Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ኅብረተሰብ / አፍሪቃ

በብሩንዲ ርእሰ ከተማ ቡጁምቡራ በተነሳው ብጥብጥ ሁከትና ግጭት ሰዎች ለሕልፈት ተዳረጉ


በብሩንዲ ርእሰ ከተማ ቡጁምቡራ በተነሳው ብጥብጥ ሁከትና ግጭት ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸው በርካታ ከባድ እና ቁላል መቁሰልት እንደደረሰባቸው ከቦታው የሚደርሱ ዜናዎች ያመለክታሉ። ባለፈው ወርሀ ግንቦት ፕረሲዳንት ኑኩርንዚዛ ከሕግ ውጭ ለሶስተኛ ግዜ ለፕረሲዳንትነት ምርጫ እንደሚቀርቡ ባስታወቁብበት ግዜ የተነሳው ብጥብጥ የባሰ መሆኑ ዜናዎቹ ገልጠዋል።

በ150 የሚገመቱ ታጣቂዎች በሶስት ወታደራዊ ሰፈሮች ጥቃት መሰንዘራቸው እና ኀይለኛ ግጭት መካሄዱ ከቡጁምቡራ ተመልክተዋል።

በሩንዲ የርስ በርስ ጦርነት ይነሳል ተብሎ መሰጋቱ እና የሀገሪቱ ህዝብ ለፍርሀት መጋለጡ ተያይዞ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

በሩንዲ የሚታየው ግጭት ጐሳዊ ሳይሆን ፖሊቲካዊ ግጭት እንደሆነ እና ሁኔታው እንደተወጠረ መሆኑ ዜናው አክሎ ገልጠዋል።

ስልጣን ላይ ያለውን የፖሊቲካ ፓርቲ እና ተቃዋሚ ኀይሎች የሀገሪቱ ችግር እና ሁኔታ በውይይት ከመፍታት ይልቅ በኀይል ለመፍታት ስለሚቃጡ በቀላሉ ሁከት ግጭት እና ብጥብጥ እንደሚከሰት ተገልጠዋል።