Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / ግብረ ሠናይና ትብብር

ቅዱስ አባታችን፥ አገልግሎታችሁ የሰው ልጅ እምባ ማበስ


በአህጽሮተ ቃሉ ኡኒታልሲ በሚል መጠሪያ የሚወቀው ኅሙማን ወደ ቅዱስ ሥፍራ ዘሉድር ወደ ተለያዩ ብሔራዊና ዓለም አቀፍ ቅዱሳት ሥፍራ የሚያካሂዱት መፈሳዊ ንግደት የሚንከባከበው ካቶሊካዊ ማኅበር የተመሠረተበት 80ኛው ዓመት ምክንያ በኢጣሊያ ሎረቶ ከተማ በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በሚዘከርበት ዕለት የሮማ አውራጃና የላዚዮ ክፍለ ሃገር የማኅበር ቅርንጫፍ አባላት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊክ  ሊቀ ካህናት የቅዱስ ጴጥሮስ ተግባረ ዕድ ሊቀ መንበር የአገረ ቫቲካን ኅየተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ  በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ የምኅረት ዓመት ምክንያት ኅሙማንን ወደ ቅዱሳት ሥፍራ በምኅረት ቅዱስ በር ለማለፍ ዓልመው የሚያካሂዱት መንፈሳዊ ንግደት በይፋ መጀመራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ  አስታወቀ።

ቅዱስ አባኣታችን ለማኅበሩ ባስተላለፉት መልእክት የማኅበሩ አባላት በስቃይ የሚገኙት ወንድሞቻን እንባ የምታብሱ የእግዚአብሔ ፍቅር ተጨባጭ መግለጫ ናችሁ በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ  አክሎ፥ ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ የቅዳሴውን ስነ ሥርዓት መርተው ባሰሙት ስብከት፥ የታናናሽ የተናቁትን የኅሙናን ወንድሞቻችን ሰብአዊ መፈሳዊ ፍላጎት ለማርካት በእምነት ተደግፋችሁ የምታገለግሉ ናችሁና በዚህ በምኀረት ዓመት ወደ አብ ምኅረት የሚጓዙትን ኅሙማን ነጋድያን በመሸኘት የምታከናውኑት አገልግሎት የጌታ ምኅረት ትመሰክራላችሁ እንዳሉ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን ርሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት፥ ኅሙማንን በመሸኘት የዚያች የቅድስት ቤተሰብ አብነት የሆነው ፍቅር የሚያረጋግጠው ወዳጅነት የእርስ በእርስ መፈቃቀርና መተሳሰብ መስካሪያን ናችሁ በማለት ማኅበሩ የሚሰጠው አገልግሎት የእግዚአብሔር የዋህነትና ምኅረት መግለጫ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ  ጠቅሶ፥ ቅድስት ድንግል ማርይም ዘሎረቶ በስቃይ በችግር የሚገኙትን የታመሙትን ሁሉ በመቀበል እምባቸው በማበስ የጌታ መጽናናት ስለ እነርሱ ታማልዳለች። እናንተ የእርሷ አማላጅነት የምትጸልዩ የማኅበሩ አባላት የምትኖሩት የእርሷ መንፈሳዊነትን አደራ፡ በጦርነት አውድማ የሚግገኝ ሁሉንም የሚያገለግል መፈሳዊና አካላዊ ድጋፍ የሚሰጥ ማከሚያ ቤት የሆነቸውን ቤተ ክርስቲያን ወክሉ እንዳሉ ያመለክታል።

ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በቅርቡ በግሪካዊቷ ደሴት ለስቦ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስታውሰው በዚያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት እዛው በስደተኞች መጠለያ ሰፈር የምትገኙት ቤተሰቦች ውስጥ  ያንዲት ቤተሰብ አባል ሕፃን እንደ ገጸ በረከት የሰጣቸው በራሱ እጅ የነደፈው ስእል አስታውሰው፡  የስደተኞችና ይተፈናቃዮች እምባና ስቃይ የሚመሰክር ነው ብለው። እደራ እናንተ እንባን የሚያብሱ የእግዚአብሔር እጆች ሆናችሁ ያንን በስቃይ የሚያነባው አይን ፈገግታ የሚታይበት እንዲሆን በጌታ መንፈስ ደገፉ እንባውን አብሱ አደራ እንዳሉ የቅስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ  አስታወቀ።