Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ወጣቶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በብሎኒያ የምሕረት አደባባይ በወጣቶች የተደረገላቸው አቀባበል


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በፓላንድ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ አምስት ሰዓት ተኵል በክራኩፍ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማ ብሎኒያ በሚገኘው የምኅረት አደባባይ በብዙ ሺሕ የሚገመቱት የ31 ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፍያ አቀባበል ተደርጎላቸው ወጣቶችን እየተዘዋወሩ ሰላምታን አቅርበው እንዳበቁም የክራኩፍ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ድዝዊች የእንኳን ደህና መጡ መልክት ካስድመጡና ወጣቶቹ ያቀረቡት መንፈሳዊ ትርኢት ቀርቦ ኣንዳበቃ መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል ቅዱስነታቸው ባስደመጡት መልእክት፥

ውድ ወጣቶች እንደምን ዋላችሁ

ለመገናኘት በቃን አደል! ላደረጋችሁልኝ የሞቀ አቀባበል አመሰግናችኋልሁ! ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊችን ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ዓለማውያን ምእመናን በጠቅላላ በዚህ በዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀን በመሸኘት አብሮአችሁ ለተገኙት ሁሉ አመሰግናችኋለሁ። በዚህች ዕለት እንድንገናኝ ሁኔታውን ላመቻቹት እምነታችንን ለማክበር እንድንችል ቅድመ ዝግጅቱን ላከናወኑት ሁሉ ምስጋናዮን አቀርባለሁኝ። ሁላችን ዛሬ ባንድነት እምነታችንን እናከብራለን።

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቀድመው ለተነበዩትና ላስጀመሩት የተለያየ የዓለም ሕዝብ ባህሎች ቋንቋዎችን የሚወክሉ ወጣቶች ባንድ ላይ ተገናኝተው ኢየሱስ ዛሬ በመካከላችን ኅያውነቱን እንድናከብር ላነቃቁት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዚህች በተወለዱባት አገር ተገኝቼ አመሰግናችኋለሁ። ከላይ ሰማየ ሰማያት ሆነው እየሸኙን ናቸው። በመካከላችን ያለው ኅያው ኢየሱስን ለማክበር! ኅያው ነው ለማለት እዚህ እንገኛለን። ኅያው ነው ስንል እርሱን ለመከተል ያለንን ፍላጎት የእርሱን ተከታይነትታችንን በጋለ ስሜት እንገልጣለን።

በመካከላችን ያለው ወዳጅነት ለማክበር ከኢየሱስ ጋር ያለን ወዳጅነት ለማደስ መገናኘታችን በመካከላችን ያለው ወዳጅነት የሚያበረታታና ይኸንን ወዳጅነት ለሌሎች ለማካፈል የወንጌልን ሐሴት በማጣጣም ሌሎችን በሰቃይና በችግርም ጊዜ ወዳጅነት ለማካፈል የሚያስችለው ከኢየሱስ ጋር ያለን ወዳጅነት የላቀ ሥፍራ ነው።

በዚህ ለ 31 ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የጠራን ኢየሱስ፥ ምሕረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኛሉና (ማቴ.5፡ 7) ይለናል። ይቅርታን የሚያወቁና የሚሰጡ ርህሩህ ተቆርቋሪ ልብ ያላቸው ብፁዓን ናቸው። ምክንያቱም ለሌሎች መልካም የሆነውን የሚናገሩ ናቸውና። የተረፈህን ሳይሆን የበለጠው መስጠት።

ወድ ወጣቶች የተከበረችው የፖላንድ መሬት በበዓል መንፈስ ተላብሳለች በእነዚህ ቀናት ፖላንድ የምኅረት ወጣት እድሜ መግለጫ ለመሆን ትሻለች። በዚህ በምኅረት ዓመት ሁላችን እዚህ የተገኘነውና እዚህ ለመገኘት ያልቻሉት ሁሉ ነገር ግን በተለያየ የመገናኛ ብዙኃን አማካኝንት ለሚሸኙን ወጣቶች በጠቅላላ የፖላንድ መሬት እውነተኛ የምሕረት ኢዮቤል እንድትሆን ለማድረግ ነው።

ጳጳስ እያለሁ በተመክሮ ከተማርኩት ውስጥ አንዱ እርሱም ከወጣቶች የተማርኩት፥ ደስ የሚያሰኝ ውብ የሆነው የሚያስተነትኑትን ለመኖር የሚጣጣሩት በጋለ ስሜታቸውና በሙሉ ኃይላቸው ሕይወት የመሻት ያላቸው ፍላጎት ነው፡ ይኽ ደስ የሚያሰኝ ውበትና ውህበትም ነው። ይኽ የመኖር ውበት ከየት ነው የሚገኘው? ያንድ ወጣት ያንዲት ወጣት ሕይወት በኢየሱስ ሲነካ አበይት ነጋራትን ይከውናል። ያንን ሁሉም ያው ነው መለወጥም ሆነ ማደስም አይቻልም የሚለውን አመለካከት የሚቃወም ወጣት ትውልድ ያለው ምኞት የሚያቀርበው ጥያቄና ህልም አወንታዊ ግፊት ነው። ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ከዚያ ዘወትር የወጣትነት እድሜ ያለው የእርሱ መንግሥት አባላት እንሆን ዘንድ ዘወትር ለሚጠራው በአብ ምህረት ላይ ያላትን እምንት ለማደስ እናንተን ትመለከታለች ከእናንተ ትማራለች።

ምሕረትን የሚያወቅ መሐሪ ልብ ምቾት ለመተው ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ሁሉንም ለማቀፍ አይፈራም። መሐሪ ልብ ቤት መጠለያ የሌለውን የቤተኝነት መንፈስ ለመፍጠር ቤቱንና ንብረቱን ጥሎ ለሚሰደደው መጠጊያ ለመሆን ይችላል። ስደተኛውና ተፈናቃዩን ለመቀበል ይችላል። ተካፍሎ መኖርን ይችላል። ምሕረት ስንል ዕድል ነገ ታታሪነት ታማኝነት መስተንግዶ ገዛ እራስ መክፈት የጋለ ስሜትና ሕልም ማለት ነው፡ ኅያው የሆነ ሕይወት።

ገና ወጣት እያለ  በእድሜ እንደገፋ ጡረተኛ ተምስሎ ሲኖር ማየቱ ያሳዝነኛል። ገና ግጥሚያው ሳይጀመር እጅ የሚሰጥ ወጣት ማየት ግጥሚያው ሳይጀመር የሚማረክ ጉዞው ሳይጀመር ከወዲሁ ደከመኝ የሚል ሕይወታቸው ክብር እንደሌለው አድርገው የሚኖሩ ባልተስተዋለ መኖር የሚያልፉ ማየቱ ያሳዝነኛል … የወጣትነት እድሚያቸው በተለያየ የተሳሳተ ምርጫ የሚከስሩ ሳይ ልቤ በሐዘን ይነካል። በአገሬ አነጋገር ጭስ የሚሸጡ እንደሚባለው ሁሉ እርሱም የሚያነወልል የተሳሳተ እምነት የሚቸረችሩ የወጣቱን የበለጠውን ዕድሚ የሚነጥቁ ለሚነዙት ትምህርት የሚማረክ ሳይ በጣም አዝናለሁ።

ስለዚህ ወዶቼ እርስ በእርሳችን ለመረዳዳት እንድንችል እዚህ በአንድ ላይ ተገናኝተናል ምክንያቱም የበለጠው የወጣትነት እድሜአችን እንዲሰረቅ አንፈቅድ ለማለት እዚህ ተገናኝተናል። የበለጠው ኃይላችን ደስታን በሐሰተኛው ትምህርታቸው እንዲሰረቅብን አንፍቀድ።

ውድ ወጣቶች፥ አምሮ ለሚሰርቀው ከገዛ እራስ ለሚያርቅ አታላይ የሆነውን ለሕይወታችሁ ትሻላችሁ ወይንም የመኖር ሐይሉ እንዲሰማችሁ ኅያዋን መሆናችሁ እንዲሰማችሁ ለሚያደርገው መንገድ እውነትና ሕይወት ለሆነው እሺ ትላላችሁ? እውነተኛው መልሱ ጽንሰ ሐሳብ ቁስ አካል ሳይሆን ኅያው የሆነው ኢየሱስ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው የመኖርን ለመኖር የጋለ ስሜት የሚሰጥ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትርጉም አልቦ በሆነው በትንሹ ነገር ደስተኞች እንዳንሆን ያደርገናል። ደስታችን ሙሉ ሕይወት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ተሸንፊያለሁ ብለን ከወደቅንበት ሊያነሳንና ከወደቅንበት ለመነሳት እንችል ይደግፈናል።

ዛሬ የተነበበው ወንጌል ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ላይ እያለ በማርታ ማርያምና አልአዛር ቤት በእንግድነት እንደገባ ያወሳል። በማለፍ ላይ እያለ ወደ ቤቱ ጎራ ይላል። ሁለቱ ሴቶች የሌላውን ስቃይ የሚካፈለውን ያስተናግዳሉ። ማርታ ሽርጉድ ትላለች። እርሷ ያንን በዙውን ጊዜ ጥድፊያ ከዚያ ወደዚያ መራወጥን ሓሳባችንና ቀልባች በመዋከቡ ተግባር የመሰረቁ ጉዳይ ምልክት ነች። ማርያም በኢየሱስ እግር ሥር ሆና ተማርካ ትቀራለች። እነዚህ ሁለት መንፈስ ብዙውን ጊዜ በሕይወታችን ይፈራረቁብናል። በዚህ በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ኢየሱስ ወደ ቤታችን ሊገባ ይፈልጋል። እንደ ማርታ ላይ ታች ማለታችንን እንደ ማርያም እርሱን ለማዳመጥ የምናሳየው ዝግጁነታችን ያያል። እንድናዳምጠው ይፈልጋል። በእርሱ የመታመን ብርታት ሊኖረን ይገባል። እነዚህ ቀናት የኢየሱስ ቀናት ናቸው። ሊያዳምጠን እንድቀበለውም ዘንድ አብሮን በግልም ሆነ በኅብረት በምናደርገው ጉዞ ሊሸኘን በመካከላችን ይገኛል።

ኢየሱስን የሚቀበል የሚያስተናግድ ኢየሱስ እንዳፈቀረው ያፈቅራል። ስለዚህ ሙሉ ሕይወት ትፈልጋለህ ትፈልጊያለሽ ወይ ሲል ይጠይቀናል። መልሱም ደስታ የሚሰጠውም ምሕረት መሆኑ ይገልጥልና። ምሕረት የወጣትነት ገጽታ ያለው ነው። ልክ ምኅረት በኢየሱስ እግር ሥር የተቀመጠቸው ማርያም ተምሳያ ነው። ልክ እንደ የናዝራዊቷ መርያም እነሆኝ ስትል የሰጠቸው መልስ ነው፡ የምኅረት እናት ስለሆነችም በሁሉ ትውልድ ብፅዕት ትባላለች።

ኢየሱስ የምኅረት ድፍረት እንዲኖረ፡ አገናኝ እንጂ ለያይ ግንብ የማይገነቡ ያደርገን ዘንድ ጌታን እንለምነው። ድኻው የተናቀው ለብቻው የተተወው የሕይወት ትርጉም ያጣውን ለመደገፍ የሚያስችል ድፍረቱን ይስጠን። እንደ ማርያም ከኤልዛቤጥ ጋር እኛም በእድሜ ባለ ጸጋ ከሆኑት ጥበብን እንማር።

መሐሪው ፍቅርህን ለማካፈል ጌታ ሆይ ላከን። ሕይወት ከምሕረት በመንደርደር መኖር ሲጀመር ሙላት ይኖረዋልና ይኽን ማንም ሊነጥንቀው የማይቻለው ምሉእ ሕይወት እንሻለን። አሜን በማለት ያስደመጡት ንግግር ማጠቃለላቸው ፒሮ አስታወቁ።