላይ ታጥፎ መኖርን እኔነትን አማክሎ ሌላውን ከመዘንጋቱ አዝማሚያ መላቀቅ ያስፈልጋል።

የቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት የማኅበራዊ ድርጅቶች ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የሚጋሩ የቤተ ክርስቲያን ተቋሞች ናቸው ስለዚህ በወንጌል ብርሃንና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት አማካኝነት ድኾችን በማስስተባበር በመደገፍ ተመጽዋች ሆነው እንዲቀሩ ሳይሆን የገዛ እራሳቸው ልማት ቀንደኛ ተወናያን እንዲሆኑ በሚያደርግ ተግባራዊ እይታ ፍቅርና ፍትህ በዓለም ደምቆ እንዲበራ የሚያደርጉ መሆናቸው ሊስተዋል ይገባዋል። ድኽነት እርሃብ በሽታ ጭቆና ዕጣ ፈንታ ወይንም ዕድል አይደለም። ስለዚህ ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስና በውስጡ የሚያቅፋቸው የተራድኦ ማሕበራት በወንጌል ብርሃን ተመርተው ሰብኣዊነት ልክነት የለሽ የሆነው ሁሉም ዓይነት ሂደት እንዲቀየር ለማድረግ የሚደግፉ የሚተባበሩ የቤተ ክርስቲያን ተቋማት ናቸው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሉንም የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ አባላትና በጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት ነቢያዊ ጽናት በመኖር ማንኛውም ዓይነት ሰው የሚያዋርድ ተግባር ሁሉ እንዲቃወሙ አደራ። ያንን የሕጻናት የአረጋውያንን እንዲሁም ሰላም ለመሻት የሚሰደዱትንና የሚፈናቀሉትን የማስተናገድ የመደገፍ ተግባር በመኖር የትብብርና የአስተናጋጅ ባህል ምልክቶች ሆናችሁ ተገኙ። ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ በሚያደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ በጣም ደስተና ነኝ በተለይ ደግሞ በቅርቡ ስደተኞች ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ የሚያነቃቃው ዘመቻ ስደተኞች ተፈናቃዮች በገቡበት አገር ሁሉ ለሌላ ችግር የሚዳረጉ መጻእተኞች ሆነው ከመኖር ተቀባይነት ያገኙ ቤተኛነት እንዲሰማቸው የሚደግፍ እቅድ እርሱም ሐሰተኛው ሰብኣዊ ያማከለው መሳይ የኤኮኖሚና የልማት እንዲሁም ግጭትና አመጽ በሚታይባቸው ኣገሮች ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረጉ የሃሰት ሙከራዎችና አሰመሳይ ሽምገላ ሁሉ የሚያጋልጥ ሲሆን ወደ እውነት ፍትህ ፍቅር ሰላም የሚመራ መንገድ አመልካቾች ናቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሥር የሚታቀፉት የካቶሊክ የተራድኦ ማኅበራት በሕዝቦች በማሕበረሰቦች በአገሮች በአማኞች መካከል የሰላም የእርቅ ሙያተኞች ሆኖ እንዲገኝ ቅዱስነታቸው በማሳሰብ ከሌሎች የሃይማኖት የግብረ ሠናይ ተቋማት ጋር በመተባበር የፍቅር አገልግሎት በመስጠት ተልእኮ እንዲተጉ አደራ ከድኾች ተማሩ ከድኾች ጋር ሆናችሁ ድኽነት ተዋጉ በድኽች ትህትና አስፈላጊ ነገር የሆነውን ብቻ በማግኘት መኖርን ተማሩ እነርሱ የዚያ ጌታና አዳኝ የሆነው በእግዚአብሔር ላይ እምነቱን ያኖረ የክርስቶስ ስቃይና አካለ ክርስቶስ ናቸው። ሕይወታቸው ጸሎትና በእግዚአብሔር ለመተማመን ተግባር አብነት ናቸው በማለት ያስደመጡት ቃለ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።