Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ወጣቶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ዓለም ለመለወጥ ነው የተፈጠርነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በምሕረት አደባባይ ልክ 6 ሰዓት ተኩል ደርሰው እዛው በሁለት ሚሊዮን በሚገመቱ ወጣቶች አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በአምስት ወጣቶች ተሸንተው ቅዱስ የምህረት በር ከተሻገሩ በኋላ በተዘጋጀው የዋዜማ ጸሎት በመሳተፍ መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ከምን ጊዜም በበለጠ ዓለማችንና እኛም ወጣቱ ትውልድ ያስፈልገናል። የደረሰው ዓለም ስጋት ነው ብሎ በሚገልጠው በኅብረ ባህል ቋንቋ ውስጥ አብሮ በሰላም መኖር የሚቻል መሆኑ ምስክሮችና አስተማሪዎችም ናችሁ፡ ኅብረአዊነት ስጋት ሳይሆን መልካም አጋጣሚ መሆኑ ታረጋግጣላችሁ። የሚለያየው ግንብ ከመገንባት ይልቅ አገናኝ ድልድይ ለመገንባት እጅግ የተዋበና ማራኪ መሆኑ ትመሰክራላችሁ።

በታደሰ መንገድ ተጓዙ ሐሴትን አዛምቱ እንጂ በደስታ ወንበር አትወዘፉ

በተለያየ ኅብረ ቀለም የተዋቡ እጆች ሲጨባበጡና በአንድ ላይ ወደ ሰማይ ሲያቀኑ ማየት የሱታፌና የእርቅ ትእምርት ነው። በዚህ በምህረት ቀለማት በቀይና ሰማያዊ መብራት ባሸበረቀው የክራኩፍ የምሕረት አደባባይ የቅርብና የሩቅ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ወጣቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ በዓለም አብሮ መጓዝ የሚቻል መሆኑ በመመስከር ያንን ጊዚያዊነት የሆነው ነገር ወደ ጎብ በማድረግ ዘላቂነት ያለው ሰላም ደስታ እንድንፈልግ ጥሪ አቅርበዋል። ተሳቢ ያንቀላፉ አሻንጉሊ የሆነ ሕይወት የምትኖሩ ናችሁ ወይ የሚል ጥያቄ ቅዱስ አባታችን በዋዜማ ጸሎት ለተሰበሰቡት ወጣቶች አቅርበው ወጣቱ አይደለንም በማለት በአንድ ላይ መልስ ከሰጡ በኋላ ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ነጻነታችሁን ተከላከሉ የነጻነታችሁ ቀናተኞች ሁኑ።

ቃኤልነት ምክንያታዊ አታድርጉ

እነዚህ በቅዱስ አባታችን ዙሪያ በመሆን ያንን ገዛ እራሱን አሰላፎ የሰጠንን የጌታችን እየሱስ ክርቶስ ቅዱስ ቁርባን ፊት በጸሎትና በአስተንትኖ በመኖር ለተገናኘው ወጣት ቅዱስነታችውን በጦርነት ግጭትና ውጥረት ባለበት ክልል የሚኖሩትን ወጣቶች በማሰብ እነዚህ ወጣታቶች ቁጥር ወይንም የመገናኛ ብዙሃን ዜና ሳይሆኑ ስም መለያና ታሪክ ያላቸው ናቸው። የሚረሳ ኅብርተሰብ የተረሱ ከተሞች መባሉ ይቅር። በጦርነት ለሚሰቃዩት ወጣቶች እንጸልይ። ቃዔልነት ወይንም የሚፈሰው የወንድም ደም ምክንይታዊ እናድርግ እንዳሉ ኦንዳርዛ ገለጡ።

ቀንደኛ ተወናያን ሁኑ ሽባ የሚያደርገው ፍርሃት በክርስቶስ ይሸነፋል

ወጣቱ በዚያ የምህረት አደባባይ የሚንጸባረቀው የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና የቅድስት ፋውስቲና አብነት በመከተል ምሕረት እንዲኖር ቅዱስ አባታችን አደራ በማለት ከክርስቶስ ጋር ፍርሃትን በማሸነፍ እያንዳንዳችሁ ያንን እግዚአብሔር ዓለምን ትለውጡ ዘንድ የሚያቀርብላችሁ ጥሪ ተቀበሉ። ወንድማማችነት ወዳጅነትና ግኑኝነት የሚነጥቀው ሽባ የሚያደርገውን ፍርሃት ከክርስቶስ ጋር ሆናችሁ ድል አድርጉ።

ሌላውን ለመቃወም ድምጻችን አናነሳም ለመጣላት ለማውደም እንተባበርም። ጥላቻን በጥላቻ ለማሸነፍ አመጽ በአመጽ ለመርታት ሽበራ በግብረ ሽበራ ለማሸነፍ እንፈልግም። ወድማማችነት ሱታፌና አንድ ቤተሰብ በመኖር ነው ምላሽ የምንሰጠው። መልሳችን ወንድማማችነት ቤተሰብአዊነትና ወዳጅነት ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አያይዘው፥ እግዚአብሔር ያለፈው ስሕተታችን ግድፈታችን ሳይሆን በአንድነት የምንኖርበት ዓለም ለመለወጥ ላይ ያለን መጻኢ ፍላጎትን ነው የሚመለከተው። ስለዚህ ሁሉም የዚህ የዓለም አቀፍ ወጣቶች ተሳታፊ አድማስን የሚለውጥ የወንድማማችነት ተመክሮ ተጨባጭ ምልክት መተው ይገባዋል እንዳሉ አስታውቀዋል።