Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ግብረ ሠናይና ትብብር

አማን፡ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍላጎትና ትብብር የተቋቋመው የግብርና ኢንዳስትሪ


ተቀባይነት ያለው የእርሻ ልማት ለማስፋፋት በሚል ዓላማ በ 10 ሺሕ ሄክታር መሬት የ 600 መቶ ወይራ ዛፍ ተከታላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልዩ ፍላጎት መሠረት ገቢራዊ መሆኑ አቡና የተሰየመው የአማን ሰበካ ይፋዊ ድረ ገጽ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎ አስታወቀ።

ይኽ የምኅረት ያታክልት ሥፍራ  በሚል ስያሜ የሚጠራው ተቀባይነት ያለው የእርሻ ልማት የሚያነቃቃው የግብርና ኢንዳስትሪ ባለፈው ሐሙስ እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም.  በሰላም ንግስት ማእከል አቅራቢያ ባለው የእርሻ መሬት የተከላው ፍጻሜ በእየሩሳኤም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋልና በዮርዳኖስና ኢራቅ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አልበርቶ ኦርተጋ ማርቲን በተገኙበት በይፋ መመረቁ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥

የእርሻው መርሃ ግብር ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብ የቤተ ክርስቲያን አሳቢነትና ቅርበት ትእምንር ነው

ይኽ ተቀባይነ ያለው የእርሻ ልማት እቅድና በተለይ ደግሞ የመካከለኛው ምሥራቅ የግብርናው ኤኮኖሚ ለማበረታታት የሥራ አጥነት ችግር ለማቃለል ተፈጥሮን ለማክበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ የ 2015 ዓ.ም. ተስተናግዶ በነበረው ዓለም አቀፍ  የባህል የኤኮኖሚ ትርኢት ቅድስት መንበር በመሳተፍ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በሚላኖ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበትና ድጋፍ ለማበረታታት በሚል እሳቤ ያስተላለፉት የአደራ ጥሪ የጳጳሳዊ ውሁድ ልብ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሰጉንዶ ተኻዶ ሙኞዝ በይፋ እንዳስተዋወቁት ዘክሮ የዚያ ጥሪ ውጤትም ይኸው በአማን ገቢራዊ ለመሆን መብቃቱንም ያመለክታል።

የግብርናው ኢንዳስትሪ በሕዝቦችና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት የሚያነቃቃ የሚያስተባበር ነው

ይኽ የምኅረት የአታክልት ሥፍራ በሚል መጠሪያ የተሰየመው የእርሻውን ኢንዳስትሪ መርቀው የከፈቱት ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ኦርተጋ ማርቲን ባስደመጡት ንግግር ለተፈናቃዮችና ለስደተኞች እንዲሁም በሥራ አጥነት የተጠቃው ዚጋ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ብቻ ሳይሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እቅዱን ሲያስቡ  እንዳሉት የውይይትና የግኑኝነት ሥፍራ ጭምር መሆኑ አብራርተው በተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች መካከል የውይይት ባህል የሚያነቃቃ  ሥፍራ ነው ሲሉ፥ በዮርዳኖስ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ ለሚጠራው  የሰብአዊ እርዳታ ማኅበር ቅርንጫፍ ሊቀ መንበር ዶክተር ዋዔል ሱለይማን የዚህ ዓይነቱ ተመሳሳይ መርሃ ግብር የሥራ እድል ለመፍጠር የሚችል ተቀባይነት ያለው  የልማት እቅድ በተለያየ መስክ እየተበረታታ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት የአማን ሰበካ ይፋዊ ድረ ገጽ ጠቅሶ ያመለታል።