Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:
የቫቲካን ሬድዮ

መታወቂያ ገጽ / ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ / ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሓዋርያዊ ዑደት በከንያ ኡጋንዳና የመካከለኛ አፍሪቃ ሪፓፕሊክ


ሮብ ኅዳር 25 ቀን 2015 በሮም ሰዓት አቆጣጠር ስምንት ሰዓት ላይ በሮም ከሚገኘው የሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ የፊዮሚቺኖ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ተነሥተዋል፣ ቅዱስነታቸው ከቫቲካን ተነሥተው ፊዩሚቺኖ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ሰባት ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ሲደርሱ የመጀመርያ የአፍሪቃ ሓዋርያዊ ዑደታቸው ወደሆነችው ወደ ከንያ ስምንት ሰዓት ላይ በረራ ጀመሩ፣ ይህ ሓዋርያዊ ጉዞ ኡጋንዳንና መካከለኛው የአፍሪቃ ሪፓብሊክ ጭምር ያካትታል፣ ቅዱስነታቸው ዘወትር እንደሚያደርጉት ከቫቲካን ይዞዋቸው የተጓዘ መኪና በአይሮፕላኑ አጠገብ ሲያደርሳቸው ጥቁር ሻንጣቸውን ይዘው ሲወርዱ በቦታው የፖርቶሳንታ ሩፊና ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ረአሊ እና የሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣኖች ሰላምታ ተለዋውጠው አየሮፕላን ላይ ወጥተው ውስጥ ከመግባታቸው በፊት እጃቸውን እያወዛወዙ ሰላምታ አቅርበዋል፣

ወዲያውኑ አይሮፕላኑ ከተነሣ በኋላ ዘወትር እንደሚያደርጉት የጣልያን አገር አየር ክልል ውስጥ እያሉ ለጣልያን አገር ፕረሲደት ሰጅዮ ማታረላ ተለግራም ልከዋል፣ የተለግራሙ ይዘትም “በከንያ ኡጋንዳና መካከለኛው የአፍሪቃ ሪፓብሊክ ሓዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግና በዚሁ ውድ አገሮች የሚገኙ በእምነት ወንድሞቻችን ጋር ለመገናኘት በታላቅ ጉጕት ጉዞየን በምጀምርበት ጊዜ ለእርስዎ ለተከበሩ ፕረሲደንት የተከበረ ሰላምታየን ለማቅረብና ለመላው የጣልያን አገር ሕዝብ በጎ ነገርና ብልጽግና በልብ ስጸልይ ይህንን መልእክት እጽፍልዎታለሁ” የሚል ሲሆን የጣልያን አገር ፕረሲደትን ሰርጅዮ ማታረላ ደግሞ ይህንን ተለግራም በተቀበሉ ጊዜ ወዲያውኑ “በከንያ ኡጋንዳና መካከለኛው የአፍሪቃ ሪፓፕሊክ ጉዞ መጀመርያ ላይ ሳሉ ለጻፉልኝ መልእክት ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፣ የጣልያን አገርና መላው ዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ይህንን የመጀመርያ የአፍሪቃ ጉዞአችሁን በታላቅ ትኩረት እየተከታተሉት ነው፣ የአፍሪቃ የዕድገትና ሥልጣኔ ችሎታ በጦርነትና ፖሎቲካዊ አለመረጋጋት እንዲሁም በድህነትና አሳሳቢ በሆኑ ማኅበረሰባዊ የእኩልነት ጥያቄዎች ታግቶ እንዳለ ብሩህ ሲሆን የቅዱስነትዎ ጉብኝት በቦታዊ ለሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን የድጋፍና የመበረታታት ምክንያት ሆኖ በምትጐበኝዋቸው አገሮች አስፈላጊ የሰላም የወንድማማነትና የውይይት ምልክት ይሆናል፣ ይህም ለአገሪቱ መጻኢ የብሩህ ተስፋ መል እክት ይሆናል፣ ቅዱስነትዎ እንደገና ጠለቅ ያለ አክብሮትየና ሰላምታየን ለማሳደስ ይህንን አጋጣሚ እጠቀማለሁ” የሚል ነበር፣

ቅዱስነታቸውን ይዛ የምትበር የአሊታልያ አየር የምታቋርጣቸው አገሮች ግሪክ ግብጽ ሱዳን ኢትዮጵያና ኬንያ በመሆናቸው ለእነዚሁ አገሮች ርእሰ ብሔሮች ማለትም ለግሪኩ ፕረሲደንት ፕሮኮፒስ ፓቭሎፑሎስ ለግብጹ ፕረሲደንት ዓብደል ፋታሕ አል ሲሲ ለሱዳኑ ፕረሲደንት ዖማር አልበሺር ለኢትዮጵያ ፕረሲደንት ሙላቱ ተሾመ እና ለከንያው ፕረሲደትን ኡሁሩ ከንያታ የሰላምታና የመልካም ምኞት ለአገሮቹም ብጽግና በመምኘት ሓዋርያዊ ቡራኬአቸውን የሚለግሱ ተመሳሳይ የተለግራም መልእክቶች ጽፈዋል፣

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ካሁን በፊት አፍሪቃን ከጐበኙ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ከብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛና ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ አሥራ ስድተኛ በኋላ አራተኛ ሲሆኑ የመጀመርያው የዛሬ አርባ ስድስት ዓመታት በፊት እ.አ.አ በ1969 ዓም ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ሲሆኑ የዛሬው ሓውጾተ ኖልዎ ሰላሳ ሁለተኛ መሆኑን የቅድስት መንበር ዘገባ ያመልክታል፣

ከንያን በሚመለከት ደግሞ ከቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሶስት ጉብኝቶች ማለትም እ.አ.አ በ1980፣ በ1985 እና በ1995 ዓም በኋላ ሁለተኛ ር.ሊ.ጳ መሆናቸው ነው፣ በዛሬው ዕለት በረራ ሰባት ሰዓታት ከአሥራ አምስት ደቂቃ 5.389 ኪሎ ሜትር ተጉዘዋል፣ ቅዱስነታቸውን የያዘች አይሮፕላን በኬንያ ሰዓት አቆጣጠር አስራ ሰባት ሰዓት ላይ ከሁለት ሰዓት ተኩል በፊት በጀሞ ከንያታ ዓለም አቀፍ የአይሮፕላን ማረፍያ በወረደች ግዜ የኬንያ ፕረሲደንት ኡሁሩ ከንያታ የናይሮቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ጆን ንጅወ የሚገኙባቸው የሃይማኖት መሪዎችና የተለያዩ መንግሥታዊ ባለሥልጣናት ተቀብለዋቸዋል፣ በአየር ማረፍያው አከባቢ ብዙ ሕዝብ በተለያዩ የኬንያ መንፈሳዊና ባህላዊ ዜማዎች እና ባህላዊ እስክስታ ቤተመንግሥት ሸኝዋቸው፣ ስቴት ሃውስ በማለት በሚታወቀው ቤተ መንግሥት ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው እስከ ሶስት ሺ ሰዎች የመቀበል አቅም ባለው ዳስ የአቀባበል ሥነሥር ዓት ተካሄደ፣ በዚሁ ሥርዓት በኬንያ ብዙ ዓለም አቀፍ የፖሎቲካ ምጣኔ ሃብት ባህልና ተወካዮች እንዲሁም ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፣

ቅዱስነታቸው ኬንያ በደረሱ ግዜ በደረሱ ጊዜ የቅድስት መንበርና የኬንያ አገራዊ መዝሙሮች ከተዘመሩ በኋላ ለቅዱስነታቸው ክብር 21 መድፍ ተተኰሰ፣ በመቀጠልም ወታደራዊ ሰልፍና ሰላምታ ቀርበዋል፣ የኬንያ ፕረሲደንት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አቅርበዋል፣

የኬንያ ስፋት 580.367 ካሬ ኪሎሜትር ሲሆን የሕዝብዋ ብዛት 42.961.00 ይገመታል፣ የካቶሊካውያን ብዛት 32.3% በመቶ ሲሆን 26 አገረ ስብከቶችና 38 ጳጳሳት ያገለግልዋቸዋል፣ በሓዋርያዊ ግብረ ተል እኮ ሲመለከት 925 ቍምስናዎችና ከ6.542 የተል እኮ ማእከሎች ይገኙባቸዋል፣ አጠቃላይ የካህናት ቍጥር 2.744 ሲሆኑ ከእነዚህ 914 ገዳማውያን ናቸው፣ በአገሪቱ የሚያገለግሉ ገዳማውያት 5.505 ሲሆኑ ገዳማውያን ደግሞ 798 ናቸው፣ ከዚህ ባሻገር 4 ዲያቆናትና 550 ም እመናን ሰባክ ያነ ወንጌል እንዲሁም 11.343 የትምህርተ ክርስቶስ መምህራን አልዋቸው፣