2018-07-07 17:46:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በባሪ የአንድ ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት አደረጉ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በባሪ የአንድ ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት አደረጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም በሰኔ 30/3010 ዓ.ም የጣሊያን ግዛት ወደ ሆነችው ባሪ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ይታወሳል። ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋሪያዊ ጉብኚት አንድ ለየት ያለ ሐዋሪያዊ ጉብኝት መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህንን የቅዱስነታቸውን ሐዋሪያዊ ጉብኚት ለየት የሚያደርገው ምክንያት የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች  በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ የሐይማኖት መሪዎች መገኘታቸው እና ሰለሐይማኖት ሕብረት በጋራ በመሆን ጸሎት ማድረሳቸው ይህንን ሐዋሪያዊ ጉብኚት ለየት ያደርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 30/2010 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 2፡00 በቫቲካን ከሚገኘው የኤሊኮፕተር ማረፊያ ተነስተው የ1፡15 ደቂቃ በረራን አድርገው በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 3፡15 ባሪ ደርሰዋል።

ቅዱስነታቸው ባሪ በደርሰቡት ወቅት የባሪ እና የቢቶንቶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ፍራንቸስኮ ካቹቺ፣ የፑሊያ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሚካሄል ኤሚላኖ እና የባሪ ከንቲባ የሆኑት አቶ አንቶኒዮ ዴካሮ ተገኝተው ለቅዱስነታቸው ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በመቀጠል በባሪ ወደ ሚገኘው የቅዱስ ኒኮላስ ባዚሊካ ተጉዘው እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በባሪ በሚገኘው የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም በሚገኝበት ባዚልካ ከደረሱ በኃላ በእዚያው የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር መገናኘታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የቁስጣንጢኒያው የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ የሆኑት ብጽዕ በርተሌሜዎስ ቀዳማዊን እና የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ቴዎድሮስ ዳግማዊ መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በባሪ የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስ ኒኮላስ የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጋራ ታላቅ አክብሮት የሚሰጡት ቅዱስ መሆኑም ይታወቃል። በእዚህ የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም በሚገኝበት ባዚሊካ የሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በጋራ ለሐይማኖት ሕብረት ጸሎት ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በተለይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ስደት እና መከራ በማንሳት ለሰላም ጸሎት ማድረጋቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በተደረገው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ላይ የመግቢያ ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን  ቅዱስነታቸው ካደርጉት የመግቢያ ጸሎት በመቀጠል  በባሪ በሚገኘው የቅዱስ ኒኮላስ ቅዱስ አጽም በሚገኝበት ባዚሊካ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በተለይም የቁስጣንጢኒያው የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ የሆኑት ብጽዕ በርተሌሜዎስ ቀዳማዊን እና የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ቴዎድሮስ ዳግማዊ እና በርካታ ከዓለም ዙሪያ የተውጣቱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርኮች ጋር በጋራ በመሆን ለሐይማኖት ሕበረት እና በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ እና ለቅሶን በማሰብ የአንድ ቀን ሐዋሪያው ጉብኚት እና መንፈሳዊ ንግደት ለማድረግ የቅዱስ ኒኮላስ ቅድሱ አጽም በሚገኝበት በባሪ በተሰበሰቡበት ወቅት ቅዱስነታቸው ካደርጉት የመግቢያ ጸሎት በመቀጠል ከብጹዕን ፓትሪያሮክች ጋር በጋር በመሆን እነርሱን ብቻ ያካተተ ዝግ ስብሰባ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ከእዚያን በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የማጠቃለያ ንግግር ማደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር 12፡15 ላይ ወደ ቫቲካን በሰላም መመለሳቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.