Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በላቲን አመሪካ በመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በላቲን አመሪካ በመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማከናወን ዛሬ ጥዋይት ከቫቲካን ተነስተዋል። በመኪሲኮ ለአንድ ሰሞን የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት 12ኛ መሆኑ ነው። 

ቅድስነትቸው ከሮም ለኦናርዶ ዳቪንቺ ዓለም አቀፍ ማረፍያ ሲነሱ የፖርቶ ሳንታ ሩፊና ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጂኖ ረአሊ እና ሌሎች ውሉደ ክህነት አሸነኘት አድርጎውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ መክሲኮ ከመጓዛቸው በፊት በኩባ ኾሰ ማርቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ከ12 ሰዓት 15 ደቂቃ በረራ ከዝግጅታችን ፍጻሜ ግማሽ ሰዓት በኃላ አውሮፕላን ማረፍያው እንዲደርሱ ይጠበቃሉ።

ኾሰ ማርቲ አውሮፕላን ማረፍያ እንደ ደረሱ የኩባ ደሴት መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት ራውል ካስትሮ በኩባ የቅድስት መንበር እንደራሴ ብጹዕ አቡነ ጆርጆ ሊንጓ የፕሮቶኮል ተጠሪ የሳን ክሪስቶባል ደላ ሃቫና ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ ካርዲናል ኽይመ ኦርተጋ ኢ ኣአላሚኖ የሳንትያጎ ደ ኩባ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዲዮኒስዮ ጋርሲያ ኢባነጽ አቀባበል ያደጉላቸዋል።

በየርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሀ ግብር መሰረት ፕረሲዳንት ራውል ካስትሮርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን አውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ ወደ ሚገኘው የእንግዶች ማረፍያ ያደርሰቸዋል። 

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና የሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል በኾሰ ማርቲ ደላ ሃባና አውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ በሚገኘው የእንግዶች መቀበያ ሳሎን ተገናኝተው በአስተርጓሚ እንደሚወያዩ የሐዋርያዊ ጉብኝቱ መርሀ ግብር ያመለክታል።  

የሮም ሀገር ስብከት ጳጳስ እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ሲገናኙ በታሪክ ይህ የመጀመርያ ግዜ በመሆኑ ግንኝቱ ታሪካዊ ያሰኘዋል። ስለ ሆነም ግንኝነቱ ድንቅ እና አለፌታ ነው ተብለሎታል። 

ይሁን እና፡ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና በየሞስኮው እና ኩላዊት ሩስያ ፓትርያርክ በብጹዕ ወቅዱስ ክሪል መካከል በሚካሄደው ታሪካዊ ግንኙነት በዮሞስኮ ፕትርክና የውጭ ጉዳይ ዋና ሐላፊ ሜጥሮጶሊጣን ሂላርዮን በቅድስት መንበር ለክርስትያን አንድነት የቆመ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ተሳታፊ እንደ ሚሆኑ መርሀ ግብሩ ያሳያል።

በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል መካከል የሚካሄደው ግንኙነት እና ውይይት ከተጠናቀቀ በኃላ የኩባ መራሄ መንግስት በሚገኙበት ሌላ የእንግዶች ማረፍያ የጋራ መግለጫ እንዲሰጡ እንደሚጠበቁ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ዑደት መርሀግብር ያመለክታል።በዚሁ መርሀ ግብር መሠረት፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል በየጋራ በጣልያን እን ሩስያ ቋንቋዎች በተጻፉ መግለጫዎች ፊርማቸውን ያሰፋራሉ የጋራ መግለጫዎቹን ይለዋወጣሉ ሁለቱም ንግግር ያደረጋሉ።

የሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል ኩባን እየጐበኙ መሆናቸው ይታወቃል። ይሁን እና በኩባ ሰዓት አቁጣጠር ከቀትር በኃላ አምስት ተኩል ሲሆን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከየሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ ክሪሊ እና ከየኩባ ደሴት መራሄ መንግስት ከፕረሲዳንት ራውል ካስትሮ ተሰናብተው ከሃቫና ኾስ ማርቲ ሀገራት አቀፍ ማረፍያ ተነስተው ወደ መክሲኮ ሲቲ እንደሚያቀኑ ሐዋርያዊ መርሀ ግብሩ ያስረዳል። ከሁለት ሰዓት በረራ በመክሲኮ ሰዓት አቁጣጠር ከምሽቱ ሰባት ተኩል በሮም ሰዓት አቁጣጠር ሌሊት ሁለት ሰዓት ተኩል መሆኑ ነው መክሲኮ ሲቲ በኒቶ ሱአረስ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ እንዲገቡ ይጠበቃሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በቅድስት መንበር የክርስትያን አንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና የፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል መገናኘት ቆራጥ ርምጃ እና ለክርስትያኖች አንድነት ትልቅ እመርታ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የሁለቱ የሃይማኖት አባቶች እንዲገናኙ ለዓመታት የወሰደ የዲፖሎምቲክ ጥረት መካሄዱ ያወሱት ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኾክ በመጨረሻ ለመገናኝት መቻላቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ጸጋ እንደሆነ አክለው ገልጠዋል። በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና በፓትሪይሪክ ክሪል መካከል የሚካሄደው ታሪካዊ ግንኙነት ለምን ኤውሮጳ ውስጥ አልተካሄደም ለምንድነው በላቲን አመሪካ ኩባ ውስጥ እንዲካሄድ ተወሰነ በማለት ከተለያዩ የማህበረ ሰብ ክፍሎት ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ለጥያቄዎቹ መልስ ሲሰጡ፡ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቱርክ ቆስጥንጢንያ ላይ ያካሄዱት ጉብኝት አጠቃልለው ወደ መንበር ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ሲመለሱ ፓትርያርክ ክሪል በፈለጉበት ግዜ እና ቦታ ልንገኛን እንችላለን ባሉት መሠረት መከናወኑ አብራርተዋል።