Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ወጣቶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በፖላንድ ፕሮኮቺም ከተማ የሚገኘውን የሕጻናት ማከሚያ ቤት ጎበኙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከክራኩፍ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው በደቡባዊ ፖላንድ ክልል የሚገኘው የአገሪቱን አቢይ የሕፃናት ማከሚያ ቤት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 10 ሰዓት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስነታቸው በማከሚያ ቤቱ በተገኙት በአገሪቱ መራሔ መንግሥት በኣታ ማሪያ ስዝይድሎ በማከሚያ ቤቱ ዋና አስተዳዳሪና እዛው የተገኙት 50 ታካሚ ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው አቀባበል ተድርጎላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ተደምጦ እንዳበቃም ባስደመጡት መልእክት፥

ውድ ወንድሞቿና እህቶቼ

በክራኩፍ እያካሄድኩት ባለው ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት ይኸንን ሕክምና ቤት ሳልጎበኝ እንደማልቀር ቀድሜ ያሰብኩትና በማከሚያ ቤት ከሚረዱት ሕሙማን ሕጻናት ጋር ለመገናኘት አቢይ ጉጉት ነበረኝ ብለው አያይዘውም የእንኳን ደህማ መጡ ንግግር ላስደመጡት ለመራሔ መንግሥትና ለሕክምናው ቤት ዋና አስተዳዳሪ አመስግነው፡ በእያንዳንዱ ታማሚው ሕፃን ጎን ለመሆን ለሕክማ በተኛበት አልጋ አጠገብ ሆኜ አንድ በአንድ ሁሉም አቅፌ ለመሳምና የሚሉኝን ለማዳመጥ አብሬ ያንን በውስጣችሁ ላለው መልስ ለመስጠት የሚያዳግተው ስቃያቸውን ጽሞና በመካፈል ለመጸለይ እወዳለሁ።

ኢየሱስ የታመሙትን ፈውስ የሚሹትን ይገናኝና ይቀበላቸው ነበር። ሊያገኛቸውም ፈቅዶ ወደ እነርሱ ይሄድ እንደነበር ወንጌል ያወሳናል። እርሱ ዘወትር ስለ እነርሱ ግንዛቤው ያለው ልክ እንደ ምትመለከታቸው እናት አይኖቹን በአንርሱ ላይ በማኖር የውስጣቸው ስሜት ተካፋይ ይሆናል።

ልክ እንደ የኢየሱስ አቀራረብ እንደ ክርስቲያን መጠን ለህሙማን በጽሞና ለማጽናናት በጸሎት ቅርብ የመሆን ክህሎት ቢኖረን እንዴት ደስ ባለኝ፡ የወቅቱ ተጠቅሞ መጣል ሌላው እንደ ጥራጊ መመልከት የሚለው ባህል ሰለባ ድኾች በቀላሉ ለአደጋ ሊጋለጡ የሚችሉት ዜጎች ናቸው። ጨካኝ ባህል። በዚህ ማከሚያ ቤት እነዚህ ታማሚ ሕፃናት በሚገባ አቀባበል ተደርጎላቸው ሲታከሙና ሰብአዊ ድጋፍ ሲቀርብላቸው ማየቱ እንዴት ደስ ያሰኛል። ለምትሰጡት የፍቅር አገልግሎት አመስግናችኋለሁ። ይኽ ነው የእውነተኛው ሰብአዊነት ክርስቲያናዊ ተግባርና ሥልጣኔ ትእምርት። የማኅበራዊና የፖለቲካው ዓይነ ልቦና ማእከል እጅግ የተጎዱትና ጐስቋሎች ሊሆኑ ይገባቸዋል።

ብዙውን ጊዜ ወላጆች የህሙማን ልጆቻቸው ጉዳይ ለብቻቸው የሚወጡት አጋጣሚ ሆኖ ይታያል። ምን ማድረግ ይችላል? ከዚህ የፍቅር ሥልጣኔ ከሚታይበት ተጨባጭ ሥፍራ በሆነው ሕክምና ቤት ውስጥ ተገንቼ ልለው የምፈልገው ነገር ቢኖርም ከክርስቲያናዊ ፍቅር ለስቁል ኢየሱስ ካለን ፍቅር ለክርስቶስ አካል ካለን ፍቅር የተነቃቃ ተግባር የሚኖርበት የተቀባይነት ባህል እንዲበረክት ነው። ሁላችን በሰብአዊነት እንድናግድ የሚያበቃን በፍቅርና በየዋህነት የተጎሳቆሉት በከፋ ድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙትን ማገልገል ያስፈልጋል። ይኽ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ክፍት ያደርገናል። የምኅረት ተግባር የሚፈጽም ሞትን እይፈራልም።

ያንን የታመሙትን መጠየቅ ለታመመው መድረስ የሚለው ወንጌላዊ ጥሪ የሕይወታቸው ጥሪ በማድረግ የሚኖሩ ሁሉ በርቱ እላለሁኝ። ሁሉንም የማከሚያ ቤቱ ሐኪሞች የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎ የማከሚያ ቤቶች ቤተ ጸሎት ቆሞሶችና የበጎ አድራጎት  አባላት ሁሉ በርቱ እላለሁኝ። አገልግሎታችሁ የተዋጣለት እንዲሆንም በዚህ ማከሚያ ቤትም ሆነ በተለያዩ ማከሚይ ቤቶች በምትፈጽሙት ግብረ ሠናይ ሁሉ ጌታ ይደግፋችሁ፡ ውስጣዊ ሰላምና የየዋህነት ብቃት ያለው ልብ ይጸግዋችሁ።

እዚህ ለተካሄደው ግኑኝነት ሁላችሁን አመሰግናለሁኝ። በውስጤ አኖራችኋለሁ። በፍቅርና በጸሎት አስባችህኋለሁ። እናንተም አደራ ስለ እኔ መጸለዩንም አትዘንጉ በማለት ያስደምጡት ንግግር ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ አስታውቋል።